የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሸን የንግድ ሥርዓቱ በሙስና የተዘፈቀ መሆኑን አረጋግጫለሁ አለ…(ትዕግስት ዘሪሁን)

January 22, 2016
ኢሕአዲግ

ይህን የሰማነው ኮሚሽኑ ዛሬ የአዲስ አበባ ነጋዴዎችንና የንግድ ሥርዓት አስፈፃሚ የሆኑ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎችን ሲያወያይ ነው፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ወዶ አጦ እንዳሉት የንግድ ፈቃድ ለማደስ የሚጠየቅ ጥቅማ ጥቅም አለ፣ በትላልቅ የመንግሥት ንብረትና አገልግሎት ግዢ ላይም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ብር ይጭበረበራል፡፡

በተጨማሪም የዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር የተገናኘ መሠረታዊ የንግድ ሥርዓት ችግር መኖሩንም ሰምተናል፡፡

በመሠረታዊ የሸቀጣ ሸቀጥና የፍጆታ እቃዎች አቅርቦትና ስርጭት ህዝቡን እያማረረ ነው ተብሏል፡፡ የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የንግድ ዕቃዎችም በመመሳጠር ለወጪና ገቢ ንግድ ፈቃድ እንዲሚሰጥ ደርሼበታለሁ ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

በንግድ ስርዓቱ ላይ ያሉ የተበላሹ አሰራሮችንም አይቻለሁ፤ ብቻዬን ለውጥ ማምጣት ስለማልችል የንግዱ ማህበረሰብም ችግሩን በማጋለጥና መፍትሄ እንዲመጣ በማድረግ ሊያግዘኝ ይገባል ሲል የንግዱን ማህበረሰብ እያወያየ ነው፡፡

እንደ አለም ባንክ ግምት ከሆነ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ የአለም አገሮች 80 ቢሊየን ዶላር በየአመቱ በሙስና መልኩ ይከፈላል፡፡

 

Previous Story

የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማ የመጨረሻቸው በሆነው በዓመታዊ ንግግራቸው ላይ ያሰሟቸው ታሪካዊ ንግግራቸው እና የቀረቡባቸው ትችቶች (ልዩ ዘገባ)

Next Story

“የሕዝቡን ጥያቄ ከ140 በላይ ንጹሃን ተገለውም ስላልተመለሰ ተቃውሞው ቀጥላል” – ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር

Go toTop