የህብር ሬዲዮ የካቲት 23 ቀን 2006 ፕሮግራም
እንኳን ለአድዋ ድል 118ኛው በዓል አደረሳችሁ!!
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
<...በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚባለው ጥቂቶች የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩበት ብዙዎች በሚያስፈራ ድህነት ውስጥ የወደቁበት... ውጭ ውጩን በህንጻዎች ግንባታ የተጋረደ ውስጡን ግን የከፋ ሙስና የተንሰራፋበት ሁኔታ ነው ያለው ይሄ አደገኛ ነው ...>>
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የቀድሞው የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ ምልልስ(ሙሉውን ያዳምጡ)
<...የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ሕዝቦች ድል ነው ይሄን ማንም አይነጥቀንም ። ዛሬ ለሚረገጠው መብታችን ግን አባቶቻችን አንድ ላይ እንደቆሙት በጋራ መቆም አለብን ...>
አቶ ስዩም መንገሻ የአንድነት ዋና ጸሐፊ የአድዋን 118ኛ በዓልን በአዲስ አበባ ስላከበሩበት ሁኔታ ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<<...ለረዳት አብራሪው ሀይለመድህን አበራ ፊርማ ማሰባሰብ ጀምረናል ።ፊርማው ለስዊዝ ባለስልጣናት የሚቀርብ ነው...>>
አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ ረዳት አብራሪው እንዲፈታ ጥረት የሚያደርገው ግብረ ሀይል አባል ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ
የህብር ሬዲዮ አራተኛ ዓመት በዓል ልዩ ሪፖርት
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
– ሙስና ኢትዮጵያን እያጠፋት መሆኑን የቀድሞው የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪ ገለጹ
– ሱዳን በአገሯ የኢትዮጵያ አማጺያንን እያሰለጠነች መሆኑ ተገለጸ
– ኢትዮጵያውያን ግፍ በዛብን ብለው የሳውዲን እስር ቤት ሰብረው ወጡ
* ጩኸትና የጥይት ተኩስ ተሰምቷል
– የአድዋ ድልን መዘከር ብቻ ሳይሆን በአንድ ላይ ቆመው ለመብታቸው እንዲታገሉ ጥሪ ቀረበ
– ተቃዋሚዎችም እንዲተባበሩ ተጠይቋል
– ኩዌት ኢትዮጵአውያን የጉልበት ሰራተኞችን አልቀበልም አለች
– ረ/አብራሪ ሀይለመድህንን የስዊዝ መንግስት ጥገኝነት እንዲሰጠው የሚጠይቅ ፊርማ መሰብሰብ ተጀመረ
– የመጀመሪያው ድሪም ላይነር አብራሪና የአየር መንገዱ ም/የስራ ሀላፊ በፈቃዳቸው ለቀቁ ተባለ
– አንድነት በባህር ዳር ያደረኩትን ተቃውሞ አዲስ አበባን ጨምሮ በ12 የአገሪቱ ከተሞች ይቀጥላል አለ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ