የኢህዴግ ቅርስ እና ዉርስ (ሌጋሲ) ገጠርን ማዕከል ያደረገ ልማት በሚል ከተሞችን በዘመቻ መልክ ከገጠር ወደ ከተማ በማስፈር እንዲሁም ነባር ነዋሪዉን በልማት ሽፋን ማሳደድ ድህነት በመቀነስ ስም ብዙኃን ድሀን ማባዛት በቀጥታ እና በግላጭ በጥዋቱ የልማት እና ዲሞክራሲ ( ከይሲ) መንገድ ተጀምሮ ዛሬም ቀጥሏል፡፡
ባለፉት ፴ (ሠላሳ) የመከራ እና የስቃይ ዘመናት በኢትዮጵያ ምድር የሞት ፣ የስደት ፣ የድህነት እና የባርነት ዕንክርዳድ ከተዘራበት አስከ አሁን የዘመናችን የመከራ ነዶ አስከሚታጨድበት ጥቂቶችን በማበልፀግ እና በማሳደግ ብዙሃኑን ማሳደድ እንዲቀጥል መሆኑ በኢትዮጵያ ድህነትን ማባዛት እንደ አንድ አገር የማሳደድ ስልት ሆኖ ይገኛል፡፡
በድፍን ኢትዮጵያ በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች ዜጎች በማንነታቸዉ ሲሳደዱ እና ሲወገዱ መኖራቸዉን ለሚያወቅ ሠባዊ ፍጡር ድህነት ማስፋፋት እና ድኃን( ሠርቶ አደር) ብዙሃን ኢትዮጵያዉያንን ማጥፋት ለመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓም ጀምሮ ጓዳዉን ማየት በቂ ነዉ ፡፡
በአገራችን የወደቁት ሠዉ እና ብሩ መሆኑን መረዳት ሆነ መስማት የማይፈልግ ቢኖር ሳይሰራ የሚኖር በአቋራጭ የሚበለፅግ ብቻ ነዉ ፡፡
ዜጎች በአገራቸዉ ባይተዋርነት እና ባርነት እየተሰማቸዉ ፤ ሠርተዉ ያፈሩትን የማያዙበት ምድር ላይ ነፃነት የሌለዉ ህዝብ ዕድገት መጠበቅ ከድንቁርና በላይ ሊገለጥ አይችልም፡፡
የኑሮ ዉድነት ፣ መፈናቀል፣ በደል ፣ ሞት ፣ ድህነት……በተፈራረቀብን ቁጥር እንደ ሠዉ ከሌላዉ ወይም ከጠላት መፍትሄ መጠበቅ መቸ እንደሚቆም ባይታወቅም በአድር ባይነት መኖር ሊቆም ይገባል፡፡
የሠራ በማይከበርበት የዜጎች ነፃነት በማይረጋገጥባት አገር እንዲሁ አንዱ የሠራዉን ሌላዉ ዘርቶ፣ አርሞ ፣ሰብስቦ እና ወቅቶ የሰበሰበዉን እየቀማ ፤አገር እና ህዝብ እያዋረዱ እና እየገደሉ አገር እና ህዝብ ዕድገት መገመት በራሱ ኃጢያት ነዉ ፡፡
ገና በዘመነ ኢህአዴግ የክህደት ዋዜማ ላይ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ህልዉና ለማጥፋት ሲጀመር ድህነትን በመቀነስ ሽፋን ድሀዉን ብዙኃን ህዝብ በማሳደድ እንደነበር የምንገኝበት የዛሬዉ ድህነት ፣ ዉርደት እና ሞት ማሳያወች የትናንት ታረካችን ፤ የዛሬ መስታዉት እና የነገ ስጋት ምልክቶች ናቸዉ ፡፡
የዓለም ሆነ የአገራችን ጨዉ ብዙኃን ኢትዮጵያዊ እና ድኃዉ ነበር ፤ ነዉ ፡፡
ዛሬ አገሪቷን ከዉስብስብ የጠላት መንጋጋ የታደጋት ብዙሃኑ እና ድኃዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የህዝብ ልጆች ብቻ ናቸዉ፡፡
የጨለማዉ ጊዚ አልፎ ብርኃን ሲገለጥ ከአገር እና ህዝብ በፊት ሞት የሚሉ መሪዎች እንዳልበቀሉባት ሁሉ መሸሻዉን ሲያማትር የነበሩ ከኃዲዎች ዛሬ ስለ ድህነት የሚያሩት በብዙኃኑ ኢትዮጵያ ድኃ ህዝብ ቁስል የሚቀልዱ ክኃዲዎች ናቸዉ፡፡
በመላዉ ኢትዮጵያ ምድር የዘመናት የደም እና ህይወት ቤዛ ሲከፈል ፤ ዜጎች ሰርተዉ እንዳይኖሩ ሲሳደዱ ድህነት ሊቀንስ የሚችለዉ እንዴት ይሆናል ፡፡
ዕዉነተኛ ዕድገት እና ነፃነት ባልተረጋገጠበት ስለ ድህነት ቅነሳ እና ህዝባዊ ዕኩልነት የሞኝ ዘፈን መደጋገም ባይኖር ለሁሉም ይበጃል ፡፡
“ድህነት በዕድገት የሚተካዉ የምድራችንን ጨዉ እና ብርኃን የሆነዉን ህዝብ ነፃነት እና ስራ በመስጠት እንጂ በማሳደድ ወይም በማጥፋት አይደለም፡፡
ማላጂ
አንድነት ኃይል ነዉ