ከአንድ ወር በፊት በሌብነት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ የታሰሩ የቀድሞው የሕወሓት ስርዓት ባለስልጣናት ወሬ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር:: ዘ-ሐበሻ የታሳሪዎቹን የፍርድ ቤት ውሎ በተቻለ መጠን እየተከታተለ እየዘገበ መረጃ ለሕዝብ በማድረስ ላይ ይገኛል:: አቃቤ ህግ በታሳሪዎች ላይ አዳዲስ ማስረጃዎችን እያቀረበ እያስደመመን ሲሆን አሁን ያቀረበው የመርዝ ጉዳይ ግን በ እጅጉ አስገራሚም አስደንጋጭም ነው:: “በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ውስጥ አደገኛ መርዝ መገኘቱን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ” በሚል ሪፖርተር ያቀረበውን ሰፊ ዘገባ ለዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች በሚስማማ መልኩ ይዘናል – ይከታተሉን::
https://www.youtube.com/watch?v=QyXK__UyEkA&feature=youtu.be