በቃሊቲ እና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!!

May 1, 2014

በቃሊቲ እና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!! ህዝቡ በነቂስ በመውጣት የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል!! በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል የሰየመውና እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ከህዝብ ጎን ሆነን ድምፃችንን እንዳናሰማ በግፍ የተወረወርንበት እስር ቤት ቢያግደንም ከአርብ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እስከሚደረግበት እለት ድረስ የርሀብ አድማ በማድረግ ከህዝቡ ትግል ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳያለን ሲሉ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ህዝቡ ከየቤቱ በነቂስ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Millions of voices for freedom – UDJ
Previous Story

6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ውጥረት ነግሷል፤ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተዋል

Next Story

ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉና የአንድነት የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ታሰሩ – ፖሊስ ህገ ወጥ እስሩን ቀጥሏል

Go toTop