ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ማንም አያንብበኝ፡፡ ከኔ ግን ይውጣ፡፡ እናም እጽፋለሁ፡፡ ለ35 ዓመታት የጻፍኩት ለኅሊናየ እንጂ ለሌላ አልነበረምና ሊያልቅ ሲል ዝም አልልም፡፡ አንድም ሰው ያንበኝ አሥር ሰውም ይጎብኘኝ የራሱ ጉዳይ፡፡ “ማቴዎስ 10፡14 – ማንም ሰው ሊያስተናግዳችሁ ወይም የምትናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ከቤቱ ወይም ከከተማው ስትወጡ የእግሮቻችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ።” Matthew 10:14, Jesus states, “And if anyone will not welcome you or listen to your words, shake the dust off your feet when you leave that home or town”. እናም አዳሜ እንቅልፍህን ድቃ፡፡ በኦነግም አዚም ተዝናና፡፡ ስንትና ስንት ሀገራዊ ጀብድ መፈጸም ስትችል ማበድና መስከርም ሆነ ራስን ማጥፋት ያማረህ ሁሉ በዳግማዊ ግራኝ አቢይ አህመድ ተፈቅዶልሃልና በነፃነት ያሻህን አድርግ፡፡ እኔም እንደለመድኩት ልጩህ፡፡
ወደዋናው ነጥቤ ከመግባቴ በፊት በሰሞነኛ ጉዳዮች ላይ ትንሽ ላንዣብ፡፡ አቢይና ቡድኑ – ቡድን ካለው – የለየላቸው ዕብዶች ናቸው፡፡ ባያብዱ ኖሮ በዚህን ወቅት የነዳጅ ዋጋ አይጨምሩም ነበር፡፡ አለመጨመር ብቻ አይደለም መቀነስ ነው የነበረባቸው፡፡ ግን ዕብድ የሚፈራው ነገር ስለሌለ ማንን ወንድ ብለው ከዕብደት ማማ ይውረዱ፡፡ ቤንዚን በሊትር ብር 112.67 ሆኗል ከትናንት ማታ ጀምሮ – የጨመረው ብር 11.17. ነው፡፡ ትልቅ ጭማሬ ነው፡፡ አምስተኛ ረድፈኛ የሚባል ካለ ሥራውን በደምብ እየሠራ ነው፡፡ ነገም ይጨምሩ፡፡ ጥሩ ነው፡፡
ነዳጅ ሲጨምር አብዛኛው ዜጋ ገልቱ ስለሆነ የሚያስከትለው ሁለንተናዊ ማኅበራዊ ውጥንቅጥ አይገባውም፡፡ እንዲያውም “እኔ መኪና የለኝ! ሺ ብር ቢገባ ምን አገባኝ?” የሚል ጅላንፎም ሞልቷል – ዕውቀትና ጥበብ ተቀብራ ድድብናና ድንቁርና በነገሠባት ሀገር የማታየው የዕንጭጭነት መገለጫ የለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሽሉ በእናቱ ሆድ ቢጨነግፍ የሚሻለው ዜጋ የሚሄደው በታክሲ መሆኑን፣ እህልና ሸቀጥ ከክፍለ ሀገር የሚመጣለት በመኪና መሆኑን፣ አገልግሎት የሚሰጡት ድርጅቶችና ተቋማት ሁሉ በዋጋቸው ላይ ለውጥ የሚያደርጉ መሆናቸውን ጭምር ልብ አይልም፡፡ ነዳጅ ማለት የአንድ ሀገር የልብ ትርታ ነው፡፡ የማይነካው ማኅበራዊ እንቅስቃሴ የለም፡፡ ይህን እያወቁ ነው እንግዲህ በዚህ ዱሮውን እጅግ የተቃወሰ ማኅበራዊ ሕይወት አሁን ካለበት ይበልጥ ለማቃወስና መቃብራቸውን ለማቃረብ እነዚህ ዕብዶች ባለቀ ሰዓት የነዳጅን ዋጋ የጨመሩት፡፡ ለዚያውም መጨመር ካለባቸው አሥር መቶኛውን ብቻ እንደጨመሩ ነው የተናገሩት፤ አማራን የሚዋጉትም በአሥር መቶኛው ጦራቸው ብቻ መሆኑን ምርኮኛ አሥር አለቃ ጁላ ቀደም ሲል መናገሩ እንዳይዘነጋ ታዲያ፡፡ በነገራችን ላይ የጨመሩት አሥር መቶኛውን ከሆነ ዘጠና ብሩ በቅርቡ ይጨመራል ማለት ነው – እያዘጋጁን መሆኑ ነው፡፡ “ሚስትህ ወንድ ወለደች?” ቢለው “ማንን ወንድ ብላ!” አለው አሉ አንዱ፡፡ የኛም ነገር እንደዛው ነው – ሺህ ቢጨምሩ እኛ’ቴ ወይ ንቅንቅ!! እኛ እማንችለው ድሎትና ምቾት እንጂ ስቃይና መከራን በደንብ ነው የምንጠኸነነው ማለትም የምንሸከመው፡፡ የቡርኪናን የመሰለ ግሩም መሪ ቢሰጠን እሱን አበሳጭቶ ለመድፋት አንድ ዓመት አይፈጅብንም፡፡
የደርግ ዘመን የስልሳ ብሩ ሠርገኛ ጤፍ በዚህ የነዳጅ ጭማሬ ሃያ ሺህ ብርን ሊያልፍ ይችላል – አሁን ከጭማሬው በፊት ነጩ ጤፍ ሃያ ሺህን እየታከከ እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ በሰሞነኛው ገበያ የስድስት ብር አቮካዶ 80፣ የ12 ብር ምሥር ክክ 320፣ የ5 ብር ቀይ ሽንኩርት 80፣ የ3 ብር ሙዝ 70፣ የ5 ብር ብርቱካን 300፣ የ10 ብር ኪሎ ሥጋ ቁርጥና ጥብስ እንደዬቦታው ከ2500 በላይ፣ የ16 ብር አዲስ መንጃ ፈቃድ ማውጫ 15000፣ የ50 ብር ቆዳ ጫማ ከ2500 ጀምሮ፣ የ5 እና 10 ብር ነጭ ሽንኩርት ከ300 በላይ፣ የ2 ብር ቲማቲም 80፣ የ50 ብር የአገር ውስጥ አየር ቲኬት 4000፣ የ12.55 የአውቶቡስ ቲኬት 2000፣ የ15 ብር ከናቲራ 450 … እንደሆነ ተጠቃሚዎች ነግረውኛል – እኔማ ከዕለት ፍጆታ ጥቃቅን መሠረታዊ አስቤዛዎች ውጪ አይነካካኝም፡፡ በዚህ በአዲሱ ጭማሪ ደግሞ ዋጋዎች እንዴት እንደሚጦዙ ነገ የምናየው ነው – “እንኳን ዘምቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ” እንዲሉ ነው፡፡ በውነት ግን ኢትዮጵያ እኮ በአቢይ አልፎላታል፡፡ ቡርኪናፋሶ በወጣቱ መሪ በኢብራሂም ትራኦሬ እየተምነሸነሸች ሳለ እኛ በሲዖል ተወካይ አቢይ አመድ በቁማችን ሥጋችን እየተተለተለ ምድራዊ ሲዖል ውስጥ እንኖራለን፡፡ እንደእግዚአብሔር የሚያዳላ የለም፡፡ ይህን ስል ደግሞ እነእፎይ ጩሁቡኝ አሏችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከካናዳ ወይም ከአፍሪካዊቷ አንጎላ ሕዝብ የበለጠ ኃጢኣተኛ ሆኖ አቢይን የመሰለ በሰው ዘር ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ጨካኝ ላከበት ብሎ የሚከራከር መምህር ከመጣ በደፋርነቱ አጨበጭብለታለሁ፡፡ እግዚአብሔር የ34 ዓመቱን ትራኦሬን ለቡርኪና ፋሶ ሃቀኛ መሲህ አድርጎ ሲልክ የሰው ሥጋና ደም ካልበላና ካልጠጣ እንቅልፍ የማይወስደውን የ50 ዓመት ጎልማሣ አቢይን ለኢትዮጵያ ሲልክ መንስኤው ምንም ይሁን ምን ልክ ነው ብዬ መቀበል ይቸግረኛል፡፡ ደግሞስ አንድ ሕዝብ እንዴት ከ50 ዓመታት በላይ በተከታታይ ይቀጣል? አመክሮ እንዴት ይጥፋ? ምሕረት የምትባል ቃል ከሰው ስምነት በዘለለ ወዴት ገባች? ስለዚህ ሰባኪዎች ስትሰብኩ ፈጣሪን ላለማስከፋት ብላችሁ በምትሰብኩት የተለመደ ስብከት ስሜቴን ላለመንካት አሳማኝ ሰበብ እንድትፈልጉ በእግረ መንገድ ሳስባችሁ እንደድፍረት አትቁጠሩብኝ፡፡ ይህን ስል ግን በአባቴ በኅያው እግዚአብሔር ኅልውና ላይ ጥያቄ ኖሮኝ እንዳልሆነ አስረግጬ መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ፍርዱ ነው ያልገባኝ፡፡
ብ/ጄኔራል ምግበ(ይ?) ኃይለ የአማራ ፋኖ በጎንደርን፣ የአማራ ፋኖ በጎጃምን፣ የአማራ ፋኖ በሸዋን፣ የአማራ ፋኖ በወሎንና ፋኖ ቢዛሞን በወለጋ እየመራ አዲስ አበባ ሊገባ እንደሆነ መከላከያ ሰሞኑን ነግሮናል – ደስ ሲል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ አርበኛ ፋኖ ምግበይ የሚመራው የፋኖ ጦር በጅብ ቆዳና በግልገል ጅቦች የምትሃት ኃይል እየታገዘ ጥይትና ድሮን ሳይነካው አራት ኪሎን ሊቆጣጠር መቃረቡንም ከፊልድ ማረሻ አሥር አለቃ ጁላ ሰምተናል፡፡ ይሄ ጁላ ከንግግሩ ጀምሮ ሲያስጠላኝ ግን! ምናለ ቅሞና መርቅኖ ወይ ሰክሮ ተወላግዶ ማይክ ባይጨብጥ! በስምንተኛው ሺ ማለትም በመጨረሻው ዘመን “ማይም ለማይም ትከሻው የማይሸከመውን ወታደራዊ ማዕረግ ይሰጣል” የሚል ትንቢት ተነግሮ ይሆን? ሊያውም ባገር ውስጥ የወንድማማቾች ጦርነት – ሊያውም ከመቀሌ ደብረ ብርሃን በሽሽት ለተመጣበትና በሽንፈት ለተደመደመ ጦርነት፡፡ ወይ አቢይ! እንዴት እንዳዋረደን ታሪክ ራሱ ጥርሱን ተነቅሶ ሲስቅብን ይኖራል፡፡ ግን ግን ከነዚህ የተሻለ ኦሮሞ ጠፍቶ ይሆን አንዳቸው ከአንዳቸው የማይሻሉ ማይማን ኦሮሙማዎች – አይቶ አያውቅ ዳቦ ፍሪዳው – ዓይነት ገገማዎች እንዲህ የሚጫወቱብን? ለነገሩ አይፍረድ ነው፡፡ ለማንኛውም ነገን ማጣጣም እንድንችል አዳነችን፣ ሽመልስን፣ አቢይን፣ ለጌ ቱሉን፣ መራሩን ጉዲናን… እናስባቸው፡፡ በእውንህ ቀርቶ በህልምህ ያላየኸው እርዚቅ ከደጅህ ሲመጣ እንዲህ ያደርጋል፡፡
ልጨርስ ነው፡፡ ኦሮሞና ትግሬ ወይም ሌላ ነገድ ሆናችሁ ከነገሩ የሌላችሁበት ምንም ሥጋት አይግባችሁ፡፡ በመሠረቱ የሰው ዘር አንድ ነው፡፡ ስለሆነም ሰውን “ዘረኛ” የምንለው ተለምዷዊ እንጂ ትክክል አይደለም፡፡ ይንጣም ይጥቆርም፣ ይወይብም ይቅላም የሰው ዘር ከጽንፍ እስካጽናፍ አንድ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረው አዳምን እንጂ ከርከሮን ወይም ትንኝን አይደለምና ይበልጡን በአካባቢያዊና በአየር ንብረታዊ ለውጥ የተነሣ ከዚያም በቀደመ መጽሐፉ እንደሚለው በሰዎች መመረቅና መረገም ምክንያት በተፈጠሩ ልዩነቶች የተነሣ የሰው ልጅ በዘር እንደሚለያይ አድርጎ መቀበልና ማመንና ስህተት ነው፡፡ ዶናልድ ትራምፕና እኔ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ – እሱ በነጭነቱ እኔ በጥቁርነቴ ብንኮራና ብናፍር ይህ ምድራዊ ልዩነት እኛ የፈጠርነው እንጂ በፈጣሪ ቤት እዚህ ግባ የሚባል ጉዳይ አይመስለኝም፤ አይሆንምም፡፡ ነፍሳችንና የጽድቅና ኩነኔ ሥራችን እንጂ ዕውቀት ቀለማችን እሱ ዘንድ ቦታ የላቸውምና፡፡ We don’t have to forget the difference in dimensions as well. ዳይሜንሽንን ያለመረዳት ችግር ነው እንግዲህ አንዳንድ ጅላጅሎች “እዚያ ስትሄድ ዘጠና ዘጠኝ ልጃገረድ ይቀርብልሃል” ሲባሉ በደስታ በመፈንጠዝ ልሂቆቻቸውን የሚታዘዙትና በጠላትነት የተፈረጀላቸውን የገዛ ወገናቸውን ባልተወለደ አንጀት በሠይፍ አንገቱን የሚቀሉት – ወይ የኛ የምድራውን ድንቁርና! ለወሬም እኮ አይመችም እናንተዬ፡፡ ስለሆነም ያለን ልዩነት ነገዳዊ እንጂ ዘራዊ አለመሆኑን በዚህ አጋጣሚ አለቦታውም ቢሆን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ የሆነው ቢሆን ሁላችንም የአዳም ልጆች ነንና አማራን በነገዱ ሳቢያ ወይም በሀሰት በተፈጠረ ትርክት ምክንያት እስካሁን ትገድሉትና ታሰቃዩት የነበራችሁ ወገኖች ተፀፅታችሁ ከተመለሳችሁ እሰዬው ካልተመለሳችሁ ግን የምትጠፉበት ጊዜ እጅግ ቀርቧል – እውነቴን ነው ድራሻችሁ ነው የሚጠፋው፡፡ የአማራን ጀግንነት ላለማመንና ወደወያኔ ለማላከክ መከላከያ ተብዬው የተጓዘበት የሀሰተኛ መንገድ ርቀት አሁን ለምለው ምፅዓተ አማራዊነት ትልቅ ምልክት ነው፡፡ የመጣው ጊዜ ማቄን ጨርቄን አያስብልም፡፡ አማራን በቆንጨራና በጎራዴ አንገቱን እየበጠስክ ትዝናና የነበርክ ሦዶማዊና ስድ አደግ ኦሮሙማ ሁላ የምትገባበት የሚጠፋብህ ዘመን እየመጣልህ ነው፡፡ ሠርግ ላይ ሳይቀር በየዳንኪረኛው ፊት ላይ እየረጨህ እንደጭቃ የምትረግጠው ገንዘብ፣ እንደውኃ የምታንደቀድቀው ዊስኪ፣ እንደቆሎ የምትከተው ጮማ ሥጋ ህልም ሆነውብህ ወደከርሰ መቃብር የምትወርድበት ጊዜ ቀርቧል፡፡ ለዘመናት ተሸክሞ የቻለህና በትግስቱ ብዙ ነገርን ያለፈህ አማራ አሁን እየመጣልህ መሆኑን የማረዳህ ብትችል ከጥጋብህ ተመልሰህ የትንሣኤው አካል እንድትሆን ልመክርህ ነው፡፡ መፈጠርህን የምትረግምበት ጊዜ በየደጅህ ነው፤ ይህም መቅሰፍት እውን የሚሆነው ባጠፉና ኅሊናቸውን በዘመን አመጣሽ የጎሣ ፖለቲካ ባሳወሩ ላይ እንጂ በንጹሓን አይደለም፡፡ አማራ ሆዳሞችና ኅሊናቢስ ባንዳዎች ቢኖሩበትም እንደአጠቃላይ ብያኔ የብልህነቱና የአስተዋይነቱ የፍትኅ ሚዛን በምንም ዓይነት የግፍና የሥቃይ አእምሯዊ ጠባሳ አይዛባም፡፡ ስለሆነም ከነገሩ የሌላችሁበት ሌሎች ነገዶች ከፍትሃዊው አማራ ጎን ተሰልፋችሁ የጋራ ሀገራችሁን ከነዚህ ጭራቆች ማዳንና በጋራ መኖር ብቸኛው አማራጫችሁ መሆኑን ተገንዘቡ፡፡ በጉጉት ለዘመናት ስጠብቀው የነበረው ታሪካዊ ክስተት ለብዙዎች ባይታይ ለእኔን መሰል “ሩቅ ተመልካቾች” ፍንትው ብሎ የሚታይበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡
ለፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ስለእውነት ብዬ አማራ ያቸንፋል አልልም፡፡ አማራዊነት ግን መጪውን የመለያ ጦርነት እንክት አድርጎ ያሸንፋል – መቶ በመቶ፡፡ ዓለም በአንድ ላይ ቢሰለፍ አማራዊነትን ሊያሸንፍ አይችልም – አማራዊነት የምልህ በውስጡ ኦሮሞም፣ ትግሬም፣ ጉራጌም፣ ሌላውም የተቀየጠበትንና ድርና ማግ ሆኖ ኢትዮጵያን ኅልው ያደረገበትን የወርቅ ጉልላት ማለቴ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አማራዊነትን እየተገዳደረና ነፃነታችንን እያዘገዬ ያለው ከአማራው የወጣው ባንዳ አማራ እንጂ ምን እንደሚናገር እንኳን የማያውቀው ሰገጤው ኦሮሙማ አይደለም፡፡ ኦሮሙማ ትግሩማን ቀጥሎ ባዶ ሆኖ እንዲጠብቀው በቀደምት ፀረ-ኢትዮጵያ ነቀርሣዎች ተመቻችቶ በጠበቀው ቤተ መንግሥት በመግባት የተወሰነ ታሪካዊ ጠባሳ እንደሚፈጥር ከተረዳን 30 ምናምን ዓመታትን አስቆጠርን፡፡ መታገስ ጥሩ ነው፡፡ አሁን ያ ጊዜ ሊገለበጥና አራጆች ለ1000 ዓመታት ደብዛቸው ሊጠፋ አንድ ግፋ ቢል ሁለት ምዕራፎች ያህል ቀሩን፡፡ እንደለመደብህ – “ይሄ ደግሞ ማንኛው ጠንቋይ ነው?” በለኝ፡፡ አይደለሁም – በሆንኩ በወደድኩ፡፡ ዱሮውንስ “ሁለተኛ አማራ አልሆንም” እያለች አንገቷን ቆርጠህ የገደልካት የዚያች ሕጻን ሙስሊም የአንሻ ደም ሊምርህ ታስባለህ? ኦሮሙማዬ፣ ያንተ ውድመት ወያኔዎች የሚቀኑበት ነው፡፡ ያንተ ውድመት እነናዚ ሂትለርና እነፋሽስት ሙሶሊኒ የሚቀኑበት ነው – ሞታቸው በዚህ ዘመን ቢሆን ኖሮ “በየት ባገኘነው!” ብለው ይቀኑበት ነበር፡፡ መለስን አፈራርሶ የወሰደ የታሪክ ባቡር ኦሮሙማንማ …. በስማም!! ልናይ ነው፡፡ “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” የሚሉት ሥነ ቃል ትክክል ነው ከዚህ አኳያ፡፡ ጥጋብና ዕብሪት የሚያስከትለው መዘዝ የክፉ አጋጣሚዎች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ ይህን ሃቅ መጪውን ወጀብ የሚሻገር የሚመሰክረው ይሆናል፡፡
ከሃይማኖቱ በኩልም የሚፀዳው ብዙ ነው፡፡ አሁን እንደምናስተውለው ከሞላ ጎደል ሁሉም እረኞች በሰይጣን ተጠልፈዋል – መጽሐፉም ይላል – “አንድም ሳይቀር ሁሉም በኃጢኣት ሥር ወድቀዋል”፡፡ በጎችን የሚቀራመታቸው እርኩስ መንፈስ የበዛውም ለዚህ ነው፡፡ በየቤተ ክርስቲያኑ የሚሰማው የስብከት ድምፅ ከቤት ጣሪያና ከዛፍ ቁመት የማያልፍ ተራ ጩኸት ነው፡፡ የሚወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል፡፡ የማትሆነውን አትናገር፤ የማታደርገውን አድርጉ አትበል፡፡ አንተ ራስህ ሲጃራ እየማግህ ሲጃራ አትጠጡ ብትል ትዝብት ላይ ትወድቃለህ፡፡ ላንቃቸው እስኪበጠስ በየዐውደ ምሕረቱና በየቲክቶኩ የሚጮኹ “መምህራን” – ከጥቂቶች በስተቀር – ያሣዝኑኛል፡፡ የነእንቶኔን የባንክ ደብተር በገንዘብ የመሙላት ፌዝ ተውት፤ እነሱ መንግሥት ስለሌለ ወይም ጃዝ ብሎ የሚያሰማራቸው የነሱው አለቃ ስለሆነ እንጂ በህግም የሚጠየቁበት ወንጀልና ማጭበርበር እጅግ ብዙ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ አማራና ኢትዮጵያዊነቱን የመረጠ ሌላው ነገድ እንደበግ እየታረደ፣ ለአማራ አዲስ አበባ ከመግባት ይልቅ አውሮፓና አሜሪካ መሄድ እየቀለለ፣ አማራ በገዛ ቀየው በቦምብና በድሮን እየተጨፈጨፈ፣ አማራ ታኅታይ መዋቅሩ ሁሉ እየወደመና ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ሕጻናት ከትምህርት ቤት እየታገዱ፣ ምንም ጥፋት የሌለበት የእህል ክምርና ዕፅዋት ሳይቀሩ በፈንጂ እንዲነዱ እየተደረገ፣ አማራ ሰው እንዳይኖረው ምሁራኑና ታዋቂ ሰዎች እየታሠሩና እየተገደሉ … አንድ ጳጳስ እንኳን አለማውገዙና ምህላም አለመጥራቱ ጳጳሣት በልብስና በማይታዘዙት መስቀል እንጅ በልብና በተግባር እንደሌሉን ከዚህ ነባራዊ እውነት መገንዘብ ይቻላል – ደግሞም አያፍሩም እኮ፡፡ (የሚወራባቸውን ሌላ ሌላ ነገር ብናነሳ እኛም እናብዳለንና ይቅር፤ በትምህርት ረገድም አቡነ ዘበሰማያትንና ሰላም ለኪን እንኳን የማያውቁ ጎሣ-ተኮር ጳጳሳት እንደሚሾሙ የምንሰማውን እዚህ ብንናገር ሃሜት ይመስላልና ይህም ይቅር፡፡ በነዚህና መሰል ነጥቦች ዙሪያ ጊዜው ሲደርስ በግልጽ እንነጋገርባቸዋለን)፡፡ ለማንኛውም ከሚርመሰመሰው እረኛ የሚተርፈው በጣም ጥቂት ነው፡፡ የሚሄደው ይበዛል፡፡ “ኅያዋን በሙታን ይቀናሉ” የሚለው ነባር ትንቢት እውን ሆኖ በምናስተውልበት በአሁኑ ዘመን ምድር ላይ መቆየቱ እምብዝም ስሜት ባይሰጥም ነገም ሌላ ቀን ነውና ለነገ አድርሶን ይህን ቆሻሻ የ666 ዘመን መመስከር እንዲያስችለን በጸሎት እንሰነባበት፡፡ አርበኛ ፋኖ ምግበይን ግን በርታ በሉልኝ፡፡ እሱ ካልመራው የአማራ ፋኖ የትም አይደርስምና በሕወሓት አምላክ፣ በለገሠ ዜናዊ ከራማ ይሁንብህ በሉልኝ፡፡ ሥራ-አጥ ወገኖቻችን ደግሞ ጅቦችን በብዛት እንዲያረቡና ለፋኖዎች እንዲያከፋፍሉ ንገሩልን፡፡ ወይ የአቢይ ቀልድ! ማለቂያ እኮ የለውም፡፡ ነገ ደግሞ ምን ይል ይሆን? ለነገሩ … ሀበሻ ይበልህ፡፡ አንድ ሚሊዮን ከማትደርሰው ጅቡቲ በ130 ዕጥፍ በልጠህ 130 ሚሊዮን ሆነህ ስታበቃ ኅብረትና ፍቅር በማጣትህ አንድ የአራተኛ ክፍል ጩጬ ዕብድ ይጫወትብሃል፡፡ ውይ – ከጨረስኩም በኋላ ጀመርኩ? ሁሉንም በየተራ የምታሳብድ ሀገር ገጠመኝና ምን ላድርግ፡፡