ለሀገራዊ አንድነትና ለውጥ ሲባል በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው የነበሩና ጉዳያቸው በህግ ተይዞ የነበሩ የ63 ተጠርጣሪ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ መደረጉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ጉዳዩን አስመልክቶ ዛሬ ከሰዐት በኋላ በሰጡት መግለጫ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተሳትፎ የነበራቸው ነገር ግን የአመራርነት ቦታ ያልነበራቸው ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል ለጠቅላይ አቃቤ ህግ በተሰጠ ሀላፊነት መሠረት የ63 ሰዎች ክስ የተቋረጠ ሲሆን ተጠርጣሪዎች ደግመው ወደ ድርጊቱ የሚገቡ ከሆነ ግን አቃቤ ህግ ጉዳዩን ዳግም የማየት ስልጣን እንዳለው በመግለጫው ተጠቅሷል።
በዚህ አጋጣሚ ህግ የማስከበሩ ስራ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
ክሳቸው የተቋረጠላቸው 63 ግለሰቦችን ዝርዝር ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ እንደሚያደርግም ጠቅላይ አቃቤ ህግ በመግለጫው ጠቅሷል።
ድልነሳ ምንውየለት
ዛሬ ክሳቸው ከተቋረጠው 63 ግለሰቦች መካከል:
1. አቶ ኤርሚያስ አመልጋ
2. ኮ/ል ቢኒያም ተወልደ
3. አቶ ክርስትያን ታደለ
4. ረ/ፕሮፌሰር ተሰማ ኤልያስ
5. አቶ ሳሙኤል በላይነህ
6. አቶ አዲስ ቃሚሶ እና
7. አቶ አለም ፍጹም ይገኙበታል
Via Sheger Times
በሀሰት ተወንጅለው የተከሰሱትን ለመፍታት በሚል የአገር ሀብት የዘረፉ ትላንትም ስልጣንን ተገን አድርገው ወንጀል ሲሰሩ የነበቱትን መፍታት አግባብ ነው የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው። የእርስዎ አስተያየት ምንድነው!?