የጀነራል አስራት ጉድይ አሳሳቢነት! ትኩረት መሰጠት ያለበት ነው

August 27, 2021

4533

1ኛ የመጀመሪያውን ኦፕሬሽን አቋርጦ ከገዳይ ቡድኑ ጋር በሻጥር ድርድር ተቀመጠ ::
2ኛ በድርድር ወቅት ገዳዮቹ መሳሪያ ሳያወርዱ ሰላማዊ ታጋይ በሚል ስም ወደ ከተማ ገብተው ስልጠና ሰጥቶ የልብ ልብ እንዲሰማቸው አደረገ። ከተማውንም በተኩስ ይንጡት ነበር ።
3ኛ በእሱ ሰብሳቢነት ገዳይ ቡድኑ ከእነትጥቁ ከወረዳ እስከ ክልል ስልጣን እንዲሰጥ አድርጓል።
4ኛ ህዝቡ ታጥቆ እራሱን ለማስከበር ሲፈልግ መከልከልና ትጥቅ ማስወረድ ከእዚያም አልፎ መከላከያ እርምጃ እንዳይወስድ በመከልከሉ በርካታ የመንግስት የፀጥታ አካላት መስዋዕት ሁነዋል። ለምሳሌ ትናንት በርካታ የመከላከያ አባላት ተጎድተዋል።
5ኛ ህዝብን በገፍ ሲጨፈጭፉ ለኖሩ ሽፍቶች ኬላ ዘርግታችሁ ተቆጣጠሩ በሚል ከቻግኒ ግልገል በለስ መስመር አስረክቦ ንፁሃን እንዲጨፈጨፉና እንዲታገቱ ብሎም እንዲዘረፉ ህጋዊ እውቅና ሰጧል ።
6ኛ እስከ ሃምሌ ወር ድረስ በነፍስ ወከፍ ለአንድ ገዳይ 1000 ብር ደሞዝ እንዲከፈል አድርጓል።
7ኛ በድርድር ወቅት ቢያንስ ከመከላከያ የተዘረፉት መሳሪያ ማስመለስ ሲገባው አላደረገም።
8ኛ ከመከላከያው ባሻገር የቀጠናው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ በመሆኑ ከየክልሉ ለህልውና ዘመቻው የመጡ የፀጥታ ሃይሎች እርምጃ እንዳይወስዱ መከልከል።
9ኛ ጀነራሉ በክልሉ አመራርና በገዳይ ቡድኑ በጥቅም በመጠለፉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለህዝብ የሚታገሉ ከቀበሌ እስከ እስከ ዞን ሰላም ፈላጊ አመራሮችን አሳልፎ ሰጧል።
10ኛ ቡለን በኩጅ የሰው ልጅ እንደ አፈር በግሬደር ከተጠረገ በኋላ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ማህበረሰቡ ታጥቆ ራሱን ይጠብቅ የሚል መመሪያ በማስተላለፋቸው ይሄንን ተንተርሶ የገዳይ ቡድኑ አባላት በብዛት ስልጠናውን በሶስት ዙር ሲካፈሉ እሱ እዛው ግልገል ሆቴሉ ውስጥ ነበር ።
11ኛ ሙስናን በተመለከተ … እቀጥላለሁ
ፎቶው
የሀገር መከላከያ አባሉ ወጣት ጀነራል አስራት ራሳቸውን እንዳይከላከሉ እና ገዳይ ቡድኑን እንዳያጠቁ በመከልከሉ ጉዳት ደርሶበት ወጣቶች ተሸክመውት ወደ ህክምና ወስደውታል።
ተስፋየ ወልደሰላሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ከተማዋ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

mekonen 2
Next Story

ከደሊላዊ  ወጥመድ  እንጠንቀቅ !! – መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

Go toTop