Español

The title is "Le Bon Usage".

ከዋቃ ጉራቻ ወደ ዋቃ ዳለቻ:- የድህነት ወይስ የትንቢት እዳ?

አሁንገና ዓለማየሁ

የነጮች የበላይነት በነገሠባቸው ክፍለ ዘመናት ውስጥ አንድ አፍሪካውያንን የሚያኮራ ነገር የኦሮሞ “ዋቃ ጉራቻ” (ጥቁር እግዚአብሔር) የሚለው የአምላክን ቀለም አገላለጽ ነበር። ኦሮሞ አፍሪካዊና ጥቁር ሕዝብ ሆኖ አምላኩንም ጥቁር ነው ብሎ ማምለኩ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ ፈጠረን የሚለው እና እኛ ጥቁር ከሆንን በአርአያውና በአምሳሉ ደግሞ ከፈጠረን የአምላካችንም ቀለም ጥቁር ነው ማለት ነው ወደ ሚል የተቃለለም ቢሆን አመክንዮአዊ (ሲምፕሊስቲክም ቢሆን ሎጂካል) መደምደሚያ የሚያደርሰውን ሃሳብ ያነገሠ ነበር። አምላክን በአምሳላቸው ፈረንጅ እያደረጉ እየሳሉ ያንንም ስእል በዓለም ላይ በመበተን በሌሎች ሕዝቦች ላይ የስነልቡና የበላይነት ለማሳደር ከመሞከርም ባለፈ ድፍረት ሰይጣንን ደግሞ በአፍሪካዊ ምስል አቅርበው የስነልቡና ስብራት ሲያካሂዱ ለኖሩት ምዕራባውያን “ዋቃ ጉራቻ” ወይም ጥቁር እግዚአብሔር ግሩም ሚዛን አስጠባቂ ነበር።

ታድያ ምን ያደርጋል ጥቂት የኦሮሞ ልጆች መንግሥታዊ ሥልጣንን በጠቀለሉበት ዘመን “ዋቃ ጉራቻ”ን በ”ዋቃ ዳለቻ” ለመተካት ሲጣደፉ ታዩ እንጂ።

መለኮታዊ ጉብኝት?

መቼም ድህነት የማያመጣው ጣጣ የለም። ሥጋን ያሸጣል፣ ነጻነትን ያሳጣል፣ ሃይማኖት ያስለውጣል። “ደሃ አታድርገኝ” ብሎ የጸለየው ማን ነበር? ወሃቢስቱ ዐቢይ አህመድ በጦርነት ድህነት ሲታሽ አንዱን ነጫጭባ መለኮት ብሎ በቅድስቲቱ ሀገር አምጥቶ በተዋህዶም በዋቄፈናም በእስልምናም ላይ ለማላገጥ መገደዱ የሚያሳፍር የታሪክ ቆሻሻ ነው።

ዐቢይ አህመድ ቢል ግራምን መለኮት ብሎ ያምጣው እንጂ አላማው ቢል ግራም የትራምፕ የነፍስ አባት ስለሆነ

“አማላጄ ድንግል አማላጄ” የሚለውን መዝሙር

“አማላጄ ቢል ግራም አማላጄ” ወደሚል ለመቀየር ነው የሚሉም አልጠፉም። የፋኖ ጦርነት ያስከተለበት የዶላር ድርቅ ያመጣበት ጦስ ነው በማለት።

እውነቱ እሱ ነው ወይስ ሐሰተኞች ነቢያት ይመጣሉ የሚለው ትንቢት የግድ ስለሆነ?

እንደዛም ከሆነ ዛሬ የተዋሕዶ አማኝ እንደ እባብ በደረሰበት በሚቀጠቀጥበት ዘመን

‘መለኮት’ ቢል ግራም በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት የተነገረለት ሰው ሆኖ እናገኘዋለን ። እንዲህ ይነበባል።

ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ይህ ሁሉ ነገር የሚሆነው መቼ ነው? የመምጫህና የዓለም መጨረሻስ ምልክቱ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው። ማንም ሰው እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ብዙዎች እኔ መሲህ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ። ብዙዎችንም ያስታሉ። የጦርነት ድምጽና የጦርነት ወሬንም ትሰማላችሁ። ይህ ሁሉ መሆን ስላለበት አትደንግጡ። በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል። ይገድሏችኋል። በስሜም ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጣላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን በመካድ ይሰናከላሉ። አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፣ ሰዎችም እርስ በእርሳቸው ይጣላሉ፣ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ይነሳሉ፣ ብዙዎችንም ያስታሉ፣.. እነሱ ቢቻላቸውስ የእግዚአብሔርን ምርጦች እንኳን ለማሳሳት ታላላቅ ተአምራትና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።

ያም ሆነ ይህ ዓድዋ ባልተከበረበት የካቲት ወር፣ በዚያው በየካቲት በዓድዋ ድል የተመታው መንፈስ በምኒልክ ከተማ በአዲስ አበባ ሠልጥኖ የመታየቱ ጉዳይ ድሉ የተቀለበሰበትን መጠን አመላካች አድርገን ማየት ይገባናል።

ክርስቶስ መጥምቁ ዮሐንስን መንገድ ጠራጊ አድርጎ እንደመጣ “መለኮት” ቢል ግራምም ዐቢይ አህመድን በእሳትና በደም እያጠመቀ መንገድ እንዲጠርግለት አድርጎ መከሰቱን ልብ ይሏል። ጌታንና ሎሌን በአግባቡ መለየት ይበጃል ለማለት ነው።

 

2 Comments

  1. ከላይ የተመለከቱት ናቸው የኢትዮጵያ አስተዳዳሪዎች? ወይ እርግማን

  2. ነገርየው የሰው ጉብኝት እንጂ መለኮታዊነት የለውም። ግራም ነፈሰ ቀኝ የጻሃፊውን ሃሳብ ለመጨበጥ ግን ተቸግሬአለሁ። ቅድስቲቷ ሃገር ማን ናት? ኢትዮጵያ? የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር ይላሉ። ወይም ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነው እንጂ አንዲትን ሃገር ቅድስ የሚያስብላት በውስጧ የሚኖሩት ሰዎች ናቸው። ሰው እንደ አውሬ ከመንገድ ጠብቆ የሚገድሉ እቡያን ባሉበት ሃገር ላይ ስለ መቀደስ ማውራት መወሽከት ነው። የኋላና የአሁን ታሪካችን የመጠፋፋት ታሪክ ነው። ድሃ አደጎችና አዛውንቶች በግፈኞች በትር በሚወቀጡባት ምድር የተረገመ እንጂ የተቀደሰ ትውልድ የለም። አዎን ሁሉን በአንድ ቀለም አጠቆርከው እንደምትሉ። ልክ ነው። ግፍና መከራ አይቶ ዝምታም ወንጀል ነው። ለእኔ በስልጣን ላይ ሆነው ህዝብን ከሚያበራዩት ታጣቂዎች ይልቅ ዝምታን የመረጠው ህዝብ የበለጠ በደለኛ ነው ብየ አምናለሁ። ነግ በእኔ ይደርሳል ማለት ቀርቶ ማን ነው የሞተው? ማነው የታሰረው? አማራ? ትግሬ፤ ሃረሬ፤ ኦሮሞ ወዘተ እያለን ስው መሆናችን ረስተን በብሄር የሰከርንና በሩቅና በቅርብ እሳት የምንቆሰቁስ ሁላችንም ተጠያቂዎች ነን። ምድራዊውን ተጨባጭ ሰቆቃ አይንን ገልጦ መመልከት ሚዛናዊ ያደርጋል።
    የፈጣሪ መልኩ ጠቆረም ነጣም እኔና አንተ ሌሎችም የምናስብበት ጭንቅላት ተሰጥቷናል። አማላጅም አያስፈልግም። ክፉና ደጉን የሚለይ አንጎል ተሰክቶልናል። ግን ለሚያልፍ ጊዜና ስልጣን፤ ሌላ ለሚበላው ሃብትና ንብረት ወገን ስናሰቃይ፤ በሌሎች እንባ ስንስቅ አሜን የሚሉ ሁሉ የቁም ሙቶች ናቸው። የቢሊግራም ልጅ ሃገር ቤት ሂዶ እንዲህና እንዲያ ማለቱ ለሚቀበሉት መልካም ነው። ለማይቀበሉት ደግሞ የሌላውን መብት ማክበር ግዴታ ነው። ሲጀመር የሌላውን እምነት እያጣጣሉ የራስን ከፍ ማድረግ አይቻልም። መጤ ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው። የኦርቶዶክስ እምነት ከባህር ማዶ የመጣ አይደለም እንዴ? ዝም ብሎ የተወላገደ ታሪክ ይዞ በተወላገደ አመለካከት ነገሮችን ከማየታችን በፊት በጣም ወደ ኋላ ተመልሰን እንጨቱን፤ ባህሩን፤ ነፋሱን፤ ቃልቻውንና ሌላውን ግኡዝ ነገር እናመልክ እንደነበረ መረዳት ተገቢ ነው። ለነገሩ ታሪኩስ ቢሆን እየተመረጠ አይደል የሚጻፈው።
    ሌላው ነጥብ መንግስታት ሃይማኖትን እንደ መሳሪያ እንደሚጠቀሙበት አሁን ላይ በህይወት ያለ የሚረዳውና ያለፈ ታሪክም መዝግቦ የያዘው ነው። የጣሊያን ወታደሮች ወደ ሃበሻ ምድር ለወረራ ሲላኩ የጊዜው ጳጳስ አሳልሞና ባርኮ ነው የላካቸው። እኛን የተለየ የሚያደርገን ሸሁ ከመስጊድ፤ ቄሱና ካህኑ ከታቦቱ ጋር አብሮ ወደ ግምባር ይዘምት ስለነበር ብቻ ነው። ያ ህብር ህዝብ ነው አብሮ እንዳይኖር በሻቢያ/በወያኔ/በብልጽግና ሴራ የተሰራበትና የሚሰራበት። አይ ጊዜ! የብልጽግናው ሚዲያ ” የመለኮት ጉብኝት” በማለት የዘገበው ለፓለቲካ ፍጆታ ታስቦ እንጂ እውነትነት የለውም። አዲስ አበባ ላይ ሰይፍ የያዘ ሁነኛ ፈራጅ መለኮታዊ ሃይል ተላብሶ ቢወርድ የስንቶቻችን አንገት እንደሚቀላ መገመት ቀላል ነው። ግፍ የሚዘንብባት ከተማ! ነጫ አምላኪዎች ሁልጊዜም ከሃበሻ ዶክተር ይልቅ የነጭ ድሬሰር ይመርጣሉና አይፈረድባቸውም የነጩን ጉብኝት መለኮታዊ ብለው ቢጠሩት። በማጠቃለያው ሃይማኖት የግል ሃገር የጋራ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። ማንም ሰው የመረጠውን ማምለክ መብቱ ነው። ግን ያንተ/ቺ እምነት ፉርሽ ነው የእኛ ግን መጡቅ ነው የሚሉን ቱልቱላዎች ራሳቸውን ቢፈትሹ መልካም ይመስለኛል። የሰው ልጅ በድርጊቱ እንጂ በቃሉ ብቻ አይመዘንምና! ለእኔ እልፎች ሲያለቅሱ፤ ግፍና መከራ ሲዘንብ ድምጽ የማያሰማ የእምነት ተቋም እምነት አለው ብዬ አላምንም። ግን ሁሉም ብብሄሩና በዘሩ በተሳከረባት የዛሬይቷ ኢትዮጵያ እንደ ጅል ኑሬና በልቼ ልኑር የሌላውን ሰቆቃ አታሰሙኝ የሚሉ በተበራከቱባት ሃገር ሰውን ከእውነት ጋር ለማስታረቅ አስቸጋሪ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች!

Next Story

የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች!

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win