![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2021/10/Debre-birhan.jpg)
ደብረብርሃን ከተማ ከተወሰኑ ሰዎች በስተቀር ከተማውን የሚመሩት በህወሓት ዘመን የተሾሙ ሰዎች መሆናቸው ሀቅ ነው ።
ህወሓት ማይጨው ስትገባ ሰው እየሸሸ ወልደያ … ደሴ ድረስ መጥቷል እነሱም የሸሸውን እየተከተሉ ያለውጊያ ደሴ ደርሰዋል ከዚህ በኋላ ወዴት ነው መሸሻው ?
እንዴት ሰው በወሬ ሀገሩን ለቆ ይሸሻል ?
የምመክርህ ሸሽተህ የምታመልጥበት ጥግ የለም ለቀህ የመጣኸውን ቀየህን ታግለህ አስመልሽ ነው ።
በጠላት ውሸት የሚሸሸው ህዝብ ደብረብርሃን ደርሷል ከዛስ ?
እውነቱን ልንገርህ ደብረብርሃን የመጨረሻው የመሸሻህ ጥግህ ነው ።
ይህንን ብታልፍ የሚቀበልህ ጠላት አለ ።
ትላንት ጥቅምት 20/2014 ዓም ጀምሮ የመከላከያ ልብስ የለበሱ ፈርጣጮች ወይም የህወሓት ሰላዮች ሊሆኑ ይችላሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ደብረብርሃን ከተማ እየገቡ እንደሆነ ስምቻለሁ የደብረብርሃን ህዝብ ካንተ በላይ ላንተ የሚያስብ የለም ራስህን አደራጅተህ ከተማህን ጠብቅ በሽሽት ሰበብ ጠላት ይመጣል የመጣውን ሰው ለይ በአንድ ቦታ አስፍር ።
ሸሽቶ የሚመጣ ወጣት ካለ አትቀበል አብረኸው ወደ ትግል ሂድ በከተማው ውስጥ ያሉ የህወሓትን ሰዎች መንጥረህ አውጣ ገዳዮችህን ከውስጥህ አውጣ ።
ለገሰ ወልደሃና