Español

The title is "Le Bon Usage".

ዛሬ ምን ማድረግ አለብን ? – 2 ዋና ዋና ጉዳዮች

December 22, 2015

\

ቁምላቸው መኩሪያ

በአሁኑ ሰዓት የኦሮሚያ ልጆች ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ የታጠቀውን የዐጋዚ(ህ ወ ሐ ት) ወታደር በባዶ እጃቸው እዬተፈለሙት ይገኛሉ። ይህ የነፃነት ፍልሚያ ግን ከኦሮሞ ጎሳ(ብሔር) በስተቀር በሌላ ጎሳዎች(ብሔሮች) በኩል ሲከናወን አይተይም። ለምን ?። በእኔ እይታ ይህ የሆነበት በሁለት አንኳር ምክንያቶች ይመስለኛል። እናሱም፦
የኦሮሞ ወጣቶችን ንቅናቄ በጥርጣሬ ዐይን መመልከት።
ህወሐት/ ኢህአዴግ የሚወረውረውን የጎሳ ቅስቃሳ(ፕሮፓጋንዳ) መስማት። የሚሉ ናቸው እላለሁ።

1፡ የኦሮሞ ወጣቶችን ንቅናቄ በጥርጣሬ ዐይን የመመልከት ጉደይ፦

በርግጥ የትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ በሆላ ለራሱ ሥልጣን ማረዘሚያ ሲል የብሔሮችን ቋንቋ ፤ የብሔሮችን ማንነት፤ የብሔሮችን መብት ማስጠበቅ እና የብሔሮችን እኩልነት ማስጠበቅ በሚል በመርዝ በተለወሱ ማር ቃላት እና በወቅቱ የተራማጅ ዘዬ ነው ይባል በተባለው በዋላልኝ መኮነን ይሰበክ በነበረው ጨቅላ የፖላቲካ ምህዋር ማለትም ”የእራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል” በሚል ፍልስፍና የኦሮሞ ጎሳዎችን ቀልብ በመስብ አሌ የማይበል ዕኩይ ተግበር በኢትዮጵያ ህዝብ ለይ ፈፅሞል። ጥቂትም ቢሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ይህንን ጥሪ ተቀብሎ አለስተጋባም ማለት ጋሃዱን መሸሽ ነው።
ነገር ግን“ንጋት እና ዕውነት እዬቆዬ ይጠራል” እንደ ሚባለው ብዙ የኦሮሞ የነፃነት ፓርቲዎች ይህንን አንቀጽ 39 የሚለውን ፈሊጥ በመተው “ኦ ነ ግ” የሚለውን ምህጸረ ቃል ወደ “ኦ ዴ ግ”በመቀየር ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመታግል ገሚሱ ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ቀሪው በኤርትራ ምድርና በአገር ቤት በመሆን የአንድነት እና የነፃነት ትግሉን ከትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን እጅ ፈልቅቆ ለመውሰደ በፍልሚያ ለይ ነው።
አሁን ትግሉ መሆን ያለበት “ከህወሀት” ውጅንብር ወጦ የኦሮሞ ልጆችን ተቀላቅሎ ኢትዮጵያን ከባርነት ማውጣት ነው። ” ኦሮማይ” !!!

2፡ ህወሐት/ኢህአዴግ የሚወረውረውን የጎሳ ቅስቃሳ(ፕሮፓጋንዳ) መስማት፦

አሁን ኢትዮጵያን እዬገደለና ንብራቷንም እዬዘረፈ መሬቷንም ለባዕድ ሀገር እዪናኘ ያለው የትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን ልክ እንደ አመንምኒት(ኤይድስ) በሽታ ብዙ ገጸበህርያት አለው።
ይኸውም ምንጩ ከሆነው ትግራይ ክ/ሀ ሲደርስ” ህወሐት” ይሆናል። ጎጃም፡ ጎንደር፡ ወሎ እና ከፊል ሸዋ ክ/ሀገሮች ሲደርስ “ብአዴን” ይሆናል። ኢሉባቦር፡ ባሌ፡ ወለጋ፡ካፋ ፡ አሩሲ፡ ከፊል ሓረር እና ከፊል ሸዋ ክ/ሀገሮች ሲደርስ “ኦህዴድ” ይሆናል። ሲደሞ እና ጋሞጎፋ ክ/ሀገሮች ሲደርስ “ደህዴን” ይሆናል። ሐረር ሲደርስ “አዴን” ይሆናል። አፈር ሲደር “አዴግ” ይሆናል። ጋምቤላ ሲደርስ “ጋዴድ” ይሆናል። አሶሳ ሲደርስ “ቤጉዴድ” ይሆናል። (ብቻ ምን አለፋችሁ የጎሣውን ስም እዬጠረ ከሆለው “ዴ”ን (ዴሞክራሲን)ወይም “ድ”ን(ድርጅትን) መሽለም ነው።
እናዚህ ሁሉ ከላይ የተዘረዘሩት የህወሐት ሎሌዎች ደግሞ በሥሮቻቸው ሊግ፤ፎራም፤ወጣት ማህበር፤የፓርቲ አባል የሚባሉ ግልገል ሎሌዎች አሎቸው። የሁሉም ታግባር ግን የህወሐትን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም አንዱን ጎሳ ከሌላው ጎሣ አንዱን ሀይማኖት ከሌላው ሀይማኖት ማጋጨት እና ደም ማፋሰስ ነው።
በተለይ ጎላ ያሉትን የአማራውን ጎሳ ከኦሮሞው ጎሣ፡ የከርስትያኑን ማህበረስብ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማጋጫት እና ደም ለማፋሰስ በራሱም ሆነ በሎሌዎች አማካኝእነት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። ይህንንም አድራጎት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአርምሞ የሚረደው ይመስለኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ጊዜ ጀግኖች ወንድሞቻችን የኦሮሞ ልጆች ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ ዘመነዊ መሰሪያ ታጥቆ የመጠውን የአጋዚ(የህወሀት) ጧር በባዶ እጃቸው ጕሮሮ ለጉሮሮ ታናንቀው ዓረፋ እየስደፈቁት ይገኛሉ።
ስለዚህ ፦ወንድም እና እህት፡ እናት እና አባት የሆነው ሌላው የኢትጵያ ጎሣ(ብሄረስብ) በወየኔ እና በሎሌዎቹ ፕሮፓጋንዳ ሳይፈታ ከኦሮሞ ወንድሞቹ ጎን በመቆም ወንድሞቹን ከሞት ኢትዮጵዮጵያ ከመከራ ሊታደጋት ይገባል።

“ኢትዮጵያ ከእነ ክብሮ ለዘላአለም ትኑር !!!!!”

Previous Story

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

Next Story

በብሩንዲ ውስጥ ያንጃበበው የእርስ በርስ ግጭት ስጋት መንሴዎቹ እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ሰሞነኛ ምላሽ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር) | ሊደመጥ የሚገባ

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win