ይድረስ ለአገር ወዳድ ወገኖቼ በያላችሁበት- ምንድነው የተፈለገው? – ከአባዊርቱ!

February 16, 2022

ቆም ብላችሁ አስተውሉ በተለይም ብዙ የማከብራችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖች:: እንዴት በ 4ኛውም አመት አንድ አይነት ስህተት እንሰራለን? እንደምንስ ወያኔ ዛሬም በስሜታችን ይጫወታል? እንደምንስ የነ ጄ/አበባውን የቀጥታ ቃለመጠይቅ ለተከታተለ እውነቱን መረዳት አቃተን?? 45000 ጦር እኮ ነው ሺንት እየጠጡ ከ 300000 የፅልመት እስካፍንጫው ከታጠቀ የጥፋት ሀይል ጋር የተላተሙት:: ሃሎ? ይሰማል ወገኖች? ዛሬ ጄኔራሉ ይፋ ስላወጡት እንጅ አደባባይ ይህን መፃፉ እራሱ ብርክ ያሲዛል:: በበኩሌ ይህን ከሰማሁ በሁዋላ እንኩዋንስ መከላከያንና አቢይን ላንጉዋጥጥ ቀርቶ በቅጡም መተኛቱ ተስኖኛል:: እነ ጌታቸው ረዳ በጤናም አልነበረም ሸዋሮቢት ድረስ በረው የመጡልን አፍረው ተሰብረው ፈረጠጡ እንጅ:: ከሱዳን አቅም እንኳ ለምን እንደተዳፈሩን ከአበባው ገለፃ በሁዋላ ለኔ ግልፅ ሆኗል – ለብዙዎቻችሁ እንደምን ይህ ግልፅ እንዳልሆነ ያማል:: እንዴት አቢይ ሆኑ አበባው: ብርሃኑ ሆኑ ባጫ አቃቂር ይወጣላቸዋል? አገርን ስለታደጉ? ጭራሽ በአፋርና አማራ ክህደት በግላጭ ሊታሙ? ከማልጠብቃቸው ሰዎች? በግልፅ እናፍርጠው እስቲ: አቢይን ሸኔ ወይም ዖነግ ነው ለማለት: አማራና አፋርን ከዳ ለማለት ወይም በዳርዳርታው ለመፎተት ፈጣሪ ይወደዋል? ከዚህ መድረክ ጠፍቼ ነበርአካሄዳችን በጣም ስለሚያም:: ሆኖም አንድ ወገን የሸዋን ዖሮሞ ክእንቅልፍ የሚያባንን ነገር ፅፈው  አባነውኝ : እኔውም ስሜታዊ ሆኜ ከፃፍኩ በሁዋላ ፀፀተኝና ተውኩት እንጅ::

ውድ ወገኖች!!

ወገን የተባለው ሁሉ አጀንዳ እንደቀለብ ተሰፍሮለት ሲባላ ሰዎቹ ልዩ መጅሊስና ሲኖዶስ እየፈጠሩልን ነው:: ገና በኛው ንዝህላልነት ብዙ ጉድ እንሰማለን:: ይህ “እኛ ለየት ያልን ህዝቦች ነን” መዘዝ የእርያንን ነገድ አመድ እንዳደረጋቸው በእብሪት ያበጠው ቀፈታቸው ገና የተረዳው አይመስልም:: ጊዜውን ጠብቆ መፈንዳቱ  ግን አይቀሬ ነው::  የሰሞኑ በከንቲባዋና ሲኖዶሱ መሃል የነበረውን ፈጣሪ ምስጋና ይግባውና ክብርት አዳነች በብልሃት ይዘውታልና ብዙ መናገር አልፈልግም:: እኚህን ብርቱ እህት/ልጅ ቢቻል በሞራል ካልሆነም በፀሎት ማገዝ እንጅ ያልሆነ ስም እየሰጡ መበሻሸቅ አገር አያሻግርም:: የለየላቸው ከሃዲዎችን ሳይሆን ስሜታቸው የተነካውን አገር ወዳድ ወገኖችን ነው እየለመንኩ ያለሁት::

ወገኖች : እንድተጠነሰስልን ጥንስስ ቢሆን የሩዋንዳው ቻይልድ ፕሌይ ነበር የሚሆነው እኮ በአገራችን::  ከዚህ መአት የተረፍነው የተጋመድንበቱ የሺህ አመታት መጫኛ እጅግ ጥብቅ በመሆኑ ብቻ ነው!!

ምን እናድርግ?

ሀ) እስቲ የሚሰሩትን ከመውቀስ መፆም:: ቢቻል ማበረታታት : ካጠፉ ከመሰለን ከነቀፌታው መፍትሄ ያልናቸውን አደባባይ ማስጣት:: ግድየላችሁም እነ ቢለኔ ስዩም እየቀመሩ አቢይ ዴስክ ያደርሳሉ:: በስድብና ዛቻ የምትተዳደሩትን ጡረተኞች አይመለከትም

ለ) እርዳታውን በደንብ ወርሃዊ አድርጎ ማሳለጥ:: እንኳንስ እኛ በቁጥር የታደልነው ከኤርትራውያንና ዋናዋ ሱማሌ ወገኖች ብዙ መማማር ይቻላል:: ባለፈው በአይዞን ከ 30ሺ በማይበልጡ ወገኖች ያ ሁሉ ሚሊዮን መሰብሰቡ ተስፋ ሰጪና የማንም ፈረንጅ ተመፅዋች ሆንን እንደማንቀር አመልካች ነው:: ታድያ የፅልመት ጆሮ ይደፈንና የሆነ ችግር ሰምቻለሁ በዚህ አካውንት – ታሪኩ ይቆየንና

ሐ) አገሪቱ የተደቀነባትን አደጋ ከልብ መረዳት:: በገንዘብ፣ ፀሎትና ዱአ በኑሮ ውድነት የሚሰቃየውን ወገን ማሰብ:: ብዙ መረዳዳት ይቻላል ወገኖች ከልብ ከተፈለገ::

 መ) በዖሮሚያ እየሆነ ያለው አንገት አስደፊ ክስተት መቆም አለበት:: የሚቆመው ደግሞ በጎሳ መደጋገፍ ወይም ጏደኝነት መተሳሰብ ላይ በተመሰረተ አመራር ሳይሆን በብቃትና ቆራጥነት ላይ መቆም ይገባዋል እላለሁ:: ለዚህም እጩ አለኝ:: አዳነች አቤቤ ዖሮሚያን ቢመሩ ለውጥ ይመጣል:: የጠቅላይ አቃቤን ቤት ነፍስ የዘራችበት አዳነች ዖሮሚያን ልክ ታገባለች ባይ ነኝ:: እባካችሁ ይህን አቢይ ጆሮ አድርሱልኝ:: ኦቦ ሺመልስ ምን መልካም ቢሆን ያለውን ችግር ለመጋፈጥ ምን እንደያዘውና ምን እንደተፈለገ ግራ  ገብቶኛል:: በንዲህ አይነት ጉዞ እንደምን ለውጥ ይመጣል? ሰላምስ ከሌለ ምንስ ትርፍ አለው ? ለምንስ ከፍ ያለ ትኩረት አይሰጥም? በቃ! እነ ኦቦ ቀጄላ መርዳሳና ኢብሳ ነገዎም ምነው ዝም አላችሁ? ተረዳዱ እንጅ:: እስከመቼ የንፁሃን ደም በኢትዮጵያ ምድር ይፈሳል? ይብቃን ::

ሠ) ማን አዳነችን ይተካ ለከንቲባነት? በኔ አተያይ አለችን በእሳት የተፈተነች ሌላዋ ቆፍጣና አንደበተ ሸጋና ስማርት ዳኛ ብርቱ ሚ’ደቅሣ!!! የፈረንሳይ ልጅ የሸገር ትክል አንበሲት:: ስራዋና ባህሪዋ ይመስክር:: የሷን ምክትል ወጣት ሌላዋን ሶሊያና (ባልሳሳት)ጀግና ቦታዋ ተክቶ ቡርቴን ቶሎ ማምጣት ወደ ማዘጋጃ:: ይህው ነው::

ረ) የአቢቹን ብረሰልስ ጉዞ አስመልክቶ በዚያ ያላችሁ አገር ወዳዶች ለአርብ የኢትዮጵያ ድጋፍ ስልፍ ያቀዳችሁ እንዲህ ነው ወገን ማለት::ስሜታችሁን ሳይሆን ኢትዮጵያን እያስባችሁ ይሁን:: በአንፃሩ ኢትዮጵያን ለማዋረድ ከነአሉላ ሰለሞን ቡራኬ ተቀብላችሁ ያውም ኢትዮጵያን የሚጎዳ የአሜሪካንን ህግ ለመደገፍ ላይ ታች የምትሉ እናት ኢትዮጵያን የከዳችሁ ከሀዲያን ያውም በ 11ኛው ሰአት ላይ ፈጣሪ ይፍረደው:: ለፖለቲካ  ዓላማ ልትሉን ነው? እነ አሉላስ ለጌቶቻቸው ነው ሌሎች ወገኖችን ማለቴ ነው::

በመጨረሻም!

በዚህ ልሰናበት:: ይህ የፈተና ጊዜ ያልፋል:: ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ ፈጣሪዋንና ህዝቧን ብቻ ተማምና እስካሁን ቆይታለች:: ወደፊትም እንዲሁ ትቀጥላለች:: እየሞትንም ትሻገራለች ይቺ ጉደኛ አገር:: ይብላኝ እናጠፋታለን እያላችሁ በቁም እየከሰማችሁ ላላችሁ የኢትዮጵያ ሁሉ ምቀኞች::ብዛታችሁ ላይጣል ቢሆንም አታሽንፉም:: ለምን? ሀቁ እናንተ ዘንድ አይደለምና! ይህው ነው!!!

ሰላም ሁኑ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በኦሮሚያ ክልል በጎሀ ፅዮን ከተማ የሚኖሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ዐማሮችና በኦነግ ሸኔ አማካኝነት መታረዳቸው ተነግሯል

Next Story

የሕግ የበላይነት ሳይረጋገጥ መነሳት የለበትም የሚል ተቃውሞ የገጠመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ

Go toTop