ቀፎው እንደተነካበት ንብ ትመም- አማራ!

November 1, 2021

ጠላት እንደ ህዝብ ወሮናል፡፡ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከአካል ጉዳተኛ እስከ ነፍሰ ጡር እናቶች፤ ከካኽን እስከ ሸክ፤ ከኢንጅነር እስከ ዶክተር፤ ከተማሪ እስከ አስተማሪ ፤ ከቀን ሰራተኛ እስከ መንግስት ሰራተኛ ድረስ አስልፎ ወደ ክልላችን ገብቶ ወረራ የፈፀመ ሲሆን፤ በሂደቱም ንፁሀንን እየገደለና እያፈናቀለ፣ ሴቶችን እየደፈረ፣ የአማራን ህዝብ ንብረት ዘርፎ ወደ ትግራይ እያጓጓዘ፤ ያልቻለውን ደግሞ እያወደመ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ዛሬ ላይ ትግራይ ውስጥ አንድም ወጣትና ጎልማሳ አይገኝም። አብዛኛው ኃይል ነቅሎ ክልላችንን በመውረር ላይ ይገኛል። ዛሬ ላይ ትግራይ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ቢኖር ዕድሜው ከ 10 ዓመት በታች የሆነ ህፃን፤ ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች እና ታመው አልጋ ላይ የተኙ ህሙማን ብቻ ናቸው፡፡

አብዛኛው የትግራይ ወራሪ እና ዘራፊ መንጋ ውሎ አዳሩን በወረራ በያዛቸው በአማራ መሬቶች ውስጥ አድርጓል፡፡ ምግብና መጠጡንም ከአማራ አርሶ አደር በመዝረፍ ላይ የተመሰረተ አድርጎታል፡፡ ይህ የሚያሳየን የዘራፊውና ወራሪው የትግሬ መንጋ ዋነኛ ግቡ አማራን አንገት ማስደፋት፣ ሥነ-ልቦናውን መስበርና ለአንድ መቶ ዓመታት በድህነት ወደ ኋላ መመለስ ነው፡፡

ስለዚህ ሰፊው የአማራ ህዝብ ይህንን አደገኛ ወራሪ እና ዘራፊ መንጋ የደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን የአስቸኳይ ጊዜ ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ‹ቀፎው እንደተነካበት ንብ› ወደ ሁሉም የጦር ግንባሮች ለመትመም ይረዳ ዘንድ በወረዳ ማእከል እንድትከት ታሪካዊ ጥሪ ቀርቦልሃል!!

ካንተ በሁለንተናዊ መስኩ የሚያንሱ አካላት ማንነትህን ደፍረው አንገትህን ሊያስደፉህ እንደማይችሉ የማይበገረውን ጀግንነትህን ዛሬውኑ አረጋግጥላቸው፡፡

እናንተ የአማራ ወጣቶች!

እናት እና እህትህን እየደፈረ፣ የወገንህን ንብረት እየዘረፈ እና እያወደመ ያለውን ቀንደኛ የህዝባችንን ጠላት መቀበሪያውን አማራ ምድር ላይ በማድረግ የአባቶችህን ታሪክ እንድትደግም ታሪካዊ ጥሪያችንን እናቀርብልሀለን፡፡

በመጨረሻም!

ከሀገር ውጭ የምትገኙ ውድ የአማራ ልጆች፣ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጠላት ትህነግ የሚነዛን የሽብር ወሬ ቦታ ባለመስጠት የሥነ-ልቦና ጦርነቱን በበላይነት መምራት ይኖርብናል። በህልውና ትግሉ ዙሪያ በሀሳብ፣ በቁሳቁስና በገንዘብ በመደገፍ ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በርግጠኝነት የምንናገረው ነገር ጠላት ጨርሶ ወደመቃብር መውረዱ አይቀሬ ስለመሆኑ ነው። የሰው ልጅ ቀርቶ እንስሳት እንኳ በጦርነት ሕይወታቸው እንዲያልፍ የማንሻ ቢሆንም ወራሪን መቅጣት ጥንትም የአባቶቻችን ነውና ሞት ምርጫው ለሆነ የትግራይ ወራሪ እና ዘራፊ ሀይል ምህረት የለንም። ለትግራይ ወራሪ የሚዝል ክንድ እንደሌለን የአማራ ምድርን የታሪክ ምስክር እናደርገዋለን!

Amhara Prosperity Party /APP

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ሁሉን በምግባሩ እና ተግባሩ እንጥራዉ ! – ማላጂ

Next Story

ኑ! እንወቃቀስ-1 እንድ ጊዜ ጥንቃቄ! – ቴዎድሮስ ጌታቸው

Go toTop