“አማራ ይንቀናል! ይንቀናል! ወደታች ነው የሚያዩን! በጣም ይንቀናል፣ እያልክ እንዴት 50 አመታት ታለቅሳለህ?” (ኢሳያስ ትናንት ካደረገው ንግግር ውስጥ በጥቂቱ)
“…. ህዳር 4 በስለላዎቻችን አማካኝነት ትነግ ጦርነት እንደሚጀምር እርግጠኞች ነበርን።
ሚሳኤል ተኮሱብን። ኤርትራን ለመምታት ያሠቡት ታርጌቶች 100 ነበሩ በወያኔ ተመርጠው የተቀመጡት።
ራሣችንን የመከላከል መብታችንን ተጠቅመን ነው ወደጦርነት የገባነው። እንጂ ጦርነቱንማ 18 አመታትኮ ታግሰናል መሬታችን ተወርሮ።
በሰሜን እዝ ከ32,000 በላይ ወታደሮች ሲኖሩት ከ10,000 በላይ ወያኔዎች ነበሩ።
በአአው ኮንፈረንስ ቢያንስ የብሔር ክፍፍሉን ተውት ትግላችሁ ላይ የነበረውን ክፍፍል ያብሰዋል ብያቸዋለሁ።
4ጊዜ የህገመንግስቱን ድራፍት አንብቤዋለሁ ተቃውሞየንም ሰጥቻለሁ። ይሄ አገር አይገነባም። ይህ ህግ ethnic institutionalization ያመጣል ለኛም ለቀንዱም ጥሩ አይደለም። አሁን ተቀራርባችሁ አገር መገንባት የሚያቀራርብ እንጂ እንዴት የሚያራርቅ ነገር ትሰራላችሁ? ብየ ሀሳቤን ሰጠሁ። ቃል በቃል “እኛ መግዛት የምንፈልገው ሁሉም ቦታ ላይ ቦንብ በመትከል ነው” ነው ያሉኝ።
አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው ሁሉ በወያኔ ፕላን የተሰራ ነው፣ ባጋጣሚ አይደለም።
ኋላቀርነት፣ ርሃብ፣ ችግር secondary ነገሮች ናቸው። አገር እንድትፈርስ የመጀመሪያው ምክንያት በዘር የተዋቀሩ ተቋማት ሲቋቋሙ የሚያመጡት ችግር ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ለውጦች እኛንም ይነካሉ፣ ኢትዮጵያ ብትወድቅ የውጭ ሃይሎች መጫወቻ ነው የምንሆነው።
ወያኔን ወደ ስህተት ከወሰዱት አንዱ የውጭ ደጋፊዎች በተረጎሙት miscalculation ነው።
አሁንም ጦርነቱ አላለቀም። ስስታምና ስግብግብ የሆነ ሃይል መቸም በሰላም ሊተኛልህ አይችልም። ሰሞኑንም የጀመርነው ክተት መክት ከዚህ ጋር ዳይሬክት ባይገናኝም ግን የወያኔ ወንበዴዎች አርፈው ስለማይቀመጡ ነው።
አሁን ላይ አሜሪካ በተለይ በኢኮኖሚ በቻይና ተበልጣለች። እኛና ኢትዮጵያ ላይ የምታሣድረው ጫና ያረጀው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የጀመረ የmonopolar ፖለቲካቸው ውጤት ነው። እኔን ጨንቆኝ አያቅም ምክንያቱም አቀዋለሁ የራሷ ጉዳይ ነው። የራሣቸው የፈጠሩትን ቴረሪዝም ለሌሎች ማዕቀብ መጣያ ነው ያደረጉት። … ውሳኔያቸው ሁሉ የሚገዛው በlaw of the jungle ነው። … በሂደት አለም አንድ እየሆነ እነሱን መታገል ይችላል።
ቀንና ሌሊት ኤርትራ እንድትጠላ ሰይጣን እንድትመስል ሲሰሩ ነበር።
ኤርትራ የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ አለባት ይሄ ለራሣችንም ሰላም ስንል የምናደርገው ነው።
… የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋሚ በአፋኙ ህወሀት የሚመራ የሚመስለው ራሱ ሞኙ ህወሀት ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊያን እኔ የሚመስለኝ በርግጥ በዘር መከፋፈሉ ያኗኑረናል ወይ? ብለው መጠየቅ አለባቸው። እኛ ሽግግራችሁ 10አመታት ይወስዳል እንደዛ አድርጉ ብለናቸው ነበር ተጣድፈው የዘር ፌደራሊዝሙ ውስጥ ገቡ ቀጥለውም አንቀጽ 39ን አስቀመጡ።
የሁሉም የኢትዮጵያ ችግር መነሻ የወያኔ ቡድን የ50 አመት ጥላቻ ነው።
አማራ ይነቀናል! ይንቀናል! ይንቀናል! amahara chauvinism እያሉ ህዝባቸውን ቀሰቀሱበት። ት*ግ*ሬ ብቻ ሳይሆን ብዙ ህዝብን የሚንቅ በጣም ትንሽ ስልጣን የነበረው ቡድን ነበረ እንጂ ያማራ ህዝብ አይደለም። በመጨረሻም ት*ግ*ሬን የተለየህ ነህ ብሎ ሌላ ኢጎ ፈጠሩበት። ይሄው አሁን ጥላቻው በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ት*ግ*ሬ ብቻውን ቀረ። ሰው እንዴት ለ50 አመታት ሙሉ ጥላቻን ማኔጅ እያደረገ ይኖራል?
ባለፉት 14ወራት ስንት ት*ግ*ሬ አለቀ? ስንቱ ተፈናቀለ? ይሄንን ኪሳራ ማወቅ አለበት የት*ግ*ሬ ህዝብ። …
Wonde Berhanu Kabaw