(የባህር ዳር ከተማ)የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን ሰብስቦ መልስ እንደሚሠጣቸው ቃል ገብቶ እንደነበር ታውቋል፡፡ ነገር ግን በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በለቱ የወጣው የማገጃ ደብዳቤ በፋብሪካው ስራአስኪያጅ አቶ አባይ መላኩ ስምና ፊርማ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል የፋብሪካው ስራስኪያጅ የሆኑት አቶ አባይ መላኩ ሰራቸኞች መባረራቸውን አምነው ቁጥራቸው ግን 5 ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የመባረራቸውን ምክንያትም ቢሆን በተባለው ጊዜ ምንም እውቅና የሌለው ህገ ወጥ የስራ ማቆም አድማ ስላደራጁ ነው ብለዋል፡፡