ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ድንበሮቿን ለሰዎች ዝውውር ዝግ አደረገች

March 23, 2020

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የአገሪቱ ሁሉም ድንበሮች ለሰዎች ዝውውር ዝግ መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከልም መንግሥት አምስት ቢሊዮን ብር መበጀቱንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

በአውሮፕላን ከውጭ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ለ14 ቀናት ተለይተው እንዲቆዩ የሚያስገድደው ውሳኔም ከዛሬ ጀምሮ በመተግበር ላይ ነው።

ሁሉም መንገደኞች በስካይ ላይት እና በግዮን ሆቴሎች ለ14 ቀናት በራሳቸው ወጪ ተለይተው ይቆያሉ ተብሏል።

የራሳቸውን ወጪ ለመሸፈን አቅም ለሌላቸው ኢትዮጵያውያንም መንግሥት ሙሉ ወጪያቸውን እንደሚሸፍን የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል።

በእዮብ ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሕብር ሬዲዮ ፕሮግራም – ድብቁ የእነ ዶ/ር አብይ ጦርነት በምዕራብ ኦሮሚያ

Next Story

የይቅርታ ፖሊቲካና የፍትሕ ነጻነት ወቅታዊ ችግራችን – ቁጥር 2 – ባይሳ ዋቅ-ወያ

Go toTop