በሸዋ ሮቢት ከተማ ጎማ እየተቃጠለ ለሰአታት መንገድ ተዘግቶ ዋለ

February 20, 2019

የዛሬው መንገድ መዝጋትና ጎማ ማቃጠል ደግሞ ለየት ያለ ነበር፡፡ ከስፍራው እንደደረሰን መረጃ በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋ ሮቢት ከተማ አንዲት ሴት በጩቤ ተወግታ ስትሞት አብሯት የነበረው ህፃን ልጇ ደግሞ በመታፈን ህይወቷ አልፎ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች በተገደሉበት ቤት ውስጥ ታፍኖ የነበረ ሌላ ህጻን ልጅ ወደ ህክምና ተወስዶ በተደረገለት እገዛ በጥሩ ጤንነት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

https://www.youtube.com/watch?v=SvwytfrDZTg&t=73s

ይህን ድርጊት በመፈፀመም የተጠረጠረው ግለሰብ አብሯት ይኖር የነበረ ሲሆን ድርጊቱ ከተፈጠረ በኋላ ጠፍቶ ቆይቷል፡፡ በዛሬው እለት ግን ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ እንደተሰማ በርካታ የሸዋ ሮቢት ነዋሪ ግልብጥ ብሎ አደባባይ እንደወጣ ሰምተናል፡፡ የተወሰኑ የከተማው ነዋሪዎች፣ ‘ግለሰቡን ፓሊስ አሳልፎ ይስጠን እና እንግደለው፣ ወይም በመንጋ እንፍረድበት’ በማለታቸው ከፓሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተዋል። ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን ጥይትም በብዛት ሲተኮስ የነበረ ሲሆን ይህን ተከትሎም ነዋሪዎቹ ጎማ አቃጥለው ለሰአታት መንገድ መዝጋታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

Previous Story

ቴዎድሮስ ካሳሁንየአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ትርዒት በዲቪዲ ተዘጋጅቶ የፊታችን ቅዳሜ ለሕዝብ እንደሚደርስ ታወቀ

Next Story

በለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆነ አቶ ለማ መገርሳን ማነጋገር አትችሉም ተባሉ

Go toTop