Hiber Radio: ከቤይሩት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ የዘጠኝ ኢትዮጵያውያን አስከሬን ወደ አገር ቤት ተሸኝቷል

December 2, 2013
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

 የህብር ሬዲዮ ዕሁድ  ህዳር 22 ቀን 2006 ፕሮግራም

<…ዓለም አቀፉ ግብረ ሀይል ቢሮ ከፍቶ በሙሉ ጊዜው በሳውዲ በችግር ላይ ያሉ በየመን በረሃ ላይ የተጣሉትን ለመርዳት እየሰራ ነው።ጉዳዩ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ሲሰራ ቆይቷል። 24 ሰዓት ሙሉ ጊዜውን ለዚህ ተግባር ያዋለ የሰው ሀይል መድቧል። ቢሮ ከፍቷል…በስብስቡ ውስጥ እነ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው፣ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ በርካታ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያ ኢትዮጵያውያን በጋራ እየሰሩ ከየትኛውም የፖለቲካ ፣የሀይማኖት የጸዳ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው…ወደ ሳውዲም ሆነ የመን ለመሄድ ከዓለም ዓቀፍ የቀይ ጨረቃና ቀይ መስቀል ጋር እየሰራን ነው…>

አባ መላ በሚል ስሙ የሚታወቀው አክቲቪስት ብርሃኑ ዳምጤ ለህብር ሬዲዮ ስለ ዓለም አቀፉ ግብረ ሀይል ወቅታዊ እንቅስቃሴ  ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ

<<…በጋዜጠኛ  እስክንድረ ነጋ፣ በርዮት ዓለሙና ውብሸት ታዬ እንዲሁም በፖለቲከኞቹ በእነ አንዷለም ላይ የተወሰነው ውሳኔ ፍትሃዊ ነው ብዬ አላምንም። …>> ወ/ሮ አና ጎሜዝ በአዲስ አበባ ለጋዜጠኛ ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ትርጉሙን ይዘናል)

<<…ኩላሊቱን ለመስጠት ከወሰነ ወደ ወ/ሮ ድንቋ ለማዛወር ራሱን የቻለ ጥልቅ ምርመራ ያስፈልጋል። ያም ሆኖ ካለፈ ቀዶ ጥገናው ከ55 ሺህ ዶላር በላይ ይፈልጋል…>> ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን በቬጋስ ኩላሊቴን እሰጣለሁ ያሉትን ኢትዮጵያዊ ጉዳይ አንስተን ካደረግነው ውይይት የተወሰደ

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

– በሳውዲ በጂዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ኢትዮጵአውያን ተቃውሞ አደረጉ

– ወደ አገራችን ውሰዱ ካሉ የተወሰኑት ታሰሩ

– ከቤይሩት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ የዘጠኝ ኢትዮጵያውያን አስከሬን ወደ አገር ተሸኝቷል

– ለሙስሊሙ መሪዎች ከብይኑ  ቀጠሮ ዋዜማ በሺህ የሚቆጠሩ የእምነቱ ተወካዮች በእስር ቤት ተገኝተው አጋርነታቸውን ገለጹ

– በአገር ቤት ያለው አገዛዝ ለዜጎቹ ሳይሆን ለምዕራባውን የተመቸ መሆኑን አንድ የውጭ ጋዜጣ ዘገበ

– ታዋቂው ኤርትራዊ ድምጻዊ ጸረ መንግስት ዘፈኖችን አቀነቀነ

– በቬጋስ በኦባማ ኬር የታክሲ አሽከርካሪዎችን የኢንሹራንስ ሽፋን እንዲኖራቸው ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Previous Story

አበሻ እና ሆድ – ክፍል 2 (ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

Next Story

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ (ተመስገን ደሳለኝ)

Go toTop