80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

January 18, 2025

ከነፃነት ዘገዬ

የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት አብነቶችን ቀጥለን እንመልከት፡፡

  • በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ገደማ አፄ ምኒልክ የፈጁት የኦሮሞ ብዛት ወደ 10 ሚሊዮን ይጠጋ እንደነበር ቀደም ሲል ከተሰራጨ አንድ የኦነግ መግለጫ ተረድተናል፡፡ በወቅቱ ከተሰጡ ትችቶች መካከል አንዱና ዋናው “ለመሆኑ ያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጠቃላይ ቁጥርስ ከዚህ ይዘል ነበር ወይ?” የሚለው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በልኩና በሚያሳምን ደረጃ ቢዋሽ ምን አለበት?
  • ውሸትን በተመለከት አንድ ቆየት ያለ እስታቲስቲካዊ አስቂኝ ታሪክ ጣልቃ ላስገባ – ለፈገግታም ይሆናል፡፡ በዘመነ ደርግ በመንግሥቱ ኃ/ማርያም ፊት ሚኒስትሮች ሁሉ የየመሥሪያ ቤቶቻቸውን ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርቡ ነበር፡፡ የወቅቱ የግብርና ሚኒስትር ታዲያልህ ስለታራሽ መሬት (arable land) ሪፖርት ሲያቀርብ የየክፍለ ሀገሩ ሁሉ ሲደመር የኢትዮጵያን አጠቃላይ የቆዳ ስፋት በልጦት አረፈው፡፡ ከዋሹ አይቀር እንደዚያ ነው፡፡ የሚነገረው እስታትስቲካዊ ቁጥር ይደምር ይቀንስ የነበረው ባለሥልጣንና ሚኒስትር ሁሉ በዚያ ሪፖረት በሣቅ ፈነዳ – መንጌም ጭምር፡፡ አንተም ሣቅ እንጂ!
  • ወደሰሞነኛው ኦነጋዊ የሀሰት ልቃቂት ልግባ፡፡ የአባይ ግድብ 97.6 ከመቶ አልቆ 2.4 መቶኛው ብቻ እንደቀረ በቱልቱላው ለገሠ ቱሉ ከተገለጸ በኋላ ይህን ቀሪ ሥራ ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ያላንዳች ሀፍረት ተነገረ፡፡ ምን ማለት ነው? አጠቃላይ ሥራውን ለመሥራት ያስፈልግ የነበረው 80 ቢሊዮን ብር እንደነበረ ትዝ ይለኛል፡፡ አሁን ባለንበት የብር የመግዛት አቅም መሽመድመድ የተነሣ ብሩ የፈለገውን ያህል ቢወድቅ ሁለት መቶኛውን ለማከናወን እንዴት ነው 80 ቢሊዮን ብር የሚፈጀው? በጭራሽ ሊገባኝ አይችልም፡፡ ይሄ የግድብ ነገር ግራ የሚያጋባ ነው – አቢይ እንደሸጠው የሚነገረውም እውነት ነው፡፡ እሱ ለገንዘብና ለሥልጣን ሲል ሌላ ቀርቶ ልጆቹንም ይሸጣል፡፡ ንጉሥ ሻካ ዙሉ ማለት አቢይ ነው፡፡ የሥልጣን ፍቅር ናላቸውን ከሚያዞራቸው የዓለማችን ዜጎች ቁጥር አንዱ አቢይ ነው፡፡ ስለሆነም ጠ/ሚኒስትር ሆኖ ትልቁን የሥልጣን ማማ ላይ ወጥቶ እንኳን ቀፎ ራስ በመሆኑ በራሱ ስለማይተማመን ከታዘዘ ለአሜሪካና ለራሽያ ሊሰልል፣ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በተለይ አማሮችን በኮንቴይነር ጭኖ እንጦርጦስ ሊከት ይችላል – ሥልጣኑን ብቻ አትንካበት፡፡ አንድ ሰው ባልተገባው ቦታ ላይ ሲገኝ ከዚህ የከፋ የለም እንጂ የባሰም ያደርጋል፡፡
  • እንዲያው ለማስታወስ ያህል ነው፡፡ የአቢይ ችግኞች ይጥደቁ ይድረቁ ሌላ ጉዳይ ሆኖ – ምክንያቱም እሱ መጀመርን እንጂ ተከታትሎ ማስጨረስን አያውቅምና – በእርሱ ሪፖርት መሠረት ሥልጣን ከያዘ ወዲህ ያስተከላቸው ችግኞች 50 ቢሊዮንን እንዳለፉ ነግሮናል፡፡ 50 ቢሊዮን ችግኝ ወንዝና ገደላ ገደሉ፣ ሐይቅና በረሃማው ሥፍራ ተጨምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት በየ5 ሜትር ርቀት ቢተከል ኢትዮጵያ እንደማትበቃ በዘርፉ ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ምን ጉድ ጣለብን ግን?
  • አንድ ኦነግሸኔ ሚኒስትር በዚያን ሰሞን ሲናገር እንደተደመጠው እርሱ የጻፈው ጽሑፍ በኢንተርኔት ተፖስቶ 56 ቢሊዮን ቪው እንዳገኘና ያም ቪው የአሜሪካን ታዋቂ ሰዎችና ፕሬዝዳንቶች በድምሩ ካገኙት ቪው እንደሚበልጥ ወሽክቷል – አንዳችም ስቅቅ ሳይለው በኦነግ ኦህዲዳዊ ድፍረትና ጀብደኝነት ሊያውም፡፡ ይገርማል፡፡ ሲዋሽ እኮ ትንሽ ለከት ቢኖር ውሸቱን የሚቀበል አንዳንድ ሞኝ አይጠፋም፡፡ ይህ ግን የተለዬ ነው፡፡ የዓለም ሕዝብ በሙሉ ያን ጽሑፉን ወይም በድምጽም ከሆነ ንግግሩን ቢያዩለት እኮ ሊኖረው የሚችለው የቪው ብዛት 8.2 ቢሊዮን አካባቢ ነው – የወቅቱ የዓለም ሕዝብ ብዛት፡፡
  • አቢይ በዚያን ሰሞን 124 የመንገደኞች አውሮፕላን ሊገዛ ለአውሮፕላን ፋብሪካዎች ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልፆልናል፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ የኢትዮያን የበጀት ጉዳይና የውጭ ምንዛሬ አቅም የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ 124 ሰው ጫኝ አውሮፕላን!!
  • በኬንያ አንድ አነስተኛ ደሞዝ በኢትዮጵያ በትንሹ ለአሥር ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮች ሊውል እንደሚችል የማይረዱት ቅንጡዎቹ የብል.ግና ሚኒስትሮች የቤንዚን ጭማሪን ትክክለኝነትና ገና እንደሚቀረውም ለማሳመን ቤንዚንን ብቻ ነጥለው ከኬንያ ጋር ለማወዳደር ሲላላጡ ስናይ የእነዚህ ሰዎች ከሒሣብና ከቁጥር ሥሌት ጋር ተቆራርጠው መቅረታቸውን እንረዳለን፡፡
  • አንድ ግም ሰው ትልቅ ቦታ ከያዘ በዙሪያው የሚገኙት ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ ግሞች ብቻ ናቸው፡፡ ለምን ቢባል “ግም ለግም ተያይዘህ አዝግም” ሲል ብሂሉም አስቀድሞ አስቀምጦታልና፡፡ አቢይ እንዳሻው ሊፈነጭበት የሚችል የጦር መኮንንንም ይሁን ሲቪል ባለሥልጣን አእምሮ እንዲኖረው አይጠበቅበትም – ማሰብ የሚችል ከሆነ ይመነጠራል፤ ይባረራል ወይም እንደዬሁኔታው በግድያ ሊወገድም ይችላል፡፡ አእምሮ ካለው “ለምን?” ብሎ ይጠይቃል፡፡ በአምባገነኖች ሠፈር ደግሞ ለምን ብሎ መጠየቅ ለቅስፈት የሚዳርግ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ስለዚህ ያ ሰው በትምህርቱ ማይም፣ በስብዕናው የረከሰና የተጠላ፣ በሞራሉ የበሸቀጠና የዘቀጠ፣ በባሕርይው የወረደ … መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህም ነው ድፍን ምርኮኛ ሁሉ ያሻን ማድረግ በማይታክተው ያበደ ማሙሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄኔራልና ማርሻል እየተባለ ይህን የአጋንንት ውላጅ ለማገልገል ቀን ከሌት ቀና ደፋ የሚለው፡፡ እነዚህ ድፍን ቅሎች ታዲያ ቁጥርም አያውቁም፡፡ ስለዚህም አንዲት ሴተኛ አዳሪ ለአንድ አዳር ሲፈልጉ ከዱባይ ካልፈለጉም ከሞሮኮ በ100 ሚሊዮን ብር በደላሎቻቸው አማካኝነት አስገዝተው ያስመጣሉ፡፡ ሴት ሴት ነው – ወደጎን የተ..ደ የለም፡፡ እዚሁ በጥቂት አሥር ሽዎች መዝናናት ሲችሉ ሚሊዮኖች ጦማቸውን በሚያድሩ በሚውሉባት ድሃ ሀገር እንዲህ ያለ ግፍ በሕዝብ ገንዘብና በሀገር ሀብት ይሠራል፡፡ ይህ እንግዲህ በየቄሮው ሠርግና ምላሽ ጭፈራ ላይ እየተዘራ የሚረጋገጠውንና ተቆጣጣሪም ያጣውን በሚሊዮኖች የሚገመት ብር ሳይጨምር ነው፡፡ በየቀኑ የሚያወጡትን ሕዝብ አስለቃሽና አገር አፍራሽ ህግና ደምብማ አታንሱት!! ጎጋው ዜጋ ምን እንደተዞረበት ሳይታወቅ የለዬለት ከብት ሆኖ ዝም ብሏል፡፡
  • በነዚህ ደናቁርት መገዛት ታዲያ አያናድድም ትላላችሁ? እግዜሩ ምን ያህል ቢቆጣን ይሆን ለነዚህ ጉግማንጉግ በላኤሰቦች አጋልጦ የሰጠን? ግዴላችሁም ራሳችንን እንፈትሽና ወደየኅሊናችን እንመለስ፡፡ ከዚያም በምህላም ይሁን በሱባኤ አምላክን እንጠይቅ፡፡ የሃይማኖት አባትና የአምልኮት ሥፍራዎቻችንንም ሳይቀር ዲያቢሎስ ተቆጣጥሮ ቢጨፍርበትም በየበኣታችን ሆነን ጌታን እንለምን፡፡ ይሰማናል፡፡ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንልን፡፡

 

 

4 Comments

  1. ሰሚ የለም እንጂ ቢኖር ጥሩ ምክር ነው፡፡ ወደፈጣሪ ካልተመለስን እዳችን ሸክማችን ከፍቷል፡፡ እግዚኦ እንበል፡፡ ካለቀስንበት የመከራና ሲቃ ጊዜው ያጥርልናል፡፡

  2. ሰሚ የለም እንጂ ቢኖር ጥሩ ምክር ነው፡፡ ወደፈጣሪ ካልተመለስን እዳችን ሸክማችን ከፍቷል፡፡ እግዚኦ እንበል፡፡ ካለቀስንበት የመከራና ሲቃ ጊዜው ያጥርልናል፡፡በርትተን እንጸልይ

  3. Well and yes, God’ Spirit is anywhere and everywhere to help and bless who deserves to be helped and to be blessed!! And this necessarily requires to be willing and able to live a life of words and actions as a human being created with a very amazing power of thinking and a very capable body structure!!! And that is the very meaning of true believers!!!
    Now, the question is are we really in line with this very essence of religious belief and value??? Or we just believers religious ceremonies and celebrations??

    It must be very clear that Lord of the Truth who created us with full mental and physical capability of protecting not only ourselves but also any human being from any unjust and brutal situation will never hear our action less ( not standing together and fighting against criminal ruling elites but just empty) cry and decry at all!!!
    So, if really want to make a difference, let’s first search our own way of doing things in a wrong way!!! Let’s understand what is powerful and what is powerless !!! Words without action are powerless ,and words of action are powerful in both earthly and heavenly lives!!

  4. አረጋዊ በርሄ አስተባባሪ ሁኖ ይህ ግድብ ተሰርቶ ያልቃል ማለት ዘበት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ሰው ሆይ!

Next Story

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

Go toTop