አንጋፋው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ታደሰን ተረባርበን ለሀገሩ እናብቃው!!

October 11, 2021

244748406 4928686723825308 7595380117449971494 nአንጋፋው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ታደሰ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ከመንገድ መዋሉን በሐዘን ሰምተናል።ነገሩ ሰንበትበት ብሎ ብዙዎች በዲሲ ያሉ የሙያ አጋሮቹ እና በቅርብ ያሉ ያቅማቸውን ማድረጋቸውን ውስጥ ውስጡን ስንሰማ ቆይተናል። አንዳንዴ በሚመጡብን ፈተናዎች ራሳችንን የማንረዳበት ወይ ከገባንበት አጣብቂኝ የማንወጣበት ሁኔታ ይፈጠራል።

በዚህ ሳቢያ የጥቂቶች ጥረት አልተሳካ ይሆናል ፍጹም ተስፋ ግን እንደ ወገን ለዚህ ታላቅ የጥበብ ሰው በቃን የራሱ ጉዳይ የምንለው አይደለም። እባካችሁ ብዙዎችን አስተባብራችሁ ቢያንስ አገሩ ገብቶ ነገሮች እንዲለወጡ ስትደክሙ የነበራችሁ የቀረውን ወገኑን እገዛ ጠይቁና ይህ ትልቅ የአገር እንቁ ደግሞ ይነሳ። በዚህ ጥረት ለምትተጉ ከወዲሁ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።የቴዎድሮስ ነገርን እንዲሁ ከንፈር መጠን የምንተወው እንዳይሆን ።ሰው ካለፈ በሁዋላ ብዙ ብንል ዋጋ የለውም።
ይሄ ሰው የአገር ሀብት ነው።በዚህ አጋጣሚ የቤተሰቦቹን ፎቶ አትለጥፉ።ጎ ፈንድ ሚ ቤተሰቡ እና ሲረዱት የነበሩ ሰዎች አውቀውና እነሱ የሚያውቁት በይፋ የሚገለጽ ካልሆነ ሞጭላፎች ከሚከፍቱት እንጠበቅ። በይፋ የተከፈተ ሲኖር እናሳውቃለን።አመሰግናለሁ።
© Habtamu Assefa

Leave a Reply

Your email address will not be published.

244754765 1072233326848188 5872322672428424514 n
Previous Story

ግልጽ ደብዳቤ ለወይዘሮ ገነት ዘውዴ (ፈቃደ ሸዋቀና)

245292007 10228212382474423 4007513069427497292 n
Next Story

አጠያያቂው ሹመት – አበበ ገላው

Go toTop