የመኢአድ አመራር መንገድ ላይ ሞቶ ተገኘ

August 11, 2014

በኮልፌ ክፍለከተማ የመኢአድ አመራር እና ይፋይናንስ ጉዳዮች ሃላፊ የነበረው አቶ ዳኜ አለሙ በዛሬው እለት ከመንገድ ላይ ሞቶ መገኘቱን እና ሬሳው ምንሊክ ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ የድርጅቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።
ነዋሪነቱ በዘነበ ወርቅ አከባቢ የሆነው አቶ ዳኜ ከመንገድ ላይ ሞቶ የተገኘ መሆኑን እና ዳግማዊ ምንሊክ ሬሳው እንዳለ የተነገረው መኢአድ የድርጅቱን አመራሮች ወደ ሆስፒታሉ ቢልክም የምርመራ ውጤቱን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለነገ ጠዋት በመቅጠር አመራሮቹን አሰናብተዋል።
በዚህ አመት ብቻ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከአዲስ አበባ አመራሮቹ ውስጥ የአቃቂ ክፍለ ከተማ አመራር የነበሩት እንዲሁ ሞተው የተገኙ ሲሆን የምርመራ ውጤታቸውን ለማግኘት ብዙ እንደተለፋ ይታወሳል። እንዲሁም በተለያዩ ክፍለሃገራት ያሉ የመኢአድ መዋቅሮችን ለማፈራርረ ክመግደል ጀምሮ እስር ድብደባ እና ማግለል እየተፈጸመባቸው ነው።ወያኔ መኢአድን አዳክሞ ጠንካራ የተባለ መዋቅሩን ለማፈራረስ ከምርጫው በፊት ብዙ እየሰራ መሆንን ይታወቃል።

Previous Story

የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት ለማጨናገፍ ችኮላው ለምን?

Next Story

በነኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላይ የተፈጸመውን ግፍ ”በአፓርታይድ ጊዜ እንኳን ያልተፈጸመ” በማለት ዳኛው መኮነናቸው ታወቀ ‪

Go toTop