የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ዜናዎች
ፍካሬ ዜና
ልዩ ልዩ አጫጭር ዜናዎች
የወያኔ የግፍ መዋጮ ሕዝብን እያስመረረ ነው
የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተሰናባች የፓርላማ አባላት ተሰጡ
የተራበው ህዝብ ቁጥር ጨመረ
ወያኔ በኮንሶ ሕዝብ ላይ የሀይል እርምጃ ወሰደ
የቻይና ኩባንያዎች ኢሰባዊነት ተጋለጠ
የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች ገበያ አልባ ሆንን አሉ
በጅቡቲ ውጊያው ተፋፍሟል፤ ፈረንሳይም ሸርተት እያለች ነው
ወያኔ በአውሮጳና አሜሪካ የራሱን ቡችላ ማህበረሰቦች የማቁቋም ጥረቱን በመቀጠል በጣሊያን ሀገር ያለውን ነጻ
ማህበረሰብ የሚቃወም ከተማ አማረ በተባለ ቅጥረኛ የሚመራ ማህበረሰብ አቋቁሟል ። በርካታ አባሎቹ ከክልል
አንድ የመጡ መሆናቸውም ተዘግቧል ። ወያኔ በአውሮጳ ሀገሮች ያሉትን ቤተ ክርስቲያኖችንም ለመቆጣጠርና
ለማፍረስ የሚያደርገውንም ጥረት እጣጧጧፈ መሆኑ ተጋልጧል ።
የሻዕቢያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለግጥሚያ ሄዶ ባለበት በቦትስዋና አስሩ ተጨዋጮች ለመመለስ እምቢ
በማለታቸውና በመኮብለላችው ብሔራው ቡድኑ ፈርሷል ሲሉ ዘጋቢዎች አቅርበዋል ። የሻዕቢያ ተጫዋጮች በገፍ
ሲከዱ ይህ የመጀምሪያቸው አይደሉም ። ይህ በዚህ እንዳለ ግን የአውሮጳ ማህበር ከኢርትራ የሚመጡትን
ስደተኞች ቁጥር ልንቀንስ እንችላለን በሚል አከራካሪ ስሌት ለሻእቢያ እርዳታ ሊሰጥ መወሰኑ ተረጋግጧል ።
በኢትዮጵያ በርካታ ግድቦችን የሰራው የጣሊያኑ የሳሊኒ (ሳልኮስት) ኩባንያ ፍቃድ ሳይሰጠው የግልገል ጊቤ
አራትን ቁፈራ ስራ በመጀመሩ ተወዳዳሪ/ተጫራጭ የነበሩ ኩባንያዎች ቅሬታ አሰሙ ። ግልገል ጊቤ ሶስት ስራው
አልቆ ለሙከራ 70 ሜጋ ዋት ሀይል ማንጨት ጀመሪ ቢባልም ስራውን ለመጨረስ የብድሩ ገንዘብ አነሰ ተብሎ
ክህገራችን ገንዘብ ለሳሊኒ መከፈሉም ይታወቃል ። ሳሊኒ ኩባንያ ለደርግም ለወያኔም ጉቦ እየሰጠ አለተገቢ
ጨረታ ኮንትራት ይይዛል መባሉም የሚረሳ አይደለም ። በተያያዘ ዜና ወያኔ ህዳሴ ግድብ የሚለው አስፈላጊው
ተርባይን መጥቶ ስራው ተጣደፈ የሚለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው ያሉ ክፍሎች ይህ የአባይ ግድብ ገና ከችግሮቹና
ከገንዘብ እጥረቱ ያልተላቀቀ ነው ብለዋል ።
የደርግና የወያኔ ባለስልጣኖች ሁሉ ጸሃፊ ሆነናል ብለው መወራጨት ከጀመሩ ዓመታት ያለፈ ሲሆን በፋሺስቶቹ
ቁንጮዎች (መንግስቱና ፍቅረ ስላሴ )የተጻፉት ደግሞ ጭፍን ቅጥፈቶችና በበር ደረጃም ሀቅን ጨፋጫፊዎች
መሆናቸው የታየ ነው ። ከነዚህ በተሻል መልክ ይቀርባል የተባለው የፍስሃ ደስታ መጽሃፍም ምንም እንኳን
ጸሃፊው ህዝብን ለወንጀላቸው ይቅርታ ቢጠይቅም (በአብዛኞቹ የእርማ ውሰዱ ሰነዶች ላይ ያለው ፊርማ
የእሱነው ) በአያሌ ገጾች የደርግ ሀሰት (በተለይም በኢሕ አፓ ላይ) ደግሞ ማንሸራሸሩ አልቀረም ። በቅርቡ
ደግሞ የወያኔዋ ቅጥረኛ ገነት ዘውዴና ፋሺስቱና ፈርጣጩ መንግስቱ (ቅጽ 2) ቅጥፈታቸውን ያሳትማሉ ይባላል።
በእስር ቆይተው የነበሩት አራት ጦማሪያን ቢለቀቁም ወያኔ ጸረ ነጻ ፕሬስ የመሆኑ ባህሪ ቅንጣት አልቀነሰም ሲሉ
ኢፖእአኮና ሊሎችም የሰባአዊ መብት አስጠባቂ ድርጅቶች አሳሰቡ ። አሁንም ወያኔ በጋዜጠኖችና በነጻው ፕሬስ
ላይ አፈና እያከሄደ መሆኑ መረሳት የለበትም ያሉት እነዚህ ክፍሎች አፋኙ የፕሬስ ህግ ሳይሰረዝ፤ የታገቱ
ጋዜጠኞች ሁሉ ሳይፈቱ፤ ጸረ ነጻ ፕሬስ እርምጃዎች ሳይቆሙ የጦማሪያኑ መለቀቀ ብቻ ያለውን ሁኔታ ሊደብቅ
አይችልም ብለዋል ።
ወያኔ የኢኮኖሚ ጉዞአችን የደቡብ ኮሪያን ይመስላል ሲል ሳያፍር ለፈፈ ። በወያኔ ስር የኢትዮጵያ ለህዝብ የሚበጅ
ኢኮኖሚ አለማደግ ሳይሆን እየከሰረ መሆኑን ሕዝብ ስለሚያውቅ የሚታለል አይሆንም ። ወያኔ ከደቡብ ኮሪያ
የሚመሳሰልበት አንድ ጉዳይ ቢኖር ደቡብ ኮሪያን ከወያኔ ቢሻልም አምባገነን የነበረና ቹንግ ሂ ፓርክ የተባለ መሪ
ቀደም ብሎ ስለነበራት ብቻ ነው ። ፓርክና ወያኔ ግን አሁንም ቢሆን አይመሳሰሉም ።
የወያኔ የግፍ መዋጮ ሕዝቡን እያስመረረው ነው፡፡ ወያኔ ሥልጣን እርካብ በተቆናጠጠበት ወቅት ደርግ ለረሀቡ
ያስከፍል የነበረውን 10 በመቶ የሱር ታክስ ይኮንንና ያወግዝ እንደ ነበር አይዘነጋም፡፡ የወያኔ የታክስ ሥርዐት
ከሕዝብ አቅም ጋር ተዛምዶ የተተከለ ሳይሆን በማን አለብኝነት የተወሰነ በመሆኑ ግብር ከፋዩን ሕዝብ ለመረረ
ችግር ዳርጎታል፡፡ ለመለስ ሙት አመት፣ ለዓባይ ግድብ፣ ለመንገድ ግንባታ፣ ለግብዣ፣ ወዘተ. የተሰኙ መዋጮዎች
ሠራተኛችን በደሞዛቸው ላይ ያላቸውን መብት አሳጥቷቸዋል፡፡ በዚህ አስራ አምስት ቀናት ሕዝቡን ለብአዴን
35ኛ ዓመት ማዘጋጃ በሚል በግዴታ መዋጮ ጥለውበታል፡፡ ይህ ድርጊት የወያኔ እኩይ ባህሪ ይብሱን ያገጠጠበት
እንደሆኑ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ በህንፃ ግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ዘጠና ከመቶው የሚሆነውን ሥራ
የሚወስዱት ከመንግስት በመሆኑ መዋጮ ሲጣልባቸው ላለመክፈል አሻፈረኝ ቢሉ ወደፊት ሥራ ለማግኘት
ይቅርና በአሁኑ ወቅት የያዙትንም ሥራ ሊነጠቁ ስለሚችሉ የተጣለባቸውን ውርጅብኝ ለመቀበል ተገደዋል፡፡
በተመሳሳይም ነጋዴዎች እንዲህ ዓይነቱን ዓይን ያወጣ ገፈፋ ከገፈተሩ ግብር ይጫንባቸዋል፡፡ በፈጠራ ከስም
ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ በዚህ ለብአዴን 35ኛ አመት የግዳጅ መዋጮ ማስተዋወቂያ ስብሰባ ላይ ከተገኙ ታዛቢዎች
መረዳት እንደተቻለው አብዛኛው ተሰብሳቢ በተደጋጋሚ ሲናገር የተደመጠው “ወገን በረሀብ እየረገፈ እናንተ
ለፈንጠዚያ መዋጮ መጠየቅ ተገቢ ያልሆነና በታሪክም ሊያስጠይቅ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡” የሚለውን ንግግር
ነው፡፡ ለዚህ በአማራው ሕዝብ ስም የአማራውን ሕዝብ ቁም ስቅል እያሳየ ላለ ድርጅት ባለስልጣኖች መፈንጠዣ
ከአንድ ሚሊዮን እስከ አስር ሺ ብር የግዳጅ ክፍያ በልዩ ልዩ ሥራ ላይ በተሰማሩ ወገኖች ላይ እንደተጣለ
ለመረዳት ተችሏል፡፡
የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተሰናባች የፓርላማ አባላት ተሰጡ በአዲስ አበባ ከወያኔ-ሰራሽ የሸቀጥ ዋጋ እየናረ ከመሄዱ በባሰ
የቤት ኪራይ ዋጋ ሰማይ ጥግ ደርሷል፡፡ ወያኔ ይህን የሕዘብ ችግር እቀርፋለሁ ብሎ ለማታለያነት እየተጠቀመበት ያለው
የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት ነው፡፡ ይህ ግንባታ ሲጀመርም ለፖለታካ ተረፌታ ተብሎ እንደሆነ አይረሳም የሚሉ ወገኖች
እንደሚሉት ከግንባታው ለምሮ እስከ እደላው ድረስ ሆን ተብሎ ብልሹ እንዲሆን ተደርጓል ይላሉ፡፡ የቤቶቹ አሰራር እረጋ
ሰራሽ መሆኑ አንዱ ወነኛ ችግር ሲሆን የቤቶቹ እደላ የሚካሄደው በብሄረሰብ ማንነትና የወያኔ አባልነት ላይ ተሞርኩዞ
በመሆኑ ለአብዛኛው ተመዝጋቢ ላም አለኝ በሰማ ወተቷን አላይ ሆኖበታል፡፡ ለትግራይ ተወላጆች እስከ አራት ቤት በደም
ካሳ ስም ሲታደል ሌሎች ተመዝጋቢዎች አስራ አንድ አመት ሙሉ እንዲጠብቁ ተደርጓል፡፡ ዘንድሮ ከፓርላማ ለተሰናበቱት
የወያኔ አባላት ቦሌ ቡልቡላ ከተገነቡት የጋራ መኖሪያዎች ውስጡ የተመረጡ አራት ብሎኮች ተመድበውላቸዋል፡፡ ወያኔዎች
የመንግስት ቤቶች ውስጥ እየኖሩ የግላቸው የሆኑ አራትና አምስት ቤቶች ያከራያሉ፡፡ የወያኔ ከፍተኛ መኮንኖችም
በተመሳሳይ እነሱ በመንግስት ቤቶች ውስጥ እየኖሩ ቢያንስ ከሁለት ቤቶች በላይ ያከራያሉ፡፡ ሕዝቡ ግን የቤት ኪራይ
በየጊዜው እየናረ በመሄዱ በሀገሩ ላይ መኖር አልቻለም፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአብዛኛው ኪራይ ናቸው፡፡ የደረሳቸው
ሰዎች ወያኔዎችና ከወያኔዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ይበዛሉ፡፡ ሌላ መኖሪያ ቤት ስላላቸው የደረሳቸውን የጋራ መኖሪያ ቤት
ያከራያሉ፡፡ ኪራዩንም እንዳሻቸው ይጨማራሉ፡፡ ወያኔ ይህን በየወሩ እየናረ በመሄድ ላይ ለውን የቤት ኪራይ ለማረጋጋት
ምንም ዓይነት ደንብ የማይደነግግበት ምክንያት አከራዮቹ በብዛት የወያኔ ካድሬዎች በመሆናቸው ነው በማለት ሕዝቡ
ምሬቱን በብስጭት ሲያወጣ ይደመጣል፡፡
ከድርቅ ጋር በተያያዘ የተራበው ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መሄዱ በይፋ ተነገረ፡፡ ወያኔን ሊሸፋፍን እየሚከረ ያለው ድርቅና
ረሀብ እየሰፋና እየመረረ በመሄዱ የዓለም የምግብ ድርጅት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በመንደርደሩ ሳቢያ በረሀብ
አለንጋ እየተንገላቱ ያሉት ሰዎች ቁጥር 8.5 ሚሊዮን አንደሆነ ቢገለጽም የተረጅው ቅጥር ከ16 ሚሊዮን በላይ ሊሆን
እንደሚችል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኞች እየገለጹ ነው፡፡ ለእርዳታ ይፈለጋል ተብሎ የተሰላው ገንዘብ 12 ቢሊዮን ብር
ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወያኔ አስቀድሞ ከካዝናው 4ቢሊዮን ብር እያወጣሁ ነው የሚለውን ልፈፋ ውሸት መሆኑን እየለፈፈ
ወያኔን በቅጡ የሚያውቁ የፖለቲካ ተንታኞች እያስረዱ ነው፡፡ ወያኔ ከረሀብተናው አፍ እየነጠቀ መብላት ልማዱ መሆኑ
ሊረሳ እንደማይገባው ያወሳሉ፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ወያኔ ዋሾ፣ ቀማኛና ቀጣፊ በመሆኑ በረሀብተናው ስም
አራት ቢሊዮን ብር ለወያኔ ቁንጮዎች ኪስ ማዳበሪያ ለማዋል ሲባል የተሰላ ሴራ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በተመሳሳም የወያኔው
ጠቅላይ ሚንስትር ከረሀብተናው ጋር እንደተወያየ የመገናኛ ብዙሀኖቹ አስተጋብተዋል፡፡ ረሀብተኛ ምግብ ይቀርብለታል
እንጂ በስብሰባ አንዲደርቅ አይደረግም፡፡ ይህ ሁሉ ሽር ጉድ በማድረግ ወያኔዎች ከራሳቸው ውጪ የሚያታልሉት እንደሌለ
የሚረዱት አይመስሉም፡፡ በረሀብተኛ ሕዝብ ስም ገንዘብ ማካበት የተዳፈነውን የሕዝብ ቁጣ መጫር መሆኑን ለጊዜው
የሚያውቁት አይመስልም፡፡
ሰሞኑን ወያኔ በኮንሶ ሕዝብ ላይ የኃይል ርምጃ የወሰደ መሆኑ ታወቀ፡፡ የኮንሶ ሕዝብ ማንነቱን ለማስከበርና ባህሉን
ለማበልጸግ የእራሱ እስተዳዳር እንዲኖረው በመጠየቁ በፈጥኖ ደራሽ እና በፌደራል ፖሊስ በሚዘገንን ሁኔታ
ተጨፍጭፏል።የኮንሶ ሕዝብ በሰላማዊ ሁኔታ ላለፉት ዘጠኝ ተከታታይ ቅዳሜዎች እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት
መብቱን ለመጠየቅና ለማስከበር ሳያሰልስ እየተሰባሰበ ሲመክር ሰንብቶ ነበር፡፡ በየጊዜው የሚሰበሰብው ሕዝብ ቁጥር
እየጨመረ መሄዱ ጥያቄው የሕዝብ ጥያቄ ለመሆኑ ዓይነተኛ ማስረጃ ነው፡፡ የሕዝብ መነሳሳትን ክፉኛ የሚፈራው ወያኔ
ከበስተጀርባ ተቃዋሚዎች አሉ በሚል ሰልፈኛውን በጭካኔ ደብድቧል፡፡ ይህን የመሰለው አረመኔያዊ ድርጊት ትግልን
ያፋፍማል እንጂ አይገታውም የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች ቁጥር በርካታ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን የቻይና ኩባንያዎች ኢ-ሰብአዊነትን አጋለጠ፡፡ የቻይና ኩባንያዎች
የሠራተኞችን መብት የሚረግጡ፣ የሠራተኛ ማህበር ማቋቋምን የሚገድቡ፣ ሠራተኞችን የሚሰድቡ፣ የሚደበድቡ፣ ደሞዝ
ከልክለው ከሥራ የሚያባርሩና፣ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፍሉ መሆናቸውን በመጥቀስ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታረሙ
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን በተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢጽፍም ምንም ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡ የቻይና
ኩባንያዎች በማንአለብኝነት ለሚጻፍላቸው ደብዳቤ እንኳ ምላሽ ባለመስጠተቸው ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት
ክስ የመሰረት ቢሆንምና እስከወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ድረስ ማመልከቻ ቢያቀርብም ያገኘው ውጤትና ምላሽ የሌለ
መሆኑን ገልጿል፡፡ የወቅቱን የኢትዮጵን የፖለቲካ ምህዳር በመተንተን የሚታወቁ ተንታኞች እንደሚያስረዱት የቻይና
ኩባንያዎች በወያኔ ውስጥ ያሉ መንግስቶች በመሆናቸው ማንም የሚነካቸው የለም ይላሉ፡፡ በተያያዘ ዜናም በአገር ውስጥ
ያሉ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ሊሠሯቸው የሚችሉ የግንባታ ሥራዎች ሁሉ ለቻይና ኩባንያዎች በገፍ እየተሰጡ
መሆናቸውን ብዙዎች በምሬት ይገልጻሉ፡፡ ቻይና ታበድራለች፤ ቻይና ትዘርፋለች፤ ቻይና የሥራ አጥ ዜጎቿ ማራገፊያ
አርጋናለች የሚሉ ወጣት ፖለቲኮች ቁጥር በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ በቅርቡ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን
አስተናጋጅ ከቻይና መቅጠሩ አገርን ብቻ ሳይሆን ዓለምንም ያስደመመ መሆኑ መስታወሱ ተገቢ ይሆናል፡፡
የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች ገበያ በማጣታቸው እሮሮ እያሰሙ ናቸው፡፡ ወያኔ በጥናት ላይ ያልተመሰተረተ የገበያ
ሥርዐት እያካሄደ በመሆኑ የሚቋቋሙ በመፈራረስ ላይ መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ ባለሀብቶችን ለመሳብ ወያኔ ገበያ
እንደሚያመቻች ባዶ የተስፋ ቃል በመግባት ወደ ሥራ እንዲገቡ ቢያደርግም ችግሩ ሳውል ሳያድር በመከሰቱ በርካታ
ኩባንያዎች ለመዘጋት ተዳርገዋል፡፡ ከዚህ በፊት አንድ መቶ አራት የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች የንግድ ፈቃድ የወሰዱ
መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ስድስቱ ብቻ በሥራ ላይ ሆነው ይታያሉ፡፡ በኪሳራ ከተዘጉት መካከል
አንደኛው ሆላንድ ካርስ የሚባለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት እያመረቱ የሚገኙት ደግሞ ያንግ ፋን፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል
ኢንጂነሪንግ፣ ቤተሬት ኢንተርናሽናል የተወሰነ የግል ማህበር፣ በላይ አብሞተርስ፣ የብረታ ብረት ኢንጂነሪነግ ኮርፖሬሽን፣
ኒግማ ሞተርስ ናቸው፡፡ አገር ውስጥ የሚመረቱት መኪናዎች የፍሬን ላይ ችግር ያለባቸው ሲሆን የመለዋወጫ እቃቸው
በቀላሉ የሚገኝ ባለመሆኑና ቢገኘም እጅግ በጣም ውድ በመሆኑ ከእነሱ ይልቅ ከውጪ የሚገቡ ያገለገሉ መኪናዎች
ተመራጭነት እንደጸና መቀጠል ችሏል፡፡ ለመንግስት መሥሪያ ቤቶች በግዳጅ የተሸጡት መኪናዎች በአጭር ጊዜ ተሰናክለው
እንደቆሙ የታወቀ ነው፡፡ በመከላከያና በቻይና በጋራ የሚመረተው “ቢሾፍቱ” የሚል ስያሜ የተሰጠው መኪና ብዙም
ሳያገለግል እየቆመ ለመሆኑ አንበሳ አውቶብስ በግዳጅ እንዲገዛ ተደርጎ ከሁለት መቶ ስልሳ አውቶብስ በላይ እየተሳናከለ
ቆሟል፡፡ ይህን መጥፎ ስም ለማደስ የተለየ ስም በመስጠት ለመንግስት ሠራተኞች አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶች
በአብዛኛው ጠዋትና ማት ሠራተኛ ወደ ሥራ ሲገባና ከሥራ ሰወጣ የሚነዱ በግብር ከፋዩ ሕዝብ ገንዘብ ተገዝተው ቀኑን
ሙሉ ተገትረው ይውላሉ፡፡ ገበያ ያላቸው መገጣጠሚያዎች የወያኔው መስፍን ኢንጂነሪግና የመከላከያው ብረታ ብረት
ኢንጂነሪንግ ሲሆኑ እነሱም በአንዳንድ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በግዳጅ ከሚሸጡት በስተቀር ሌላው ሰው አይገዛቸውም፡
፡ ወደ ጎረቤት አገር ለመላክ የታሰበ ቢሆንም ከቅዠት ሊሻገር የማይችልበት ምክንያት ኬንያ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እንደዚሁ
የቻይና የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች ስላሉ ገበያ አይኖርም፡፡ ድርጅቶቹ ያመረቷቸው መኪናዎች በቆሙበት እየዛጉ
እንደሆነ በመግለጽ መንግስት ሊገዛቸው እንደሚገባ እየተወቱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የግሉን የንግድ ዘርፍ የወያኔ
ኩባንያዎች በማጣበባቸው ገበያው በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ እንቅፋት ሆነዋል፡፡ መከላከያም ከግዙፍ እስከ ትናንሽ
ሥራዎች በመግባቱ የግሉን የንግድ እንቅስቃሴ እያሽመደመዱት ይገኛሉ፡፡
በጅቡቲ ከመስከረም 30 ጀምሮ የተጧጧፈው የአገዛዙና የተቃዋሚው ፍሩድ ውጊያ አሁንም ተፋፍሞ እየተካሄደ ሲሆን
በቅርቡ በተልያዩ ከተሞች የፍሩድ ደጋፊዎች ናችሁ በማለት የገሌህ አገዛዝ በርካታ ዜጎችን አስሯል ። ከዚሁ ተያይዞ ፍሩድ
የተባለው ተቃዋሚ ሀይል ከታጁራህ ወደ ሰሜን የመኪና መንገድ ይሰራ የነበረውን የሲሺል ኩባንያ የጭነት መኪናዎች
ማቃጠሉ ተነግሯል ፡፤ ይህን እርምጃ ድርጅቱ የወሰደበት ምክንያት መኪናዎቹ የወታደር ማመላላእሻ ሆነው በማገለገላቸው
ነው ሲል የፍሩድ ፕሬዚዳንት መሃመድ ካዳሚ አብራርቷል ። ገሌህ ከቻይና በመቀራረቡ የተቆጡ አሜሪካና ፈረንሳይ ሲሆኑ
ፈረንሳይ የፍሩድ ፕሬዚዳንት በራዲዮኗ ቃል መጠይቅ እንዲደረግለት ፈቅዳ ለመናገር የቻለ መሆኑ ታውቋል ።
ታዬ አስቀስላሴ የሚባለው የወያኔ አሸርጋጅና ባለሟል ለአሽከርነቱ ካሳ በወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ
ተብሎ መሾሙ ታውቋል። ታዬ አስቀስላሴ የብአዴን አባል ሆኖ ከማገልገሉ ባሻገር ፎረም 84 ን በማደረጀትና በውጭ
አገርም በዋሽንግተን ዲሲ የወያኔ ኢምባሲና በሎስ አንጀለስ የወያኔ ቆንስላ ውስጥ በመመደብ በአገርልጅነትና በትውውቅ
ግለሰቦችን ለወያኔ ባለሟልነት ሲመለምል የነበረ በተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ሴራ በመጎንጎን ሆነ ስለላ በማካሄድ ለመከፋፈል
ጥረት ሲያደርግ የቆየ ዋና የወያኔ አገልጋይና አጫፋሪ ግለሰብ ነው።
በኢትዮጵያና በሱዳንና ወሰን አካባቢ በኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮችና በሱዳን ወታድሮች መካከል ሰሞኑን ግጭቶች
የተፈጥሩ መሆናቸው ከአካባቢው የተገኙ ዜናዎች ይገልጻሉ። የወያኔ አገዛዝ በወሰን አካባቢው የሚገኘውን ለም መሬት
ለሱዳን አሳልፎ ከሰጠ ጅመሮ የአካባቢው አርሶ አደር በየጊዜው በሱዳን ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽም የቆየ መሆኑ
የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን ኢትዮጵያውያኑ በሱዳን ወታደሮች ላይ የወሰዱት እርምጃ ጠንካራ በመሆኑ ሱዳን ተጨማሪ
ወታድሮች ለመላክ የተገደደ መሆኑ ተነግሯል። የወያኔ የሱዳን ባለስልጣኖች ስለጉዳዩ ምንም የሰጡት መግለጫ ባይኖርም
የሁለቱም ከፍተኛ የድህንነት ባለስልጣኖች ሰሞኑን ካርቱም ውስጥ የድብቅ ስብሰባ ማድረጋቸውን ከስብሰባው አካባቢ
ሾልኮ የወጣው መረጃ ይገልጻል። ሰሞኑን በድንበር አካባቢ የደረሰው ሁኔታ ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከል አንደኛው
ሲሆን በቅርቡ በጋራ ለማኬሄድ ባቀዱት ፕሮጀክት ላይ እና እንዲሁም በሱዳን ስለሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ የተነጋገሩበት
መሆኑ ታውቋል።