በአዲስ አበባ የሩዋንዳ ኤምባሲ የጥበቃ ሰራተኛ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ጥበቃ ላይ እያለ ተገደለ

November 26, 2019

የሩዋንዳ ኤምባሲ ጥበቃ የሆኑት አቶ ሸረፋ በጥበቃ ላይ እንዳሉ በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። የኤምባሲው የሴኩሪቲ ኃላፊ ሚስተር ጆን በነበረው ሁኔታ በማዘንና በመበሳጨት “እንዴት በስራ ላይ ያለን ሰው ተኩሳችሁ ትገላላችሁ? ኤምባሲውን ደፍራችኃል” በማለት ፖሊሶች ወደ ግቢው እንዳይገቡ ያደረገ ሲሆን የሟችን ሬሳ ከሌሊቱ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ድረስ ሳይነሳ ቆይቷል። በድናቸው ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል።
በአሁኑ ወቅትም አባዲና ቦታው ላይ መጥቶ ምርመራ እያከናወነ ይገኛል። የአዲስ አበባ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በብዛት ቦታው ላይ ይገኛሉ።

ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ

Previous Story

የሕብር ሬዲዮ ሕዳር 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ፕሮግራም

Next Story

የአቋም መግለጫ – ኢትዮጵያን የዘመናችን ጽንፈኞችና ጎሰኞች እንዲያፈርሷት አንፈቅድም!

Go toTop