ዶ/ር አብይን በእውቀት እንወቅ – ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

September 24, 2019

የኢትዮጵያ ነገር መላ እንደሌለው፤
አምላኳ አወቀላት ጉዳዩ ሌላ ነው።

ብርሃን ፈነጠቀ ዶ/ር አብይ መጣ፥
ኢትዮጵያን ሊታደግ እርሱ እንቅልፍ አጣ፥
ሁሉም ደገፈና አንድ ላይ ሰልፍ ወጣ፥
ልናርፍ ነው ብሎ ከነበረን ጣጣ።

ቃሉ የሚጣፍጥ የሌለው ወደር፥
ትህትናው ግሩም ልዩ ከምድር፤
ፅናቱ የሚገርም ደግሞም እይታው፥
ድፍረቱ ትጋቱ እጅግ የሚደንቀው።

ጠላቱ እያደር እየበዛ ሲሄድ፥
ወደድኩህ ያለውም ሊያወጣው ከመንገድ፤
ከወዲህ ከወዲያ ሁሉም ሲጎትተው፥
ስምም እያወጣ ቢጎነታትለው፤
ዝም ብሎ ነጎደ አልተነቃነቀ፥
ሁሉንም እያየ አውቆም እያወቀ።

የኢትዮጵያ ነገር መላ እንደሌለው፥
አምላኳ አወቀላት ጉዳዩ ሌላ ነው፤
ጠላቶቿ በዙ እጅግ ጨከኑባት፥
ስለዚህ ወረደ አምላክ ሊፈርድላት፥
ምድር ዝም ትበል ይታይ ሲለይለት።

ትዕግስት አይጠቅመንም ቶሎ ያልቃልና፥
ተስፋም አይረዳንም ስጋት ያንቃልና፤
ይልቁንስ እንይ የማይታየውን፥
በእውቀት እንወቅ አይለፈን ይህ ቀን።

Previous Story

የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቁጣቸውን ለጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ

Next Story

“Fly out of Ethiopia while you can.” ማለትስ አሁን ነው – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

Go toTop