የአሸባሪው ህወሓት ሀይል በኮምቦልቻ ከ100 በላይ የከተማዋን ወጣቶች መጨፍጨፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ

November 1, 2021
የአሸባሪው ሕወሀት ሀይል በኮምቦልቻ ከተማ ሰርጎ በመግባት ዛሬ ሌሊቱን ከ100 በላይ የከተማዋን ወጣቶችን አሰልፎ መጨፍጨፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የሽብር ሀይሉ ሰርጎ በገባበት በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የግል እና የመንግስት ሀብቶችን እየዘረፈ እና እያወደመ ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል።
በቦርከና ዳዋ ጨፌ አካባቢዎች ሕወሀት እየመጣ ነው በሚል የአሸባሪው ሸኔ ሀይል መንገድ የመዝጋት እና ሌሎች አፍራሽ ድርጊቶችን ለመፈፀም ቢሞክርም በአካባቢው ወጣቶችና በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አላማው ከሽፎበታል ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ በክህደት የተፈጠሩበትን የውጊያ መዛነፎች እንደገና በማስተካከል አሁንም ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛልም ተብሏል።
“መንግስት ተዳክሟል፣ ሕወሀት አሸንፎ እየመጣ ነው” በሚል ደሴ ላይ እንደተፈፀመው ሁሉ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ጭፈራ የገቡ ሀይሎች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
እንድ ኢቢሲ ዘገባ፤ ይህንን አስመልክቶ መንግስት እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ።
ኢዜአ

መከላከያ ውስጥ ያሉ አማራዎች በክልሉ ወዳሉት ግንባር የሚንቀሳቀሰውን ሀይል እንዲመሩት ተለይተው ቢመጡ መልካም ነው

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“ለአማራ ድል፣ ብአዴን መወገድ አለበት!!!! – አቻምየለህ ታምሩ

Next Story

መከላከያ ውስጥ ያሉ አማራዎች በክልሉ ወዳሉት ግንባር የሚንቀሳቀሰውን ሀይል እንዲመሩት ተለይተው ቢመጡ መልካም ነው

Go toTop