አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛ ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ ። ዛሬ በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ 806 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ አቡነ ማትያስ 500 ድምፅ በማግኘት ነው ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት
እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 98፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ፣ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ 70፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
98 ድምፅ ሲያገኙ፣ አንድ የድምፅ መስጫ ፎርም ምልክት ሳይደረግበት ተገኝቷል፡፡