“እነዚህ ሰዎችኮ ሠይጣኖች ናቸው!” – ዳንኤል ሽበሺ

January 31, 2022
ትክክለኛነቱ ገና ቢሆንም ሰሞኑን ከሕወሓት ጋር የድርድር ንፋስ ሽውው እያለ ነው ። ከወደ አገር ኬኒያ ።
የኔ ጥያቄ?
“እነዚህ ሰዎች ሠይጣኖች ናቸው!” በተባሉበት ሁኔታ እንዴትና በምን ቋንቋ ከሠይጣን ጋር መነጋገር እንደሚቻል ነው ግራም ቀኝም የገባኝ ። በተሰጣቸው ስያሜ መሠረት ይወራ ከተባለ ከሠይጣን ጋር የሚደራደር አንዴም ከሠይጣን ከፍ የሚል አሊያም በልኩ ያለ ሌላይኛው #ሠይጣን መሆን አለበት ። በተያያዘም ከሰይጣን ጋር የሚነጋገር ምን አይነት ሰው ነው? እንደምን ሊግባባ ይችላ? ብለን ከጠየቅንም ነውርነት ያለው አይመስለኝም ።
ቢያንስ “እነዚህ ሰዎችኮ አውሬዎች ናቸው!” ብለናቸው ቢሆን ኖሮ ለድርድርም ለንግግርም ይመቸን ነበር ። ምክንያቱም አውሬን በሂደት ማላመድ ይቻል ይሆናልና ግን ሠይጣንን እንደት?
ስለዚህ ጥያቄው በአካልም፣ በገብርም ሰዎች መሆናቸውን ክደን «ሠይጣኖች ያደረግናቸው እኛ ነን» ማለት ነውና በጊዜ ለንስሐ መዘጋጀት አለብን ። የተሳሳትን እኛ ነን ወይስ እነሱ? ብለን በሞራል ጥያቄ ራሳችንና ነፍሳችንን የምናስጨንቅበት ጊዜ ቢኖር አሁን ይመስለኛል ። ያም ሆነ ይህ …
«”ተጨባብጠን እየመጣን ነው?”»
….
በግል ስብዕናዬም፣ እንደሰላማዊ ታጋይም፣ በሃይማኖት ፣ በባህል ተጽዕኖ ውስጥ እንዳለ ሰው በድርድር፣ በንግግር፣ በውይይት፣ በይቅርታ፣ በምህረት … አምናለሁ ። እነዚህ ሁሉ እሴቶቼ ቢሆኑም ግን ለሁሉም ነገር ወግ አለው ባይ ነኝ ። የተመረጠ መንግሥት፣ የሕዝብ ውክልና ያለው ገለመለ የሚባለውን ድስኩር እንዳልሰማ ፈጣሪዬን እየተማፀንኩ፤ አንተ ጥቁር ሕዝብ ሆይ! በተለመደው ሆደ ሰፍነትህ፣ መከራ ባጎመጠው ጫንቃህ ሕወሓትን #ይቅርታ ለመጠየቅ ተዘጋጅ ። አሁንም የጠየቁትን ለመስጠት እጅህ አይሳሳ¡ ሌላ ምርጫ የለንምና ።
“ጣጣችን ጨርሰን ተጨባብጠን እየመጣን ነው?”
ቸር ያሰማን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ጀነራል ባጫ ደበሌ ሰራዊታችን ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅ አለበት አሉ

Next Story

የሶማሊያ መንግስት ጦር ባለፉት 48 ሰዓታት በመካከለኛው ሸበሌ ግዛት ባካሄድኩት ዘመቻ 28 የአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች ገደልኩ አለ፡

Go toTop