ጉዳያችን
የፖለቲካ፣የሰላም እና ደህንነት (Peace and Security) ምሑሩ ዶ/ር ኃይለየሱስ ሙሉቀን ፕሬዝዳንት፣የምጣኔ ሃብት ምሁሩን ዶ/ር ሰይፈስላሴ አያሌውን ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ጉባኤው መርጧል።
ዛሬ ዕሁድ የካቲት 29፣2012 ዓም በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማዕከል የመስራች ስብሰባውን ያካሄደው አዲሱ እናት ፓርቲ የፓርቲውን ሎጎ በጠቅላላ ጉባኤው ያፀደቀ ሲሆን፣ የስራ አስፈፃሚ አባላትን፣የላዕላይ ምክር ቤት አባላትን፣ የሂሳብ ክዋኔ ኦዲት ኃላፊዎች እና የሕግ ስርዓት ጉዳዮች ኃላፊዎችን መርጧል።የእናት ፓርቲ አደራጆች በዛሬው መስራች ጉባኤ ላይ የፓርቲው መመስረት ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዱ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግሮች በሶስት ጉዳዮች ተተብትበው መያዛቸውን እና ለእዚህም በቂ መፍትሄ ፖለቲካው መስጠት ያለመቻሉን በዋናነት ያስቀምጣሉ። እነርሱም –
2. ማኅበራዊ ችግሮች፣
3. ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣
በእዚሁ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ እና የመስራች ጠቅላላ ጉባኤው አባላት በንቃት እንደተሳተፉበት በተነገረው ስብሰባ ላይ አሁን ላሉት የፓርቲው መዋቅሮች ከቀረቡለት ዕጩዎች ክዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመስራች ጉባኤው ተሳታፊዎች መምረጣቸውን ጉዳያችን ከአዲስ አበባ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።በእዚህም መሰረት የፅህፈት ቤት አባላት –
1) የፓርቲው ፕሬዝዳንት = ዶ/ር ኃይለየሱስ ሙሉቀን
2) የፓርቲው ም/ፕሬዝዳንት = ዶ/ር ሰይፈ ስላሴ አያሌው እና
3) የፓቲው ጠቅላይ ፀሐፊ = አቶ ጌትነት ወርቁ የተመረጡ ሲሆን እንደ ቅደም ተከተላቸው በደረጃ ተለያይቶ ነገር ግን ሁሉም ከ400 በላይ ድምፅ አግኝተዋል።
በእዚህም መሰረት የፕሬዝዳንቱ፣ም/ፕሬዝዳንቱ እና ፀሐፊው የትምህርት እና የስራ ልምድ ሁኔታ በአጭሩ እንደሚከተለው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
1)ፕሬዚዳንት፡- ኃይለኢየሱስ ሙሉቀን (ፒኤችዲ)
3) ጠቅላይ ጸሐፊ፡- አቶ ጌትነት ወርቁ
የሕግ ስርዓት ጉዳዮች ሆነው የተመረጡ –
1) አቶ ሰለሞን (በአንደኝነት) እና
2) አቶ ለሜሳ (በሁለተኛነት)
ሂሳብ ክዋኔ ኦዲት
1) ኢንጅነር ዓቢይ (በአንደኝነት)
2) አቶ ተመስገን (በሁለተኛነት)
ለሥራ አስፈፃሚ አባልነት የሚከተሉት ተመርጠዋል።
1) አቶ ፍሬው፣
2) አቶ ኪሮስ፣
3) አቶ አበበ፣
4) አቶ ማቲያስ፣
5) መምህር ሳሙኤል፣
6) ወ/ት ዓለም፣
7) አቶ ታከለ፣
8) አቶ ዓይነሰው፣
9) አቶ ሰለሞን፣
ለፓርቲው የላዕላይ ምክር ቤት የሚከተሉት ተመርጠዋል። እነርሱም –
1) ዶ/ር መሰሉ፣
2) ወ/ት አስማሩ፣
3) ዶ/ር ታመነ፣
4) ዶ/ር ናሁ ሰናይ፣
5) ዶ/ር ወንድወሰን፣
6) አቶ መኩርያ፣
7) ኢንጅነር ማቲያስ፣
8) አቶ ጌታሰው፣
9) አቶ ብርሃኑ፣
10) ወ/ት ጉዳዩ፣
11) አቶ ሮቤል፣
12) አቶ ካሳሁን፣
13) አቶ አሰፋ፣
14) ወ/ት ናሆሚ፣
15) ኢንጅነር ደሳለኝ፣
16) አቶ ተመስገን፣
17) ወ/ሮ ሜሮን ሆነው ተመርጠዋል።
እናት ፓርቲ በዛሬው የመስራች ስብሰባ ላይ በዋናነት የመጠፋፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ዳግም እንዳያንሰራራ እና ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የኖረው ህዝብን ከህዝብ የሚከፋፋል ”የእኛ እና የእነርሱ” የሚሉት የፖለቲካ አካሄዶች እንዲያበቃ እንደሚሰራ ተወስቷል።
በመጨረሻም ተመራጮች በሙሉ በታማኝነት እና በትጋት እንደሚያገለግሉ እና የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል። (ከስር ቪድዮውን ይመልከቱ)