ብርጌድየር ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ትላንት በጆንያ ስለተያዘው ሽጉጥ ተናገሩ

January 2, 2019

የአማራ ክልል የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ብርጌድየር ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ የአማራ ክልል የቪአይ ፒ ጥበቃ ሀላፊ መኖሪያ ቤት ስለተገኙት ሽጉጦች መግለጫ ሰጡ፡፡ 

https://www.youtube.com/watch?v=5nRC0uUMz70&t=141s

እንደተናገሩትም የመስተዳድሩ የልዩ ጥበቃ አዛዥ በነበሩት በኮምንደር ዉበቱ ሺፈራዉ መኖሪያ ቤት፣ በሰባት ጆንያዎች ተቋጥረው የተገኙት ሽጉጦች በየሥፍራዉ ሊከፋፈል እና ሊሰራጭ የተቃደ ነበር፡፡ 

ሽጉጦቹ በሙሉ አዳዲስ እና ቱርክ ሠራሽ መሆናቸውን ያስረዱት ብ/ጄ/ል አሳምነው የተያዙትም ጉዳዩን በቅርብ በሚያዉቁ ወገኖች ጥቆማ እና ትብብር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ሽጉጦቹ የተያዘባቸዉ ኮማንደር ዉበቱ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀውም፤ «ባንድ እና በሁለት ሰዉ ይሠራል ብለን እንገምትም» ብለዋል። 

በመሆኑም በአባሪና ተባባሪዎች ላይ ክትትሉ እንደቀጠለ ተናግረዋል፡፡ አንድ የክልሉ ፀጥታ ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣን ይሕን ያክል ጦር መሣሪያ ደብቀዉ መገኘታቸዉን፣ ጄኔራል አሳምነዉ «አሳዛኝ እና አሳፋሪ» ብለዉታል። የክልሉ ቪአይፒ ጥበቃ ሃላፊ መኖሪያ ቤት 498 ሽጉጦች መገኘቱን ትላንት በዘሃበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ብ/ጄ/ል አሳምነው ፅጌ ደም መለገሳቸውን ሰምተናል፡፡

Previous Story

የኢንጂነር ስመኘው አባት “ልጄ ራሱን አጠፋ የሚባለው ፖለቲካ ነው” አሉ

Next Story

“የገዛ ወገኖቼ በቁሜ ቀበሩኝ” – የሚወዷቸውን የተነጠቁ እናት ዋይታ

Go toTop