“ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች በይቅርታ እየተፈቱ ነው” -የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

January 5, 2022
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ከሽብር ቡድኖች ጋር መስራታቸው አገርን እንደ መካድ የሚቆጠር መሆኑን አምነውና በድርጊታቸው ተጸጸተው ይቅርታ በመጠየቃቸው ከእስር እየተፈቱ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሰታወቀ፡፡
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ ከተለያዩ የሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የተጠረጠሩ ሰዎችን የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወሳል፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በጸጥታ አካላት ተጠርጥረው ከታሰሩት ውስጥ የጥፋት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆነና መንግስት ከጥፋታቸው ተገቢውን ትምህርት ወስደዋል መንግስት ጉዳዮን በሆደ ሰፊነት አይቶ የለያቸው በርካታ ሰዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ አድርጓል ብለዋል፡፡
የቀሩትም እንደ ሁኔታው የጥፋት ደረጃቸው እየታየ ቀጠይ የሚለቀቁ እንደሚሆን ገልጸው፤ቁልፍ የችግሩ ተዋንያን የሆኑት ደግሞ ጉዳያቸው ተጣርቶ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
የመንግስት ዓላማ አስተማማኝ፣ ዘላቂ ሠላም አስፍኖ የህግ የበላይነት እንዲረጋጋጥ ማስቻል ነው ያሉት ዶክተር ለገሠ፤ ይህንን የሚገዳዳር ማናቸውን እንቅስቃሴዎች ከህግ ተጠያቂነት አያመልጥም ብለዋል፡፡
ሕዝቡም እስካሁን የሚያደርገውን ድጋፉን እንደ ወትሮው ሁሉ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡
በጌትነት ምህረቴ (ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ አሸባሪውን ትሕነግ በአደባባይ ወጥቶ ሊቃወመው ይገባል አለ

Next Story

ጀፍሪ ፌልትማን እንደ ኸርማን ኮኸን – መስፍን አረጋ

Go toTop