![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2022/02/273474042_10159758118516411_6693056935331202885_n.jpg)
የህወሓት ንብረት በሆነው በድምጺ ወያኔ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የቀረቡት የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች በክልሉ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ከዋናው ጠቅላይ ቤተ-ክህነት የተለየ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ለመመስረት መወሰናቸውን ተናግረዋል።
የሃይማኖት አባቶቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በትግራዩ ጦርነት ለፌደራል መንግሥቱ ወግናለች ሲሉ ከሰዋል። ከዚህ በተጨማሪም ‘በትግራይ ሰዎች ሲገደሉ፤ በተቋማት ላይ ውድመት ሲደርስ ቤተ-ክህነቱ ጦርነቱን አላወገዘችም፣ ይቁም አላለችም’ ብለዋል።
በዚህም ምክንያት “የፈረሰውን ለመጠገን እና ሕዝብን ለማጽናናት የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን መመሠረት አስፈልጓል” ብለዋል የሃይማኖት አባቶቹ።
ይህ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ውሳኔ የተሰማው፤ የሃይማኖት አባቶቹ ከህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር መገናኘታቸው ከተዘገበ ከቀናት በኋላ ነው።
ድምጺ ወያኔ ከአራት ቀናት በፊት ማለትም ጥር 27/2014 ዓ.ም. በዘገባው የህወሓት ሊቀ መንበር እና የሃይማኖት አባቶች በተገናኙበት ወቅት፤ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)፤ “የትግራይ ሕዝብ ተጠቃ ማለት የትግራይ ቤተ ክርስትያን ተጠቃች ማለት ነው” ስለማለታቸው ዘግቧል።
ይህ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት የተለየ ሌላ ቤተ-ክህነት የመመሠረት ጥረት ሲደረግ ይህ የመጀመሪያ አይደለም። ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለመመስረት ጥረት ሲደረግ ነበር።
ከ15 ወራት በፊት በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ ተቀረው የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተስፋፋው ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳቶችን አስከትሏል።
በጦርነቱ ሳቢያ በእምነት ተቋማር ላይ ውድመትና ተዘፈፋ መፈጸሙ በተለያዩ ጊዜያት የተዘገበ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎችም በእምነት ተቋማት ውስጥ መገደላቸውን የእምነቱ ተከታዮች ይናገራሉ።
የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመመስረት ውሳኔን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የፓትሪያርኩ ጽ/ቤት አስተያየት ለማግኘት ቢቢሲ ያደረግነው ጥረት አልተሳክም።
የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የፀሎት እና ምህላ በማወጅ ሰላም እንዲወርድ ጥሪ ስታደርግ ቆይታለች።
ከዚህ ባሻገር የትግራይ ሀገረ ሰብከት ከዚህ ቀደም ጦርነቱን በማውገዝ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ የመድኃኒት እና የምግብ እጥረት በመከሰቱ የሰዎች ሕይወት እያለፈ መሆኑን ገልጿል።
በሌላ በኩል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ግንቦት 2013 ላይ ተቀርጾ በወጣ ቪዲዮ ላይ ስለትግራይ እንዳልናገር “ድምጼ ታፍኗል” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስርስትያን ፓትርያርክ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ጦርነት “የአረመኔነት ሥራ” በማለት ጠርተው ብዙ ጊዜ በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት ፈቃድ መታገዱን ተናግረው ነበር።
ይህ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያ ንግግር በፈረንሳዩ የዜና ወኪል የተቀረጸ ሲሆን ፓትሪያርኩ በቪዲዮው ላይ በትግራይ ክልል ስላለው ግጭት እና ስለሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲናገሩ ተሰምተዋል።

BBC Amharic እነደዘገበው