ሕሩይ እስጢፋኖስ Hiruy Estifanos – ጀርመን
ማን ይታደጋቸው?
በኃጢዓት ምክንያት የጠፉትን የሰውን ልጆች ሁሉ ለማዳን ከሰው ልጆች ተወልዶ ሞት የማይገባው አምላክ ሞቶ በደሙ የመሠረታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምላክነቱን አምነው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን ለሚከተሉ ሁሉ እናት ሆና ሳለ።
እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ ማንኛቸውም የእምነት ተቀዋማት ሳይኖሩ በፊት ያለች እና የነበረች ለሀገር ሥልጣኔ መሠረት የጣለች በአጠቃላይ ኢትዮጵያን አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ ያደረሰች እና ቆይተው የመጡትንም የእምነት ተቀዋማት እና የነዚህንም የእምነ ተቀዋማት ተከታይ ማህበረሰብን በፍቅር እና በሰላም አብረዋት እንዲቂዩ ያደረገች እና አሁንም እያደረገች ያለች ናት።
ነገር ግን አሁን ያለው የብልጽግና መንግሥት እና ጠቅላይ ሚንስቴር ነኝ ብሎ በማጭበርበር እራሱን የኢትዮጵያ መሪ አድርጎ የሾመው ዓቢይ አህመድ ይህቺን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን የአማራው ሕዝብ ብቻ እንደ ሆነች እና የእምነቱ ተከታይም የአማራው ሕዝብ ብቻ ነው በሚል እሳቤ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታይ የሆነውን የአማራውን ሕዝብ በየቀኑ በቤቱ እና በእምነት ቦታው በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል እና በማፈናቀል ሀብትና ንብረቱን በማቃጠል ገንዘቡን በመዝረፍ እንዲሁም በዚህ ድርጊት ምክንያት ሸሽቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲጠጋ ቤተ ክርስቲያንንም ሸሽቶ የተሸሸገውንም የአማራ ሕዝብ እያቃጠሉት ይገኛሉ። ስለዚህ አማራውን እና ቤተ ክርስቲያንን ማን ይታደጋቸው?
ይህ አረመኔያዊ ድርጊት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ለአማራው ሕዝብ መሪር ኀዘን ነው!
በየገዳናቱ እና በየአድባራቱ ጉባዔ ዘግተው ተርበው እና ተጠምተው ተተኪ ደቀ መዛሙትን ለማፍራት የሚታስተምሩ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር እየተገደሉ ይገኛሉ።
የዚህ አረመኔ አገዛዝ እቅድ እና አላማ እምነትን እና የእምነት ተቀዋማትን እንዲሁም አማኙን ሕዝብ ማጥፋት ነው።
ምክንያቱም ለእምነቱ መስፋፋት ምክንያት የሚሆኑ ሊቃውንት መምህራንን እና ተተኪ ደቀ መዛሙርት ስለሆኑ አሁን ትኩረት አድርገው እያጸዷቸው የሚገኙት በዚህ ምክንያት ነው።
አሁን በቅርቡ የዜማና የቅኔ መምህር የማኅሌቱ ጌጥ የነበሩ የኔታ ገብረ መድሕን ትኩየ ከሦሥት ተማሪዎቻቸው ጋር በአማራ ክልል ጥሙጋ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በምትገኝ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያ ውስጥ ባለ የጉባኤ ቤታቸው ውስጥ ንጋት እያስተማሩ ባሉበት በድንገት ተገድለው አድረዋል።
የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም የካቲት 28/2017 ዓ.ም በጥሙጋ ደብረ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተፈጸማል።
በመቀጠልም የእሳቸው ኀዘን ሳይውል ሳያድር በ3ኛው ቀን የካቲት 30/2017 ዓ/ም ሌሊት በጥሙጋ ደብረ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ያለው የቅኔ ጉባኤ ቤትን በእሳት አቀጥለውታል። ስለዚህ ከዚህ አረመኔ የብልጽግና ስብስብ አማራውን እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማን ይታደጋቸው?
መፍትሄውም አንድ እና አንድ ብቻ ነው። ይሄውም ያለበደሉ ስለሚገደለው የአማራው ሕዝብ እና በእሳት ስለምትቃጠለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ህልውና ሲል የሚጋደለውን ፋኖን በሀሳብ እና በገብዘብ እንዱሁም ወዘተ….በመሰለው ሁሉ መደገፍ ነው! ጎበዝ የተኛህ ተነሥ! የፈራህ ጀግን! በልቶ ሳይጨርስህ አውሬውን አስወግድ!
እግዚአብሔር ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና አማራውን ነጻ ያውጣ።