በሰሜን አሜሪካ ትልቋ የኢትዮጵያ ጋዜጣ ዘ-ሐበሻ እነሆ ቁጥር 60 ለንባብ በቅታለች።
እንደተለመደው በውስጧ የያዘቻቸውን ቁምነገሮች እፍታውን እናጨብጣችሁና ንባቡን ለናንተው እንተወዋለን።
* ዓብይ ትኩረታችን ያደርግነው በአውሮፕላኑ ጠለፋ ዙሪያ ነው። የተለያዩ ጉዳዮች ተዳሰዋል።
– ከአውሮፕላኑ ጠለፋ ባሻገር የፖለቲካ ይዘት አለው
– አውሮፕላኑን የጠለፈው ኃይለመድህን አበራ ተገኝ ማን ነው?
– የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የዜጎች እኩልነት አለመረጋገጥ፣ በሥራ ቦታ ላይ ነጻነት ማጣት፣ የኢኮኖሚ ችግር፣ የነፃነት እጦት አውሮፕላኑን አስጠለፈው
– የረዳት ፓይለቱ ድርጊት የአፈናው ውጤት?
– የኢትዮጵያ ነገርና – የአብራሪው ጉዳይ የሚሉ ወቅታዊ ዘገባዎችን ይዘናል።
* በወሩ ታላቅ ዜና አምዳችን፡ የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ “ኢትዮጵያዊነት-”የለህም ይሉኛል፤ እውን የለህም ወይ?” በሚል የፃፈውን ወቅታዊ ትንታኔ ይዘንላችኋል።
* ከሚኒሶታ የጤና ማዕከል ጋር በመተባበር በምናቀርበው አምዳችን ‘ስለ ክትባቶች እና ስለ እርግዝና ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች” የሚል ትንታኔ ይዘናል፤ ቢያነቡት ይጠቀማሉ።
* አዲሱን የNYPD (የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት) ስማርት ካር ውስጡ ምን እንዳለው ሰምተዋል? – ሊያመልጥዎ አይገባም።
* በሕይወት በአሜሪካ አምዳችን፡ ሥራ ፍለጋ ኢንተርኔት ገብቼ ፌስቡክ ላይ ተሰጥቼ እውላለሁ የሚል ትዝብታዊ ጽሁፍ አካተናል።
* ተወዳጁ ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ (ያምቡሌ) በሚኒሶታ ሥራዎቹን ማርች 15 ያቀርባል
* ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “የመረረው አብዮተኛ (ለ1966ቱ አብዮት 40ኛ ዓመት ማስተዋሻ)” በሚል የፃፈው መጣጥፍም የቁጥር 60 ዕትማችን አካል ነው።
በወንጀል ዜና አምዳችን፦
– 3 ልጅ የወለደችለት ሚስቱን በጥርጣሬ የተነሳሕይወቷን አጠፋ
– በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ የታክሲ ሾፌሩን ተሳፋሪው ገደለው የሚሉ ሁለት ዜናዎችን ይዘናል ትንታኔ አላቸው።
በእንመካከር አምድ 4 ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
– “ከባለቤቴ ጋር ስምምነት መፍጠር ተሳነኝ፤ እባካችሁ አንድ በሉኝ”
– ከድብርት ለመላቀቅ ወሲብ ማድረግ ቢነገረኝም እርሱም አልረዳኝም
– ጉሮሮዬ ከተዘጋ 10 ዓመት ሆነው
– በዱካክ ተሰቃየሁኝ፤ ምን መፍትሄ አላችሁ? ምላሾቹን ያንብቧቸው፤ ይማሩባቸዋል።
* በጤና አምዳችን 3 ጉዳዮች እንደተለመደው ተካተዋል።
– ፕሮቴስት የወንዶች ብቻ ችግር (ወንዶች ልብ ብላችሁ አንብቡት)
– ትራኮማ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ
– የነስር ነገር – Epistaxis ፦ ለምን ይነስረናል? የሚሉ 3 ምርጥና አስተማሪ ዘገባዎችን አካተናል ያንብቡን።
* በሴቶች አምድ፡ ማስካራ ትጠቀሚያለች? እንግዲያውስ ይህን አንብቢ ትለናለች ሊሊ ሞገስ፤ ያንብቡላት።
* በሳይኮሎጂ አምዳችን፤ ቅናት ለፍቅር ምኑ ነው? የሚል ቆንጆ ዘገባ አለን።
* በስፖርት አምድ እንዳስለመድነው 3 ጉዳዮች አሉን።
– ፍሌቸር በቀን እስከ 30 ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይመላለስ ነበር
– ማርቴሳካር፡ ግዙፉ ጀርመናዊ
– ጋሪ ኩክ የማንቸስተር ሲቲው አዳኝ
በዘ-ሐበሻ ቁጥር 60 ላይ እነዚህ ብቻ አልተካተቱም፤ በርከት ያሉ ዘገባዎች ከማስታወቂያዎች ጋር ታጅበው ቀርበዋል። ያንብቡ።
ጋዜጣውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ