Español

The title is "Le Bon Usage".

ዓረና-መድረክ በመቀሌ የጠራው ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በህወሓት መሪዎች ታገደ

February 27, 2016

ከአምዶም ገብረሥላሴ
ዓረና_መድረክ በኣራት ኣንገብጋቢና ኣስቸኳይ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ክልላዊና ሃገራዊ ርእሰ ጉዳዮች ኣስመልክቶ ለ20 / 06 / 2008 ዓ/ም በመቐለ ከተማ የጠራው ሰለማዊ የተቓውሞ ሰልፍ የህወሓት መሪዎች ኣግደውታል።
ሰልፉ ከኤርትራ በመጡ ታጣቂዎች ታግተው ስለተወሰዱ ወጣቶች መታገት፤ የህግ ልእልና እንዲከበር፤ በረሃብ እያለቁ ስላሉ ወገኖቻችንና የኦሮምያ ክልል ስለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ( ‪#‎Oromo_protest‬ ) ና እየተወሰደ ያለው ግድያና እስር ቆሞ መንግስት ከሚመለከታቸው እንደ መድረክ የመሰሉ ፖለቲካዊ ድርጅቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ድርድር እንዲጀምር የሚጠይቁ ኣጀንዳዎች ናቸው።
ህወሓቶች ለእገዳው የሰጡት ምክንያት፦
ሀ) “ወቅቱ ያልተረጋጋና ለግርግር የተመቸ ስለሆነ በኣሁኑ ስዓት የተቃውሞ ሰልፍ መፍቀድ ለሰላም ሲባል ኣይመረጥም።”
ለ) “በኣሁኑ ሰዓት መንግስት የግምገማ መድረኮች(ፅሬት) እያካሄደ ስለሆነ የፕሮግራም መደራረብ ያጋጥማል” የሚል መልስ ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ሓላፊ ኣቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃ ትናንት ወደ ፅህፈት ቤታቸው ጠርተው ገልፀውልኛል።
ኣቶ ዘመንፈስቅዱስ የእገዳው ውሳኔ በፅሁፍ ስጡን ብየ ስጠይቃቸው ” እኔ በቃል እንዳሳውቅ ነው ከኣለቆቼ የተነገረኝ ስለዚ በፅሑፍ ኣልሰጥህም። የሆነ እንቅስቃሴ ብታደርጉ ሰለማዊ ሰልፍ ሳይሆን ብጥብጥና ሁከት በከተማው ለማስነሳት እንደተሞከረ ይቆጠራል። ለዚህ የፀጥታ ሃይሎች ኣስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ታዝዘዋል” የሚል ዛቻ ኣዘል መልእክት ነግረውኛል።
ይሄ ነገር በፅሑፍ ካላሳወቃቹን ሰለማዊ ሰልፉ እናካሂዳለን። ብየ ከፅህፈት ቤቱ ወጥቼ ስሄድ ኣቶ ወላይ (ወላይ ጎት) የመቐለ ዞን የድህንነትና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ከህንፃው በር ጠብቆ “ምን ምላሽ ተሰጣቹ? ” ብሎ ጠየቀኝ።
እኔም ኣቶ ዘመንፈስቅዱስ “ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፉ ታግደዋል” ብሎ ብቃል ብቻ እንደነገረኝ ገለፅኩለት።
ኣቶ ወልዳይም “እና ምን ኣሰባቹ?” ኣለኝ።
እኔም ሰለማዊ ሰልፉ ለማካሄድ ወስነናል። በህጉ መሰረት ኣስተዳደሩ ደብዳቤው ከደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ ምላሽ መስጠት ነበረበት ይሁን እንጂ ኣላደረገውም።
ኣሁንም ውሳኔው በፅሑፍ ኣድርገው ስንለው “በቃል ብቻ እንድነግራቹ ነው ከኣለቆቼ የታዘዝኩት ብሎናል።
ስለዚ እኛ በኣንድ ኣለቃ የተሰጠ የቃል መመርያ ሳይሆን ህገ መንግስቱ በሰጠን መብት መሰረት ሰልፉ እናካሂዳለን። ለሰልፉ ተሳታፊዎች የጥሪ ቅስቀሳው ለመጀመር መኪና፣ ጀነሬተርና ምንታርቦ ድምፅ ማጉልያ ተከራይተናል። ስለዚ በእቅዱ መሰረት ሰልፉ ይካሄዳል ኣልኩት።
ኣቶ ወላይ ” በቃል ይሁን በፅሑፍ ሰለሚዊ ሰልፉ ኣታካሂዱም ከተባላቹ ኣታካሂዱም ነው። ማንኛውም ሰው ለሰልፉ ቅስቀሳ ኣካሂዳለው፣ ሰልፍ እወጣለው ካለ ኣስፈላጊ እርምጃ እንወስዳለን። የሚደርሰው ጉዳትም ዓረና_መድረክ ተጠያቂ ይሆናል። በዚህ ሰዓት ሰልፍ ማካሄድ ማለት ሁከትና ብጥብጥ ኣንስቶ የህዝቡ ሰላም መበጥበጥ ነው” በማለት ዛቻው ገልፆልኛል።
እኔም ሰልፉ ለማካሄድ የህግ ክፍተት ስለሌለን እናካሂደዋለን። ብየ ህንፃው ጥየ ወጣው።
በነገራችን ላይ ኣቶ ወላይ ማለት ከዓመት በፊት ከቤቴ ኣፍነው በመውሰድ የኣብራሃ ደስታ ኣሸባሪነት እንድመሰክር፣ እኔ ራሴም ኣሸባሪ እንደ ሆንኩና ትግራይ ሙሉ እየዞርኩ ህዝቡን ይቅርታ ካልጠየቅኩ በፈለጉት ሰዓት መጥተው ኣስረው በመውሰድና በኣሸባሪነት ክስ ከሰው እንደሚያስቀጡኝ በመግለፅና በጉዳዩ እንዳስብበት ኣስጠንቅቀው ከለቀቁኝ 4 የህወሓት የድህንነትና የፀጥታ ባለ ስልጣናት ኣንዱ ናቸው።
በሉ እንግዲህ “ለተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ግዜው ምቹ ኣይደለም ብጥብጥ ሊነሳ ይችላል?” የሚልና “ህወሓት የህዝብ ግምገማ(ፅሬት) እያካሄደ ስለሆነ” የሚሉ ተልካሻ ምክንያቶች በመደርደር ኣግደውታል።
ይሁንጂ በነሱ መስዋእትነት ወደ ስልጣን የወጡት የህወሓት ባለስልጣናት ህዝቡ ብሶቲ ለመግለፅ ኣንድ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንኳን ኣላስቻሉትም።
የትግራይ ህዝብ የውድ ልጆቹ መስዋእትነቱ ኣንድ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያህል እንኳን ዋጋ እንኳ ኣለመስጠታቸው ኣዝነዋል።
ኣቶ ጌታቸው ኣሰፋ የብሄራዊ ድህንነት ሃላፊ በ12ኛ የህወሓት ጉባኤ ” የትግራይ ህዝብ የፈለገው ኣጀንዴ ኣንግቦ ሃሳቡ በሰለማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብቱ እስካሁን ኣልተከበረለትም። ካሁንዋ ሰዓት ጀምሮ መብቱ እንዲጠቀም መፍቀድ ኣለብን” ያለውና ጉባኤተኛው ያጨበጨበለት ንግግሩ ውሃ በልቶታል።
እና ሰለማዊ ስልፉ ከትናንት 10: 00 ጀምሮ እገዳ ተጥሎበታል።
የሰላም በር ሲዘጉ የዓመፅ በሮች ይከፈታሉ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

Previous Story

አረና 21 ጥያቄዎችን ይዞ የፊታችን እሁድ ጠዋት በመቀሌ ሮማናዊት አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

Next Story

ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ… | በዕውቀቱ ስዩም

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win