Español

The title is "Le Bon Usage".

የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች!

ቀን የካቲት 2017
በአንዳርጋቸው ጽጌ


ክፍል ፡ 9 ወዳጅ ማብዛት ጠላትን መቀነስ፤ የአማራ ስትራተጂ

እንኳን ለህልወናው መከበር የሞት የሽረት ትግል የሚያደርግ የአማራ ህዝብ ቀርቶ፣ በሁሉም ዘርፎች ማንም አይገዳደረኝም የሚል ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቴክኖሎጂያዊ አቅም አለን የሚሉ ሃያላን መንግስታት ሳይቀሩ ወዳጅን መብዛት ጠላትን መቀነስ የሚል ስትራተጂ አላቸው። በአማራ ህዝብ እንቅስቃሴ ውስጥ፣ ትግሉን በሃገር ቤት የሚመሩትም ፋኖዎች ይሁኑ እነሱን እንደግፋለን የሚሉ በውጭ የሚገኙ አካላት ይህን መሰረታዊና ለህልወና ትግሉ ወሳኝ የሆነን ጉዳይ የተረዱት አይመስልም።

ትልቁ የአማራ ህዝብን ለድል የሚያበቃው፤ በአማራነቱ ለዘመናት ጥቃት ሲደርስበት የነበረውን አማራ በአንድ ጠንካራ አደረጃጅት በጋራ እንዲሰባሰብና በጋራ እንዲታገል ማድረግ ነው። ይህ እውነታ በአፋጣኝ መሬት ላይ ባሉ የፋኖ አካላት መሃከል መግባባት ተፈጥሮ አንድ ወጥ የሆነ የጋራ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር እንዲፈጠሩ የሚጠይቅ ነው። ይህ ጉዳይ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ እየታወቀ፣ ሁሉም ፋኖዎች ሁሉን ነገራቸውን እርግፍ አድርግው፣ የአማራን ህልውና ለማስከበር በርሃ እንዳልገቡ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በፋኖ መሪዎች መሃከል አደባባይ መውጣት የቻለ ስም መጠፋፋትና መዛዛት እያየን ነው። ይህ አደገኛ አዝማሚያ በጊዜ ካልታረመ በህልውና ትግሉ ላይ ትልቅ መዘዝ ማስከተሉ አይቀርም።

የሃገር ቤት የፋኖ አመራሮች በአፋጠኝ የጋራ አመራር መስረተው የአማራን ህዝብ ለከፍተኛ እልቂትና ስቃይ የዳረገውን አገዛዝ ለማስወገድ ማድረግ የሚገባቸውን እንዳያደርጉ በውጭ ሃገር ተቀመጠው የልዩነትን አጀንዳ የሚገፉ፣ ገንዝብና ሚድያ ያላቸው አካላት ድርጊታቸው በመከረኛው የአማራ ህዝብ ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን ከባድ መዘዝ ተረድተው ወደ ቀልባቸው ሊመለሱ ይገባል።\

በትግል ወቅት ስራ ላይ ከሚውሉ ስትራተጂዎች መሃል የጠላትን ካምፕ እገዛና ድጋፍ ማሳነስ፣ የራስን ካምፕ እገዛና ድጋፍ ማሳደግ የሚለው ስትራተጂ ይገኝበታል። በዚህ አኳያ የአማራን የህልውና ትግል የሚጎዱ በርካታ ስህተቶች ሲፈጸሙ ይታያል። ከእነዚህ ስህተቶች አንዱ የአማራ ጠላቶች ከሆኑ ካምፖች ትግሉን ለመደገፍ የሚመጡ ግለሰቦችን ማስበርገግ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ትግሉ ሊከተለው የሚገባው ስትራተጂ የመጡትን ማስበርገግ ሳይሆን ከጠላት ጋር አብረው የሚሰሩትን “ኑ ተቀላቅሉን እናት አባታችሁን ከሚገድል ጨፍጫፊ ጋር እንዴት ትተባበራላችሁ? እጃችን ዘርግተን እንቀበላችኋላን” የሚል ቅስቀቃሳ በማድረግ ወደ ትግሉ መሳብ ነው። ሲመጡም በሙሉ ወገንተኛነት ማስተናገድ ነው።

ሌላው መታወቅ ያለበት ጉዳይ በትግል ወቅት ሁሉም ሰው እኩል የትግል አስተዋጽኦና የሚከፍለው መስዋእትነት እንደማይኖር ነው። መሬት ላይ ያሉ ፋኖዎች በህይወታቸው ይከፍላሉ። ሌላው ከእለት ጉርሱ ከፍሎ ፋኖን በመመገብ ይከፍላል። ሌላው ካለው ዳጎስ ያለ ሃብት ከፍ ያለ ድጋፍ ያበረክታል። የሌለው እንደ አቅሙ። አንዳንዱ ደግሞ በጉልበት ይረዳል፤ እቃ በማመላልስ። ሌላው መረጃ በመስጠት ይተባበራል። ከዛም አልፎ ከጠላት ጋር ባለመተባበር መተባብር ይቻላል። እነዚህ የትብብር አይነቶች በመጠናቸው ቢለያዩም ለትግሉ የየራሳቸው አስተዋጽ አላቸው። ታጋይ፣ የአንተ ድጋፍ ትልቅ ነው ያንቺ ድጋፍ ትንሽ ነው ብሎ ድጋፎችን አያበላልጥም። ድጋፍ ትንሽ ስለሆነ አያጣጥልም። ሁሉንም አመስግኖ ይቀበላል። እዚህ ላይ የሚሰራ ስህተት ሳላለ መስተካከል አለበት። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ አማሮች በትንሹ ቢያዋጡ ጥቂት ሃብት ካላቸው ግለሰቦች እጅግ የላቀ ሃብት ፋኖ ማሰባሰብ እንደሚችል ማወቅ አለበት። ለህልውና ትግሉ መሳክትም ስር ህልወናን ለማጽናትም፣ ብዙሃኑ “የአቅሜን እያዋጣሁ ነው” ብለው የትግሉ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርገው አካሄድ የተሻለው አካሄድ ነው።

ሌላው ከፋኖዎች የጋራ አመራር መፍጠር በመለስ የአማራው የህልውና ትግል የሚሳካው በራሱ በአማራ አጠቃላይ ማህበረሰብ ውስጥ በሚፈጠርው የመንፈስና የድርጊት አንድነት ነው። ዛሬ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝም ለማስወገድ ሆነ ነገ በቦታው ሊተካ የሚችል አዲስ መንግስት የአማራን ጥቅም አስከባሪ እንዲሆን ማድረግ የሚቻለው ስፋት ያለው የማህበረስብ ክፍል በተደራጀ መንገድ ትግሉን እንዲቀላቀል፣ እንዲደግፍ በማድረግ ብቻ እንጂ በሰበብ አስባብ እንዲመናመን በማድረግ አይደለም። ዘመኑ ብዙ ትእግስት የሚያስጨረሱ የራሱ ፈተናዎች ይዞ መጥቷል። በወገን መሃከል ያለን ልዩነት በብልሃት በትእግስት ማስተናገድ፣ ለፍረጃ ለመለያይት መጣደፍን ማስቀረት ያስፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአማራውን ስቃይ ከሚያራዝሙ ጉዳዮች አንዱ ከአገዛዙ ጋር በመተባበር የአማራን ህዝብ የህልወና ትግል የሚገደረደሩ አካላት መኖራቸው ነው። እነዚህን አካላት ከፍተኛ ጉዳት እያመጡ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። እነዚህን አካላት አምሮ መታገል ተገቢ ነው። ሆኖም ግን እነዚህ አካላት በጅምላ የአማራ ጠላት አድርጎ ማቅረብ፣ የሚደግፉት መንግስትዊ አገዛዝ ሲወድቅ ዋጋቸውን እንደሚያገኙ፣ ከብልጽግና ውጭ ህይወት እንደማይኖራቸው አድረገው እንዲያስቡ የሚያደርግ ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨት፣ ትግሉን ለማገዝ ፍላጎት የሚኖራቸውንም የሚያደፋፍር አይሆንም። እንኳን መሃከለኛና እና ዝቅተኛ የብልጽግና የሲቪል ባላስልጣናትና ወታደርዊ መኮንኖች ቀርቶ፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ጄነራሎችና ሚኒስቴሮችም “የአብይ አህመድ ነገር በቃኝ” ብለው ቢመጡ፣ የአማራ ታጋዮች እጃቸውን ዘርግተው እንደሚቀበሏቸው ደግመው ደጋግመው መግለጽ አለባቸው። እንዲህ አይነቱን አሰራራ ከደካማነት መገለጫ ጋር ማስተሳሰር ስህተት ነው። ጠላትን ተዋግቶ ከማሸነፍ፣ ሳይዋጉ በፕሮፓጋንዳ ማሸነፍ የተዋጣለት አዋጊ መገለጫ ነው። የሰው የቁሳቁስ፣ የጊዜ ኪሳራ ሳይበዛ ድል ማግኘት ማለት ነው።

የመንግስት ባላስልጣናት ስርአቱን ክደው፣ መረጃዎችን፣ እና ቁሳቁሶችን ገንዝብ ይዘው ፋኖ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ሊደርግላቸው ይገባል። የአብይ ተላላኪ የሆኑ የብልጽግና አማሮች ከአብይ ጋር የተለጠፉት ክሆዳቸው ውጭ ሌላ ምክንያት ኖሯቸው አይደለም። ትግሉን የማይደገፉት አብይ ለአማራና ለኢትዮጵያ ህዝብ የተሻለ ራእይ አለው ብለው እንዳልሆነ የታወቀ ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን አማራ ሌላውም ቢሆን አብይን በራእዩ ብሩህነት የሚደግፈው የለም። ለአብይ የሚሰጥ ድግፍ ከስልጣን እና ጥቅም ፋላጎት የሚመነጭ ነው። ሁሉም ሆዳም አንድ አይነት ሆዳም አለምሆኑን አውቆ ከሆዳሞቹም መሃል ወደህሊናው ለመመለስ ለሚፈልገው የማሪያም መንገድ መስጠት ያስፈልጋል። የእነዚህ የአብይ ተላላኪ አማሮች ዘመዶች ወንድም እህት የአባት እናት አጎትና አክስት ክሰፊው የአማራ ህዝብ ጋር ስቃይና መከራ ውስጥ መኖራቸው የማይቀር ነው። ሌላው ቢቀር በቅርብ ዘመዶቻቸው ስቃይ የተነሳ ድርጊታቸው የሞራል ጫና ሊፈጥርባቸው የሚችሉ ተላላኪዎች ሊኖሩ እንድሚችሉ መታወቅ አለበት። ትናንት አብይን ሲያገለግሉ ከነበሩ መሃል ዛሬ ትግሉን የተቀላቀሉ እንዳሉ ሁሉ ነገም የሚቀላቀሉ ይኖራሉ። “የሞራል መቆጥቆጥ የሚሰማኝ እኔ ብቻ ነኝ” በሚል መታበይ፣ የሌሎችን በሞራል ጉዳይ የመፈተንን ስብእና አንኳሶ ማያት ተገቢ አይደለም።

በአደባባይ ፋኖን መቀላቀል የማይችሉት ለታጋዩ መረጃዎች በመስጠት ትልቅ ስራ መስራት ይችላሉ። የቀሩትም ስራ በሚገባ ባለመስራት፣ በመለገም፣ በማሻጠር ስርአቱን ክውስጥ እንዲዳከም የሚያደርግ ስራ ሊሰሩ ይችላሉ። እነዚህም ጭምር በአጋርነት መታየት አለባቸው። አንዳንድ የፋኖ ደጋፊዎች ነን በሚሉ ወገኖች እየተደረገ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው። ትግሉን ለመቀላቀልና ለመደገፍ በራሳቸው ፍላጎት ስርአቱን ጥለው የወጡ ግልሰቦችን ማዋከብና ማጥቃት ይታያል። እንዲህ አይነቱ ድርጊት የአማራ ወዳጆች ሳይሆን የጠላቶች ስራ ነው።

በሃገር ውስጥ ከአማራው ማህበረሰብ ውጭ የሚገኙን ቡድኖችን እና ግለሰቦችን በጥንቃቄ በወዳጅነትና በጠላትነት፣ በዋና ጠላትነትና በመለስተኛ ጠላትነት በዋና ወዳጅነት እና በመለስተኛ ወዳጅነት የመመዘን፣ የመፈረጅ ስራ የትግሉ አንድ አካል ነው። በዚህ ፍረጃ ላይ ተመስርቶ የጠላትን አቅም ማዳከም፣ ወዳጆችን የማብዛት ስራ መሰራት አለበት። እንዲህ አይነቱ ጥናት ግን በጥቃቄና በሚስጥር የሚያዝ እንጂ ጠላትና ወዳጆች በሚል በአደባባይ የሚታወጅ አይደለም። ትልቁ ቁምነገር የሁኔታዎች መቀያየር በአንድ ወቅት ከፉ ጠላት ተብሎ የታስበ ግለሰብ በሌላ ወቅት ወዳጅ ሆኖ ሊጠቅም የሚችል አጋጣሚ እንደሚፈጠር ማወቁ ነው። ወዳጅ የተባለው ሊከዳና በጠላትነት ሊሰለፍ ይችላል።

እንዲህም ተብሎ የአማራ የህልወና ትግል የጠላትና የወዳጅ መለኪያው መስፈርት ምንም ይሁን ምን፣ የአማራ ህልውና በቅድሚያ ማስከበር የሚችለው፣ በዲፕሎማሲ ስራ በመስራት፣ የወገንና የጠላት ትንተና በማቅረብ ሳይሆን፣ በክንዱ መሆኑን ማውቅ ይኖርበታል። ወዳጅን በክንድ መደገፍ፣ ጠላትን በክንድ ማድቀቅ የሚያስችል አቅም ሳይኖር ትንተና ማድረግ ወይም በእምነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚገባባት ውል አደጋ እንድሚኖረው ማወቅ ያስፈልጋል። የክንድ ጠንካራነት ወዳጅን ለማብዛት ጠላትንም ለመቀነስ ትልቅ መሳሪያ ነው።

በቀጠናው ላይ የሚሰራ የወዳጅነትና የጠላትነት ትንተና በጥቃቄ ተሰርቶ በጥንቃቄ መያዝና የተግባር መመሪያ ሊዘጋጅለት የሚገባ ነው። ይህ ማለት ሁሌም ሁሉንም እየጠረጠርን በገዛ ጥላችን እየበረገግን እንኖራለን ማለት አይደለም። በሂደት እየተጠናክሩ፣ በከፍተኛ መርህና በተጨባጭ በተሰሩ ስራዎች እየጠበቁ በሚሄዱ ግንኙነቶች ላይ በመመስረት ከተለያዩ አካላት ጋር የሙሉ ወዳጅነት እድገት ደረጃ የሚደርስ የህዝብና የሃገራት ግንኙነት ሊኖር እንደሚችል መታወቅ አለበት። ዘብንና ትጥቅን ሳያላሉ ለወዳጅነት የተከፈተን በር የበለጠ እንዲከፈት መስራት ተገቢ ነው። በአለማችን ውስጥ ከዚህ ቀደም በጠላትነት ሲተያዩ የነበሩ ሃገራት በሂደት በፈጠሩት መልካም ጉርብትና ወደ መልካም ዝምድና ከዛም በአንድ ቤት ወደሚኖር ቤተሰብ የተቀየሩበት አጋጣሚ እንዳለ ማስታወስ ያስፈልጋል።

ዘለቄታነት የሚኖረው የወዳጅነት መሰረት “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚለው መርህ የሚመራ አይደለም። ወይም ነጮቹ አለምን በቅኝ ገዥነት ሲቀራመቱ ያፈለቁትን ከኢኮኖሚና ክወታደራዊ አቅማቸው ጋር የሚሄድን “ሃገራት ቋሚ ጥቅም እንጅ ቋሚ ወዳጅ” የላቸውም የሚል ከኛ ጉስቁል ድህነት፣ አቅመ ደካማነት ጋር የማይሄድ ብሂል ያለምን ጥያቄ ተቀብለን፣ እንደበቀቀን በመድገምና በስራ ለማዋል በመጣር እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። በቀጠናው የሚገኙ ሃገሮች በቋሚ ወዳጀነት መርህ ተባብሮ ከመስራት ውጭ መበልጸግ ቀርቶ ህልውናቸውን ማስከበር እንደማይችሉ መገንዘብ ይገባናል። የነጮቹ “ሃገራት ቋሚ ጥቅም እንጅ ቋሚ ወዳጅ የላቸውም” መርህ እነሱ በቀጠናው ማካሄድ ለሚፈጉት የከፋፍሎ አገዛዝና የዘረፋና የውክልና ጦርነት የሚጠቅም መርዘኛ መርህ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ይህን ለመረዳት የሚያስችል በቂ ጥበብ ያለው የአማራ ልሂቅ በተለይ ከኤርትራ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ከዚህ አቅጣጫ መቃኘት የሚቸግረው እንዳልሆነ እምነት አለኝ። በቀጠናው ከሚገኙ የትኞቹም ሃገሮች በሙሉ ለአማራ የህልውና ትግል መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ የምትችለው ኤርትራ ናት። በፋኖና በኤርትራ መንግስት መሃከል የሚኖረው የቀረበ ግንኙነት ለአማራ የህልውና ትግል መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብዬ አምናለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ በሌላ ክፍል እመለስበታለሁ።

Previous Story

ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ!

Latest from Same Tags

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win