Español

The title is "Le Bon Usage".

አረና ፓርቲ ተከፋፈለ መባሉን አስተባበለ

August 3, 2014

  አረና ፓርቲ ተከፋፈለ ሲል የዘገበው አፍሪካን ኢንተለጀንስ ዶትኮም፤ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ የተወሰኑ አባላት ራሳቸውን ከፓርቲው እንዳገለሉ ቢናገሩም የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ በፓርቲው ውሳኔ መባረራቸውን እንደገለፀ ትላንት ጠቆመ፡፡ አረና በበኩሉ፤ ፓርቲው ተከፋፈለ መባሉን አስተባብሏል፡፡ በፓርቲው ውስጥ የስነ ምግባር ጥሰት የፈፀሙ አባላት ላይ በፓርቲው ህገ-ደንብ መሰረት የተወሰነ ቅጣት ከመጣሉ በስተቀር ፓርቲው በምንም ሁኔታ የመከፋፈል ችግር ውስጥ አልገባም ሲሉ የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርሄ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

“አባላቱ የዲሲፕሊን ቅጣት የተጣለባቸው የፓርቲውንና የአመራሩን ስም ወደማጥፋትና ወደ አላስፈላጊ አሉባልታ በመግባታቸው ነው” ያሉት አቶ ብርሃኑ፤ እነዚህ የአመራር አካላትና አባላት፣ ፓርቲውን የሚጉዳ ሴራ እንደፈፀሙና በወንጀልም ሊያስጠይቃቸው እንደሚችል በግምገማ መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ “አንድ ተራ አባል፤ የፈፀመው ጥፋት ከፓርቲው እስከማባረር የሚደርስ በመሆኑ የስራ አስፈፃሚው እንዲባረር ወስኖበታል” ያሉት የአረና ሊቀመንበር፤ አንድ የፓርቲው የቁጥጥር ኮሚቴ አባል ደግሞ ጉዳዩ በቁጥጥር ኮሚቴው እንዲታይ ከተደረገ በኋላ ፓርቲው የሚቀጥለውን ጉባኤ እስኪያካሂድ ድረስ ከቁጥጥር ኮሚቴው አባልነቱ ታግዶ እንዲቆይ መወሰኑን ገልፀዋል፡፡

በዲሲፕሊን ጥሰት የተገመገሙ ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጉዳያቸው በማዕከላዊ ኮሚቴው እንዲታይ ከተደረገ በኋላ፣ ሺሻይ አዘናው የተባለው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በፓርቲውና በአመራሩ ላይ ያደረሰውን ስም ማጥፋትና አሉባልታ እንዲያስተባብል የ14 ቀን ጊዜ እንደተሰጠው የጠቆሙት ሊቀመንበሩ፤ ግለሰቡ ከጥፋቱ ሊታቀብ ቀርቶ በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመረ ቢሄድም ውሳኔ ለመወሰን፣ የተሰጠው የጊዜ ገደብ እስኪጠናቀቅ እየጠበቁ እንደሆነ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ “ይሄው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የፓርቲውን ስም ከማጥፋቱም ባሻገር ለሁለት አመት የአባልነት መዋጮ አለመክፈሉ፣ እንዲሁም በተመደበበት ኃላፊነት ላይ በአግባቡ እየሰራ አለመሆኑ በግምገማ ተረጋግጧል” ብለዋል – አቶ ብርሃኑ፡፡

ሌላው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል መምህር ታደሰ ቢተውልኝ፤ በስራውና በፓርቲው ላይ እያሳየ ባለው የስነ-ምግባር ጉድለት ቀላል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው ሊቀመንበሩ ጠቁመው፤ “ለምን ማስጠንቀቂያ ይሰጠኛል” በሚል የፓርቲውን መታወቂያ ቢሮ ጥሎና ተቆጥቶ መሄዱን ተናግረዋል። “የተባረረው ተራ አባልም ቢሆን ዓምና በተደጋጋሚ በፈፀመው ጥፋት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እንደነበር ያብራሩት አቶ ብርሃኑ፤ “ከላይ በተዘረዘሩት ጥፋቶች የተባረሩና ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው የፓርቲው አመራሮችና አባላት “አረና ተከፋፈለ፤ ተሰነጣጠቀ” በሚል በየፌስቡኩና በየዌብሳይቱ ቢያስወሩም ፓርቲው ግን ህግና ደንቡን ተከትሎ በተጠናከረ ሁኔታ ስራውን ቀጥሏል” ብለዋል፡፡ የፓርቲው አባላትና አመራሮች ግለሰቦቹ በሚያስወሩት አሉባልታ መደናገር ሳይሰማቸው ስራቸውን በአግባቡ እንዲቀጥሉም አሳስበዋል – የፓርቲው ሊቀመንበር፡፡

ምንጭ፥ -አዲስ አድማስ

Previous Story

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍ/ቤት ቀጠሮው ለመጪው ዓመት ተቀጠረ

Next Story

በሁለት ካርቶን ታሽጎ ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል የተያዘው ወርቅ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ትዕዛዝ እንዲወጣ መደረጉ ተዘገበ

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win