የካቲት 12 ቀን የፋሺስት ሰማዕታት 80ኛው ዓመት ለምን ትኩረት ተነፈገው? – ሔኖክ ያሬድ

አበው ‹‹ነውን ለማወቅ ነበርን ጠይቅ›› ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከጥቁር ዓለም ልቃ በነፃነት የኖረችበት በቅኝ ገዢዎች በአካል ያለ መንበርከክዋ ምሥጢር የሚቀዳው ከነበር ታሪኳ ለመሆኑ እነዚያው አበው ብሂሉን ማጣቀሻ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከ130 ዓመታት በፊት በአፄ ዮሐንስ አራተኛ ዘመን በዶግአሊ የኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊትን በራስ አሉላ ጠቅላይ አዝማችነት የደመሰሰችበት የመጀመሪያው በአውሮፓ ላይ የተገኘ ድል ነበር፡፡ ከዶግአሊ ዘጠኝ ዓመት ቆይታ በኋላ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ግዙፉን የጣሊያን ወራሪ ሠራዊት በዳግማዊ ምኒልክ ጠቅላይ አዝማችነት ዓድዋ ላይ በድል መደምደሙ በተለይ የጥቁር ዓለም መኩሪያ ለመሆን በቅቷል፡፡ የ40 ዓመት ቂም የቋጠረው የኢጣሊያ ፋሺስታዊው መንግሥት በ1928 ዓ.ም. በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የፈጸመው ወረራ ከአምስት ዓመት የአርበኞች እርመኛ ትግል … Continue reading የካቲት 12 ቀን የፋሺስት ሰማዕታት 80ኛው ዓመት ለምን ትኩረት ተነፈገው? – ሔኖክ ያሬድ