ጀነራል ባጫ ደበሌ ሰራዊታችን ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅ አለበት አሉ

January 31, 2022

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሥራዎች አስተባባሪ ጀነራል ባጫ ደበሌ ሰራዊታችን ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅ እንዳለበት አስገነዘቡ፡፡

የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ሰራዊታችንን በዘርና በኃይማኖት ለመከፋፈል በሚዲያ የሚያሰራጩትን አሉባልታዎች በመስማት የውስጣችንን አንድነት መሸርሸር የለብንም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ማንኛውም ሰራዊት በመካከላችን ከተቀላቀለ ፕሮፌሽናል የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው፣ የእኛ አላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማሰከበርና ሰላሟን ማስጠበቅ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
የመሃንዲስ ሥራ እንደ ስሙ ምንጊዜም ከባድ ነው፣ መሃንዲስ የለሌው ሰራዊት መሪ እንደሌለው አይነ ስውር ነው፣ ዛሬ ያገኛችሁት የሜዳሊያና ሌሎች ሽልማቶች የግዳጃችሁ አፈፃፀም ውጤት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌ/ጀነራል ደስታ አብቼ፣ ሀገራችን አትበተንም በማለት የመሃንዲስ ክፍሉ ከፍተኛ አስተዋፆኦ አደርጓል ብለዋል፡፡
በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በግዳጅ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ጥር 23/2014 (ዋልታ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በፋኖ ደም ሊነግድ የገባው የለንደኑ ወራዳ ፣ ልክስክስ፣ ይሉታቢስና ውታፍ ነቃይ ዲያስፖራ – ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ

Next Story

“እነዚህ ሰዎችኮ ሠይጣኖች ናቸው!” – ዳንኤል ሽበሺ

Go toTop