ፖሊስ አላሰርኩትም › ያለውን አስራት አብርሃምን ፍርድ ቤት አቀረበ

May 26, 2014

ጋዜጠኛ ዳዊት ስሎሞን

አስራት አብርሃም

የመድረክን ሰላማዊ ሰልፍ በመቀስቀስ ላይ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣብያ በመታሰራቸው ትናንት ከአንድ የአረና ፓርቲ አመራር ጋር ለጥየቃ ያመራው ፖለቲከኛና ደራሲ አስራት አብርሃም በጣብያው መታሰሩን ቤተሰቦቹና የአንድነት አመራሮች ሊጠይቁት እንደሄዱ የከተማይቱ ፖሊስ ‹‹አስራት አብርሃም›. የሚባል ሰው አለማሰሩን በመግለጽ አስራትን መሰወሩን ት መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት አስራትን አላሰርኩም ያለው ፖሊስ ፖለቲከኛውን ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡በፍርድ ቤት የቀረበው የአንድነት ፓርቲ አባል ‹‹ምሽቱን በፖሊሶች መደብደቡንና ፖሊሶቹም ለሌት ላይ ህክምና እንዲያገኝ ክሊኒክ እንደወሰዱት አጋልጧል፡፡
አንድ ፖሊስ ‹‹ሰድቦኛል››በማለት ክስ የመሰረተበትን አስራትን በ500 ብር ዋስ እንዲፈታ ክብርት ዳኛዋ ቢወስኑም ፖሊስ አልፈታም ብሏል፡፡

Previous Story

የሐውዜን አስተዳዳሪዎች የዓረና አባላትን ዉጡልን እያሉ ደበደቡ

Next Story

ወያኔ በ«ዐማራ ክልል» ለኤች. አይ. ቪ. ኤድስ በሽታ መከላከያ ብሎየሚያሠራጨው መድኃኒት በሽታውን የማይከላከል መሆኑ ተገለጠ

Go toTop