ዐውደ ዓመት በየዓመቱ የሚከሰት ማለት ነው ።ገ…ና የሚመጣ ። ሁሉም ዓመት በዓሎች ገ…ና በየዓመቱ የሚከሰቱ ናቸው ። በተለምዶ አውደ ዓመት ይባላሉ ። ያው ዞረ የሚከሰቱ ፣ ዑደታቸው የማያቋርጥ ገ…ና ሥለሆኑ ። …
አውደ ዓመቶቻችን ብዙ ናቸው ።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ፣ ገና ( የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ቀን ) ፣ ጥምቀት ( መጥመቁ ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያጠምቀው የኢየሱስ ዓምላክነት በግልፅ ከሰማይ የተመሠከረበት ቀን ።) ፣ ሥቅለት ( ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል ለመንሣት በዕለተ ዓርብ የተሰቀለበት ቀን ) ፋሲካ ( የክርስቶስ ኢየሱስ ትንሣኤ ፤ ሞትን ድል አድርጎ ከሞት የተነሳበት ቀን )
በሙስሊም እምነትም አውደ ፣ ዓመቶች አሉ ። ሥራ የማይሰራባቸው የፆም ፣ የልደትና ፣ የፈጣሪን ቸርነት ማሣያ በዓለት ፣ በየዓመቱ ይከበራሉ ። ግን ለምንድነው በየዓመቱ ” የዓመት ባዓሎቹ ” ብርቅና አዲስ የሚሆኑብን ? ለምሣሌ ገና ፣ ታህሳስ 29 (በየአራት ዓመቱ በታህሳስ 28 ይከበራል ። ) ላለፉት 2015 ( በእኛ አቆጣጠር ) ዓመታት ደጋግሞ ገና መጥቷል ። ይምጣ እንጂ ዛሬ የምናከብረው ” ገና ” ካለፈው “ ገና “ ፈፅሞ አይመሣሠልም ። አዲስ ቀን ነው ። በየዓመቱ ።
ገና በየዓመቱ ፣ አዲስ ቀን ነው ማለት ምን ማለት ነወ ?
አዲስ ቀን ትላንት ያልሆነ ያልተኖረ ፣ ያልኖርነው ቀን ማለት ነው ። በሩቅ የሚታሰበን በጊዜ መፈራረቅ የደረሰ አዲስ ቀን ሆኖም ከዕምነታችን እና ከባህላዊ እሴታችን ጋር በብርቱ የተቆራኘ ቀን ማለት ነው ። ለዚህ ለሰርክ አዳስ አውደ አመት ፤ በታሪክ ለየት ያለ ቀን ፣ ” ሽር ጉድ ” ብንልነት ፣ አይበዛበትም ። ካለን ፣ ኪሳችን ካበጠ ምን ችግር አለው ? ኪሳችንን በሚገባው መጠን እናስተነፍሰዋለን ። ከሌለንም ተለቅተንም ሆነ ተበድረን በደመቀ ሁኔታ እናከብረዋለን ።
ገና ( የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ። ) ሥሙ ፣ ኃይማኖታዊ ትርጉሙ ከቶም ሳይለወጥ በየዓመቱ ያው እና አንድ ሆኖ ሣለ ፤ በየዓመቱ እንደ አዲስ ማክበራችን ግን ሁሌም ያሥገርመኛል ።
አውቃለሁ ። ሰው ነገን ናፋቂ ነው ። ነገ ለሰው ሁሌም አዲስ ነው ። ሰው ትላንትን ቶሎ የሚረሳ ፍጡር ነው ። አብሶ መጥፎ መጥፎውን ለማስታወስ አይፈልግም ። ነገ የተሻለ እንዲገጥመው ግን አጥብቆ ይሻል ። ሰው ተሰፋው በነገ ላይ የተመሠረተ ፍጡር ነው ። እናም ሰው ነገን በጉጉት እና በናፍቆት ይጠባበቃል ። ነገ ያሥደስት ፣ ወይ ያስከፋ ግን አያቅም ። ነገ ሁልጊዜ ነገ ነው ። መቋጫ የለውም ። የሞተ ብቻ ነው ነገ የሚቋጭለት ። ሰው ከነገ ናፍቆት የሚገላገለው ሲሞት ብቻ ነው እናም ፣ ሰው ህይወቱ እሥካለች ጊዜ ድረስ ነገን የሚጠብቅ አሳዛኝ ፍጡር ነው ።
ለሰው ፣ ያልኖራቸው ፣ ከፊት ለፊቱ ያሉ የልነጉ ቀናቶች ሁሉ ነገ ይባላሉ ። ሰው ፣ ነገ መሽቶ _ እንደነጋ የሚያያት ፀሐይ ፣ ያቺ ፤ የአህያ ሆድ የምትመስለው ፣ ሁሌም አዲስ ናት ። ፀሐይቱ ሥትጠልቅም ” በሰላም ያዋልከኝ በሰላም አሳድረኝ ። ” ብሎ የሚፀልየው አዲሷን ነገ ለማየት በብርቱ ሥለሚሻ ነው ። እንግዲህ ከዚህ ነገን ያለማወቅ እና ” ዛሬን ኖሬ ለነገ እበቃ ይሆንን ? ” በሚል ጥርጣሬ ሰው ልጅ ሥለሚኖር ፣ ፊቱ ያሉትን ፣ ያልኖራቸውን ቀናት በእጅጉ ይናፍቃል ።
ዛሬ በህይወት ያለ ሰው ፣ የዛሬውን የጌታችንን የመድኃኒታችንን የ 2015 ዓ/ም የልደት ቀን እያከበረ ፤ ለ2016 ዓ/ም በሠላምና በጤና እንዲያደርሰው ይለምናል ። “ዓመት ከዓመት ያድርሰን ። እንዲሁ እንዳለን አይለየን ። ” እያለ ይፀልያል ። እስከ መቃብር ። በተሰለፈው የሞት ሰልፍ መሠረት እየተጠራ ሥጋው ወደ አፈሩ እሥኪመለሠስ ድረሥ …
መልካም የመዳኃኒዓለም የልደት ቀን ይሁንላችሁ ።