![](https://cdn.statically.io/img/amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/04/279350451_293809442942518_8662268630049886372_n.jpg?quality=100&f=auto)
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከትናንት በስቲያ በጎንደር ከተማ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንደገለጹት፣ የጐንደር ከተማ በሁሉም የሃይማኖት ተቋማት በመቻቻል፣ በመከባበር የሚታወቅ ከተማ ነው። ይሁን እንጂ ሰሞኑን ከሁሉም የሃይማኖት አስተምህሮ ውጭ የሆነ ድርጊት ተፈጥሯል።
የተፈጠረውን ችግር ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ከእምነቱ አስተምህሮ በተቃረነ መንገድ እያራገቡ ለተጨማሪ ጥፋት የሚቀሰቅሱ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል።
የተፈጠረው ችግር ከየትኛውም የሃይማኖት አስተምህሮ ያፈነገጠ በመሆኑ ጉባኤው አውግዟል።
ጠቅላይ ጸሃፊው በመግለጫቸው፣ የተፈጠረውን ችግር የሃይማኖት ግጭት በማስመሰል ሀገር ለማተራመስ በሚሰሩ አካላት ላይ የክልሉ መንግስት የእርምት እርምጃ እንዲወስድም ጉባኤው አሳስቧል።
በሞገስ ተስፋ/(ኢ.ፕ.ድ)