የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 11, 2025 ነፃ አስተያየቶች Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል 4 ፡የአማራ ትግልና የፋኖ ማኒፌስቶ በተደጋጋሚ አማራ የትግል ማኒፌስቶ የለውም የሚለው ጉዳይ ይነሳል። አዎ የለውም። ይህ ማለት ሁሉም በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የሚገኙ የፋኖ ቡድኖች ማኒፌስቶ መጻፍ ተስኗቸዋል ማለት አይደለም። እጅግ በርካታ ማኒፌስቶዎች ተጽፈዋል። ማኒፌስቶ መጻፍ በጣም ቀላል ነገር ነው። በተለይ የአማራ ህዝብ የትግል ማኒፌስቶ። የጎጃሙ የፋኖ አመራር አባል የሆነው አርበኛ አስረስ እንዳለው በቀን 5 ማኒፌስቶ መጻፍ ይቻላል። አርበኛ አስረስ ሁለት አይነት ማኒፌስቶዎች እንዳሉት ገብቶታል። እየተፈለገ ያለው ማኒፌስቶ ዝርዘር የፖለቲካ ፕሮግራምና ፖሊሲዎች እንዴት በተግባር ሊተርጎሙ እንደሚችሉ የሚያሳይ ለምርጫ እየዘጋጁ ያሉ ፓርቲዎች የሚያቀርቡት አይነት ሰንድ አይደለም። ይህ አንዱ አይነት ማኒፌስቶ ነው። ይህ አይነት ማኒፌስቶ የሚዘጋጅበት ሁኔታ የተለየ ነው። ማዘጋጀቱም ዝርዝር ጥናት የሚጠይቅ፤ ሰነዱም በጣም ብዙ ዝርዝር ነገሮችን ያካተተ ነው። ሌላው ማኒፌስቶ በጣም ጥቅል ጉድዮችን የሚያነሳ ነው። የድሮው አብቅቶለት፣ በአዲስ አተያይ በአዲስ አካሄድ ወደ አዲስ ዘመን የሚውስድ ነገር መምጣቱን የሚያበሰር ጥቅል የሆነ መነሻና መዳረሻን የሚያመላክት ማኒፌስቶ ነው። አንዳንድ ማኒፌስቶች ጥቅል ሆነውም ረጅም ሊሆኑ ይችላሉ። ዝነኛውና በ1848 በካርል ማርክስ በፍሬድሪክ ኤንግልስ የተጻፈው የኮምኒስት ማኒፌስቶ እንደዚህ አይነት ነው። በትንሽ መጽሃፍ መልኩ የተሰነደ ነው። ይህ የሆነው ሰፊ የንድፈሃሳብ ይዘት ስለነበረው ነበር። አንዳንድ ማኒፌስቶች በጥቂት ገጾች ብቻ የሚጠቃለሉ ናቸው። ሱራሊዝም የሚባለው በ1924 አዲሱን የምስል አሳሳል ፈለግና ንድፈ ሃሳብ ለማመላከት የተጻፈው ሰነድ ስደት ገጾች ርዝመት ነበረው። በተግባራዊ ፖለቲካ በስፋት የሚታወቀው፣ በሩሲያው ንጉሰ ነገስት በኒኮላስ ሁለተኛው ተፈርሞ በ1907 አ.ም የታተመው የጥቅምቱ ማኒፌስቶ በሚባል የሚታወቀው ሰነድ ብዙ መሰረታዊ የፖለቲካ ቁምነገሮችን አካቶ በአንድ ገጽ ተኩል ላይ ብቻ ያረፈ ነበር። ንጉሰ ነገስት ኒኮላይ የአገሩን ፖለቲካ ለመቀየር የሚወስዳቸውን አዳዲስና ጥቅል እርምጃዎችን የሚያመላክት ሰንድ ነው። ዝርዝር ውስጥ አይገባም። የአማራ ህዝብ ካላበት የፖለቲካና በተለይ ወታደራዊ አቅም ደረጃ ሲታይ ዝርዝር ውስጥ የሚገባ ማኒፌስቶ አያስፈልገውም። በጥቅሉ ምን ትግሉን እንደቀሰቀሰው ትግሉ በየት አልፎ የት መድረስ እንደሚፈልግ፣ የሚያመላክት ሊሆን ይችላል። ለአማራ ለተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ለቀጠናውና ለአለም ማህበረስብ የሚያውጀው ነገር ይኖረዋል። አበቃ። በጣም ዝርዝር ውስጥ የሚገባ ማኒፌስቶ የውጭ አካላትን ማሳመን ቅርቶ በፋኖዎችም መሃከል ስምምነት እንዳይኖር ሊያደርግ ይችላል። ማኒፌስቶው ጥቅል የሆኑ ነገሮችን ያካተተ እንዲሆን የሚመከረው ለዚህ ነው። ሌላው ትልቁ ቁም ነገር ማኒፌስቶ ማዘጋጀቱ ሳይሆን ማኒፌስቶውን ሁሉም የአማራ ፋኖዎች በጋር የተቀበሉትና ያጸደቁት መሆኑ ነው። ይህ እስካልሆነ ድረስ የተለያዩ ማኒፌስቶዎች በተለያዩ ቡድኖች መዘጋጀታቸው ብቻ፣ አማራ ትግሉን በተመለከተ ማኒፌስቶ የለውም የሚለውን ክስ ማስቆም አይቻልም። ስለሆነም ትልቁ አንገብጋቢ ጥያቄ ማኒፌስቶ ሳይሆን የህልወናውን አደጋ የጋራ አጀንዳና መሰባስቢያ አድረጎ አንድ የአማራ ፋኖዎች የጋራ የፖለቲካና ወታደራዊ አደረጃጀት መፍጠር ነው። ይህ አደረጃጀት በተፈጠረ ማግስት የማኒፌስቶ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ በፋይናንስ፣ በሎጂስቲክ፣ በዲፕሎማሲ፣ በህዝብ ግንኙነትና በሌሎችም የስራ ዘርፎች የአማራ የህልውና ትግል የገጠሙትን ሌሎችንም ችግሮች በቀላሉ መቅረፍ ይቻላል። ፋኖ የጋራ አመራር ከፈጠረ በኋላ በማኒፌስቶ ላይ ከሚቀርቡ ጥቅል ከሆኑ ጉዳዮች ወደ ዝርዝርዝ ጉዳዮች መግባት ይችላል። እነዚህ ዝርዝር ጉዳዮችም ቢሆኑ የአስፈላጊነት ቅደም ተከተል ያላቸው የፋኖን የፖለቲካና ወታደራዊ አደረጃጀት እድገትና ጥንካሬ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰሩ ናቸው። ከማኒፌስቶ በፊት ከሌላም ጉዳይ በፊት፣ የአማራ ፋኖ የስራዎች ሁሉ እናት የሆነው ስራው አንድ ፖለቲካዊና ወታደራዊ የጋራ አመራር ባስችኳይ የማቆም ስራ ነው። የአማራን የህልውና ትግል የሚደግፍ ማንኛው የአማራ ህዝብ ወዳጅ፣ ጉልበቱን እውቀቱን ሃብቱን ስራ ላይ ማዋል የሚገባው ይህ የጋራ አመራር በፍጥነት እንዲፈጠር በመጣር ስራ ላይ ነው። ይህ እንዳይፈጠር የሚፈልግ ወይም የሚጥር አማራ ከዋናዎቹ የአማራ ጠላቶች ልዩነት ያለው መሆን አይችልም። Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Related Posts የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 10, 2025 የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 8, 2025 የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 7, 2025 Previous Story ከዋቃ ጉራቻ ወደ ዋቃ ዳለቻ:- የድህነት ወይስ የትንቢት እዳ? Next Story ፍጥጫው ከሯል – መቀሌ ውጥረት ነግሷል – ጦርነት በቅርብ አድፍጧል Latest from Same Tags የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡ 3 የአማራ የህልወና ትግል የአማራ ታጋዮች የጋራ ግንዛቤ፤ የአማራ የህልወና አደጋ እንዲህ በቀላሉ በዋዛ ፈዛዛ የሚቃለል እንዳልሆነ የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡2 ያለፈው እና መጪው ዘመን ለአማራ፤ ነብይ፣ ጠንቋይ፣ ሳንቲስት መሆንን አይጠይቅም። ያለፉትን መቶ ለመሙላት ጥቂት አመታት የቀረውን ዘመን የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ከአጻጻፍና ከይዘት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሀ) የቅርጽ ጉዳይ የማንበብ ባህል እየተዳከመ መጥቷል። በመሆኑም ሰፊ ትንታኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በአጭሩ ጨምቆ አብይ አህመድ በገዛ ወሬው የስከረ መሪ – አንዳርጋቸው ጽጌ ነሃሴ 2016 የሚገርም ዘመን፣ ከዋናው የሃገር መሪ እስከ ተራው ካድሬ ምንም አይነት የሞራል ኮምፓስ የሌላቸው፤ የሞራል ልጓማቸው የተበጠሰባቸው ሆነዋል። የኢትዮጵያ ጉዶች ። እንዳንዴ ለእነዚህ አንዳርጋቸው ጽጌ ሣይቀር የሚሣለቅበት አማራ ይህችን የጨለማ ዘመን ካለፈ ምንም አይል – ሥርጉት ካሣሁን (አዲስ አበባ) ይሄ “እንደሠራ አይገድል” የሚባል አማርኛ አንዳርጋቸው ጽጌን የመሳሰሉ የታሪክ ዝቃጮችንና በሞቀበት ዘፋኞችን ለመግለጽ ምንኛ ክርክም ያለ ውብ ገላጭ መሰላችሁ! ብዙ ነገሮች አጀማመራቸው ቢያምር አጨራረሳቸው
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡ 3 የአማራ የህልወና ትግል የአማራ ታጋዮች የጋራ ግንዛቤ፤ የአማራ የህልወና አደጋ እንዲህ በቀላሉ በዋዛ ፈዛዛ የሚቃለል እንዳልሆነ
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡2 ያለፈው እና መጪው ዘመን ለአማራ፤ ነብይ፣ ጠንቋይ፣ ሳንቲስት መሆንን አይጠይቅም። ያለፉትን መቶ ለመሙላት ጥቂት አመታት የቀረውን ዘመን
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ከአጻጻፍና ከይዘት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሀ) የቅርጽ ጉዳይ የማንበብ ባህል እየተዳከመ መጥቷል። በመሆኑም ሰፊ ትንታኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በአጭሩ ጨምቆ
አብይ አህመድ በገዛ ወሬው የስከረ መሪ – አንዳርጋቸው ጽጌ ነሃሴ 2016 የሚገርም ዘመን፣ ከዋናው የሃገር መሪ እስከ ተራው ካድሬ ምንም አይነት የሞራል ኮምፓስ የሌላቸው፤ የሞራል ልጓማቸው የተበጠሰባቸው ሆነዋል። የኢትዮጵያ ጉዶች ። እንዳንዴ ለእነዚህ
አንዳርጋቸው ጽጌ ሣይቀር የሚሣለቅበት አማራ ይህችን የጨለማ ዘመን ካለፈ ምንም አይል – ሥርጉት ካሣሁን (አዲስ አበባ) ይሄ “እንደሠራ አይገድል” የሚባል አማርኛ አንዳርጋቸው ጽጌን የመሳሰሉ የታሪክ ዝቃጮችንና በሞቀበት ዘፋኞችን ለመግለጽ ምንኛ ክርክም ያለ ውብ ገላጭ መሰላችሁ! ብዙ ነገሮች አጀማመራቸው ቢያምር አጨራረሳቸው