እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን!! ጄነራል አበባው ታደሰ

November 25, 2021
ኢትዮዽያ እየሞትን የምናስቀጥላት እናት ሀገራችን ናት። ይሄ ከአባቶቻችን የወረስነው እውነተኛው ማንነታችን ነው።
ለአማራ፣ ለአፋር እንዲሁም በአጠቃላይ ለመላው የኢትዮዽያ ህዝብ የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር ‘ኢትዮዽያን አፈርሳለሁ!’ ብሎ በአደባባይ ተናግሮ የተነሳው ጠላታችን ግብአተ መሬት በቅርቡ ይጠናቀቃል።
ሆኖም ግን የአሸባሪው ፕሮፓጋንዲስቶች እና የእርሱ ተላላኪ ባንዳዎች በሚነዙት ወሬ ባለመሸበር እንዲሁም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሙያዊ ክህሎት ሳይኖራቸው ከሀሰተኛ መረጃዎች ተነስተው ያልተገባ አስተያየት እና ነቀፋ ለሚሰጡ ቡድኖችና ግለሰቦች ጆሮ ሳትሰጡ በውስጣችን የተሰገሰጉ የአሸባሪው ተላላኪዎችን እና ባንዳዎችን በመያዝ፣ አካባቢያችሁን ከአሸባሪዎች በመጠበቅ እና ከሰራዊቱ ጀርባ ደጀን በመሆን የጀመራችሁትን ድጋፍ አጠናክራችሁ በመቀጠል ሞራል ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን!
ጀግናው ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
የጦር ኃይሎች ም/ኢ/ሹም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተጠርጥረዋል በሚል ላለፉት 2 ዓመታት ከ6 ወራት የታሰሩት የጦር መኮንኖች በህልውና ዘመቻው ምክንያት አቃቢ ህግ ረዥም ቀጠሮ እንዲሰጥ መጠየቁን ተቃወሙ

Next Story

መዳረሻውን በእንግሊዝ ኤምባሲ ያደረገው “በሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያ ሕዝብ” አስተባባሪነት የተጠራው ሰልፍ

Go toTop