ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በባርነት እና በዕስር መሆናቸዉን ከረጂም ዓመታት ያላሳለሰ ህዝባዊ ብሄራዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ያላሳለሰ ትግል በማድረግ በሁለት ሽ ስምንት ዓ.ም. የነፃነት ትግል ፍሬ አሽቷል፡፡
ይህም ኢህአዴግ በራሱ አልቃሽ እና ዘፋኝ ሆኖ በሚገኝ አድር ባይ የፖለቲካ አባላት አንዱ አሸባሪ እንዱ ተቆርቋሪ እንደነበር እና ኢህአዴግ እና ስርዓቱን በመታደግ የስርዓቱን ጨቋኝ ዕድሜ ማራዘም የተቻለዉ በኢትዮጵያዉያን እና በተለይም በዓማራ ህዝብ ወሳኝ ተጋድሎ ነዉ ፤ነበር ይህንም ያፈነገጠዉም ሆነ የተገላበጠዉ ኢህአዴግ እና አመራሮች የመሰከሩት እናየሚመሰክሩት ነዉ ፡፡
ሆኖም የተናገሩትን ትተዉ በዕስር እና ከባርነት ያወጣቸዉን እና ከወደቁበት አንስቶ ወደ ስልጣን ማማ ዕርካብ ያወጣቸዉን ባለዉለታ ህዝብ የዓማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጀዉ ከዕስር ያወጣቸዉን ህዝብ ጣራ አልባ ዕስር ቤት ዉስጥ በአዲሱ ተያይዘዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ትህነግን እና ኢህዴን/ብአዴንን ከሞትበት አስትንፋስ ዘርቶ ፤ ከወደቀበት መቃብር ፈንቅሎ ፤ ከአፈር አንስቶ ፤ ከተደበቀበት ጎትቶ ከጎንደር እና ከትግራይ በረኃ አዉጥቶ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በራሱ የሞት እና የጭቆና ቋጥኝ ጭኖ ከዚህ መከራ ለመዉጣት ከፍተኛ ዋጋ ኢትዮጵያዉያን ከፍለዋል ፡፡
አገር ሲያረጂ ሜጭ ያበቅላል ፤ ዐድባር ሲጠፋ አምቧጮ አድባር እንዲሆን ላለፉት ሶስስት ዓመታት በታሪክ ኢትዮጵያ እና ህዝቦች በተለይም ዓማራ የመከራ መድብል እና የመከራ ቤተ ሙከራነታቸዉ ብሷል ፡፡
ስለ ነፃነት እና ህልዉና ስንናገር በመከራ እና ጭቆና ምድር ዉስጥ ጣራ እና በር ባላቸዉ ዕስር ቤት ባቻ የሚገኙትን ብቻ ሳይሆን ለአንድ ክ/ዘመን አጋማሽ ስደት ፣ ባርነት ፣ ሞት እና ዉርደት ዉስጥ ላሉት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ከጣራ አልባ ዕስር ፤ ከምድር ሲኦል ለመዉጣት መነጋገር ፣መግባባት ፣መምከር እና ለአነድ ህዝብ እና አገር መተባበር የሚኖርበት ጊዜ አሁን ነዉ ፡፡
“በዘመነ ሉቃስ ጥላቻ እና ክህደት ይደምሰስ ”
“ ኢትዮጵያ ከመከራ ወደ መድረ ፍስኃ ትሸጋገራለች ፡፡”
“ተስፋችን ከዘመናት መላቀስ ወደ ዘመነ ሉቃስ ዘመነ ድህነት እና ዘመነ ካሳ ነዉ ፡፡”
“ነፃነት እና ህልዉና ዕዉን የሚሆነዉ በአንድነት እና በዓላማ ፅናት በሚቆም ክንድ ነዉ ፡፡”
“አንድነት ኃይል ነዉ ”