(ዘ–ሐበሻ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ዛሬ የልደት በዓላቸውን እያከበሩ ነው::
ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም‘ ከ1966 እስከ 1983 ዓ.ም. ለ17 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ ነበሩ። ወደ ስልጣን የወጡት በደርግ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በመገልበጥ ሲሆን ተቃናቃኝቻቸው የነበሩትን የቅርብ ጓደኞቻቸውንና የደርጉን መሥራቾች ባማስወገድ ብቸኛ የአብዮቱ መሪ ሆነው ቆይተዋል::
በአሁኑ ወቅት በዙምባቤዌ በጥገኝነት ኑሯቸውን እየገፉ ያሉት ኮለኔሉ ከሮበርት ሙጋቤ የስልጣን መውረድ ጋር ተያይዞ ባለፈው ዓመት ስማቸው በየሚዲያው ሲነሳ ነበር:: በቅርቡም አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዓብይ አህመድም “ከፈለገ መንግስቱ ኃይለማርያምም ወደ ሃገሩ መመለስ ይችላል” ማለታቸው ከተዘገበ በኋላ እንዲሁ መነጋገሪያ ሆነው ቆይተዋል::
የኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ልጅ ዶ/ር ትእግስት መንግስቱ በፌስቡክ ገጿ ለአባቷ መልካም ልደት ተመኝታ “ከብዙ አደጋ ጠብቆ ለዚህ ቀን ያበቃህ እግዚአብሄር ይተመሰገነ ይሁን :: እግዚአብሄር ይባርክህ:: እግዚአብሄር ኢትዮዽያን ይባርክ” ስትል መልካም ምኞቷን ገልጻለች::