በፖለቲካ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች በቀጣይ በሚደረገው ውይይት እና ድርድር ዙሪያ ከምርጫ ቦርድ ጋር እየመከሩ ነው

January 10, 2019

በፖለቲካ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች በቀጣይ በሚደረገው ውይይት እና ድርድር ዙሪያ ከምርጫ ቦርድ ጋር እየመከሩ ነው። በምክክር መድረኩ ላይም በፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች መካከል ለሚደረገው ውይይትና ድርድር 32 አጀንዳዎችን አቅርበዋል።
https://www.youtube.com/watch?v=ncwpPfdrV3E&t=991s

ፓርቲዎቹ ለውይይት ቢቀርቡ ብለው ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፅሁፍ ያቀረቧቸው አጀንዳዎች በሰባት ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

ሰባቱ ርእስ ጉዳዮችም፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ፣ ምርጫ ቦርድን የተመለከቱ ጉዳዮች፣ ምርጫ 2012 እና የአካባቢ ምርጫ፣ የዴምክራሲ ተቋማትን የማሻሻል ጉዳይ፣ ህገ መንግስት እና ፌዴራሊዝም፣ የውጭ ጉዳይ እና ሌሎች ጉዳዮች ናቸው። በእነዚህ ርእስ ጉዳዮች ላይም 32 የውይይት ወይም የድርድር አጀንዳዎች ተዘርዝረው ቀርበዋል። ከ32ቱ አጀንዳዎች መካከል ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደረግ ድጋፍ፣ ስለ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደት ትብብር ጥምረት፣ የምርጫ ቦርድ አደረጃጀት፣ ምርጫ መራዘም፣ የ2012 ምርጫ፣ ሰላም እና መረጋጋት፣ የፀጥታ እና ደህንነት የግንባታ ማሻሻያ፣ የህገ መንግስት ማሻሻያ፣ የስራ ቋንቋ፣ የአዲስ አበባ ጉዳይ፣ ሰንደቅዓላማ፣ የመንግስት አደረጃጀት እና የክልሎች አደረጃጀት እንደሚገኙበት ሰምተናል:

Previous Story

ባህርዳር ከተማ ሁለት ዓይነት የተቃውሞ ሰልፎችን አስተናግዳለች

Next Story

ጥብቅ መረጃ – ተስፋዬ ኡርጊ: ከበግ ደላላነት እስከ ጌታቸው አሰፋ ዋና ቀኝ እጅነት

Go toTop