የአንድነት ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበርና የመድረክ ከፍተኛ አመራር አባል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከሕወሐት ልሳን ራድዮ ጣቢያ ራዲዮ ፋና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “በሰላማዊ ትግል ተስፋ የቆረጡና በሌሎች መንገዶች ለውጥ እናመጣለን የሚሉና የሰላማዊ ትግል የማያምኑ ዲያስፖራዎች በኛ ላይ ፕሮፓጋንዳ እያደረጉ ነው። እንደውም እናንተ ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል: እንደዚህ የሚሉንን ዲያስፖራዎች ከፈለጋችሁ ገንዘባችሁን አትስጡን ብለናል” ሲሉ ተናገሩ።
1 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ በፈጀው ቃለ ምልልሳቸው ላይ ክራድዮ ፋናው ጋዜጠኛ ጋር ቃል የተመላለሱት ዶ/ር ነጋሶ ምላሻቸውና ጥያቄው ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤን ይሰጣል ብለን ስላሰብን ከታች አቅርበነዋል።