የሶማሊያ መንግስት ጦር ባለፉት 48 ሰዓታት በመካከለኛው ሸበሌ ግዛት ባካሄድኩት ዘመቻ 28 የአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች ገደልኩ አለ፡

January 31, 2022
ጥር 21፣ 2014
ጦሩ ጽንኞችን የማፅዳት ዘመቻውን ያካሄደው በባላድ ከተማ አቅራቢያ እንደሆነ የቱርኩ አናዱሉ ፅፏል፡፡
ባላድ ከመዲናዋ በስተሰሜን በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ እና ወታደራዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ከተማ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
ጦሩ በባላድ አቅራቢያ ባካሄደው ዘመቻ 28 የፅንፈኛውን ቡድን ታጣቂዎች ከመግደሉም በተጨማሪ ምሽጋቸውን ማውደሙም ተሰምቷል፡፡
አልሸባብ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የጦር መላውን ወደ አጥፍቶ መጥፋት እና ወደ ድንገት ደራሽ ጥቃት ማዞሩ ይነገራል፡፡
በአፍሪካ ህብረት (አሚሶም) የሚደገፈው የሶማሊያ መንግስት ጦር ከፅንፈኛው ቡድን ጋር ሲዋጋ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
የኔነህ ከበደ/ ሸገር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“እነዚህ ሰዎችኮ ሠይጣኖች ናቸው!” – ዳንኤል ሽበሺ

aklog birara 1
Next Story

ሁሉም ነገር ወደ አፋር ግንባር!!! ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ ህወሓትን መደምሰስ ያስፈልጋል – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

Go toTop