ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም የተለያዬ ጉዳይ የተነሣ ትግሉ አሁንም የዕንፉቅቂት እየሄደ ብዙዎቻችንንም ተስፋ እያስቆረጠ ይገኛል፤ በዋናነትም የብዙዎችን ታጋዮችና የአማራ ሕጻናትን፣ አረጋውያንን፣ ሰብልንና እንስሳትን ሳይቀር እያወደመ ለሚገኘው ጦርነት መሠረታዊ ምክንያት ከመሆን አልዘለለም፡፡ ይሄ አካሄድ ለዐይን ይበጃል ያሉት ኩል ዐይንን እያጠፋ ስለመሆኑ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ ከእንግዲህ ግን “ያበጠው ይፈንዳ የሚሰማንን ከመናገር ወደኋላ አንልም” የምንል ዜጎች ወደ መድረክ መዝለቅ ይገባናል፡፡ “እንትና እንዳይከፋ፣ እነእንትና እንዳይቀየሙ፣ እንቶኔ እንዳያኮርፍ ወዘተ.” የሚለው ሰበብ አስባብ ሀገርንና ሕዝብን እንጦርጦስ ከማውረድ አላደነም፡፡ አቢይንና የሚመራውን ዐረመኔ የዘረኞች መንጋ አንድም ሳናስቀር በስድብና በዘለፋ እየሞለጭን ሳለን ገና ለገና እገሌ የሚባለው የነጻነት ታጋይ አራት ኪሎ ሲገባ “እንዲህ ወይ እንዲያ ሊያደርገን ይችላል” በሚል ፍራቻ ይመስላል ብዙዎቻችን እየተሸፋፈንን ቆይተናል፡፡ ውጤቱ ግን ያው የምናየው ነው፡፡ “እየመጡ ነው” የሚለው መፈክርም የተነገረበት ቅላጼና የተጻፈበት ቀለም መደብዘዝ ከጀመሩ ቆዬ፡፡ “እየተፈራራን እንጂ…” – አለ ኃይሌ – “ፋኖን ብንተች ቀዳሚው ተጠቃሚ ራሱ ነው” ብዬ ጨመርኩ እኔ፡፡
ለገባንበት ፋኖኣዊ የአደረጃጀትና የአካሄድ ችግር አንድ ልጨኛ ሥነ ቃላዊ ብሂል ባስታውስ ደስ ይለኛል፡፡ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ምናልባት ወጣቶችን ማስታወስ ካስፈለገ ነው የምደግመው፡፡
አንድ ሠነፍ እረኛ በአንድ መንደር ውስጥ በጎቹን አሰማርቶ እየጠበቀ ሣለ “በጎቼን ቀበሮ በላብኝ፤ ቶሎ ድረሱልኝ” ብሎ ወደ መንደሩ ሰዎች ጮኸ፡፡ ትንሹም ትልቁም ዝርግፍ ብሎ መጣ፡፡ ግን ውሸቱን ነበር፡፡ ከዚያም በሰዎቹ “ሞኝነት” ከትከት ብሎ ሣቀባቸው፡፡ በሁለተኛውም ቀን ልክ እንደቀደመው ቀን በጎቹን ቀበሮ በላብኝ ብሎ ጮኸ፡፡ ባለፈው ከመጡትም እንደአዲስ ከሰሙትም የተወሰኑት ደረሱለት፡፡ ግን ውሸቱን ነበርና አሁንም በሰዎቹ “ሞኝነት” መሬት ላይ ወድቆ እየተንፈራፈረ በሣቅ አላገጠባቸው፡፡ በሦስተኛውም ቀን ደገመው፡፡ አሁን ግን አንድም ሰው ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ግን እውነቱን ነበር፡፡ የቀበሮ መንጋ ድንገት መጥቶ በጎቹን ለቃቅሞ በላበትና ማታ ባዶውን ወደቤቱ ተመለሰ፡፡
አዎ፣ አንድ ነገር ወረቱ ሳያልቅ ሲሆን ያምራል፡፡ ፍቅርም በወረት ነው፤ ንግድም በወረት ነው፤ የሥራ ቅልጥፍናን ስኬትም በወረት ነው፡፡ ወረቱ ያለፈ ነገር ደስ አይልም፤ ስሜትን ያጎፈያል፡፡
የፋኖም ነገር ከፍ ሲል ከተጠቀሰው መራር እውነት የሚዘል አልሆነም፡፡ በጥቃቅን ሰበር ዜናዎች አእምሮን ቢያደነዝዙት ጎመን ተበልቶ ጉልበትን በዳገት እንደመፈተን ነው፡፡ አንድን የገጠር ከተማ ለተወሰኑ ሰዓታት ወርሮ የተወሰነ ጥቃት በጠላት ላይ ማድረስ በሰበር ዜናነት የሰውን ቀልብ መያዝ የሚችለው ለተወሰነ ጊዜ እንጂ ለሁለትና ሦስት ዓመታት ሊሆን አይችልም፤ ራሳችንን አናታልል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አስቡበት፡፡ በጣት በሚቆጠሩ ሰዎች አለመግባባትና የፍላጎቶች መለያየት የተነሣ ሀገርና ሕዝብ አይጥፋ፡፡ አቢይ አንድ ወር በሥልጣን በቆዬ መጠን ኢትዮጵያና ሕዝቧ የ50 እና 60 ዓመታት ጥፋት እያስተናገዱ ነው፡፡ በልማት ስም አዲስ አበባ ጠፋች፡፡ ሌሎችም እየተከተሉ ነው፡፡ የፋኖ ጥረት ደግሞ አቢይን በተሻለ አቢይ የመተካትና ሥቃይንና መከራን የማስቀጠል መሆን የለበትም፡፡ ጭንቅላት የተሠራው ትናንትን ከዛሬ፣ ዛሬንም ከነገ በማገናዘብ መልካም ውሳኔዎችን ለመወሰን እንጂ አንዱን የሲዖል በር ዘግቶ ሌላውን ለመክፈት አይደለምና ተሰሚነት ያላችሁ ወገኖች በበረሃ ያሉ ወንድሞቻችንን ምከሩ፡፡ አራት ኪሎ የሚይዘው የሰው ብዛት አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ያ አንድ ሰው ደግሞ ራሱን የመረጠና አቢይ አዘውትሮ እንደሚለው በእናቱ ትንቢት የሚነዳ ሳይሆን በሕዝብ ቀጥተኛ ምርጫ የሚሾም መሆን ይኖርበታል፡፡ በሕዝብ ምርጫ ሥልጣን የማይዝ ሰው የሚፈራው ነገር ስለሌለ ያሻውን እያደረገ ሥልጣን ላይ መቆየት ነው ቀዳሚ ምርጫው፡፡ አቢይ ከእርሱ የተሻሉና የበለጡ ናቸው የሚባሉትን የተማሩና የሠለጠኑ አንጋፋ ዜጎችን ሳይቀር ባልተወለደ አንጀት እየቀረጠፈ ወደመቃብርና ሻል ሲልም ወደስደት የነዳው ከርሱ በላይ ዐዋቂና ከርሱ በላይ መሪ የሌለ መሆኑን ለማረጋገጥ ሲል ነው፡፡ ለሥልጣኑ እንደሚያሰጉት የሚገምታቸውን አማራና ትግሬዎችን ከነጄኔራል አሳምነው፣ ጄኔራል ገዛኢ አበራና ዶክተር አምባቸው ጀምሮ በጥይት ሲጨፈጭፍ ኦሮሞዎች ከሆኑ ግን በአብዛኛው በድርድር ከሀገር እንዲወጡለትና በዚያው እንዲያርፉለት ሲያደርግ መቆየቱ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡
ለማንኛውም ፋኖ ለራስህ ስትል ጣፍጥ፤ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ተብሎ መጣልም አለ፡፡ ልድገመው – የሥልጣን አራራና የሀብት ጥማት ከሚያቃጥላቸው እፍኝ የማይሞሉ ባላባቶች ይልቅ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጣልና በተለይ የፋኖ አመራሮች ከዚህም በላይ ሳይረፍድባችሁ ተሰባስባችሁ አንድ ነገር ወስኑ፡፡ ጊዜው ካለፈ ትርፉ ጸጸት ነው፡፡ ሁሉም እናንተን አንጋጦ ሲጠብቅ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ያ ተስፋ እየተሸረሸረ ነውና በጥልቀት አስቡበት፡፡ የተበላሸ ዕድል “ና ተመለስ በሞቴ፣ በጊዮርጊስ ባውነተህሌ” ቢሉት አይሆንም፡፡ ፈረንጆቹ እኮ Hit the iron when it is hot! የሚሉት ወደው አይደለም፡፡ አለቀ፡፡
በእውነቱ ይህ ጽሁፍ ፋኖን የሚመክር አቅጥጫ የሚሰጥ ብሎም የሚኮንን መሰለኝ። ፋኖ ነገሮች አልጋ በአልጋ የሆኑለት አልመሰለኝም ከባህር ማዶ ከሁኔታው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ዋናው ፋኖ ነን ገንዝብ ወደኛ ላክ ይባላል እዚህ የተሰበሰበው ብር በአንድ በኩል እዚህ ተሽራርፎ እራሳቸውን ሚዲያ ብለው ለሚጠሩት መተዳደሪያ ይሆናል። እንግዲህ ሰው መተዳደሪያውን ከነኩበት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ አይሆንም ተው ሲባሉ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል ስራ መስራት ካቆሙ ቆዩ አሁን ስሩ ሲባሉ ፍርሃት ፍርሃት ይላቸዋል።
እነዚሁ ሰዎች የዩቲዩብ ገበያ ለመሳብ ከስር ስር እየተከታተሉ አንዴም በድሮን ሲያስፍጇቸው በሌላው በኩል ያለው ዩቱዩበኛ ደግሞ እኔን ችላ አሉ ብሎ ይወርድባቸዋል። የተዋጣውን ገንዘብም በዲያስፖራ የሚኖሩት ዘራፊዎች ለፋኖዎች ባለማድረሳቸው ፋኖዎች ችግር ላይ ናቸው ማዋከቡን መቼም የምናውቀው ነገር ነው። ስለዚህ ፋኖዎች አጥፍተው ሳይሆን ዲያስፖራ አንድም ለስልጣን አንድም ገንዘብ በነሱ ስም ለመሰብሰብ በሚያደርገው ግብ ግብ ነገሮች ተጎትተዋል። ጎበዝ እነዚህ በዲያስፖራ ገንዘብ እየሰበሰቡ መተዳደሪያቸው ያደረጉ የካበተ የሌብነት የመበጥበጥ የማምታታት ልምድ ያላቸው ናቸው ይህም ስሩ ሲፈለግ ወደ ግምቦት 7 ላይ ያደርሰናል እነዚህ ሞራል የሌላቸው ከኢትዮጵያ ጠላቶች (ግብጽ) ሳይቀር ገንዘብ ሲቀፍሉ የኖሩ ሞራል የሌላቸው ናቸው። በእርግጥ የነጻነት ቀን ሲቀርብ ብርሃኑ ነጋ፤ነአምን ዘለቀ፤ታማኝ በየነን የመሳሰሉ ዘራፊዎች በህግ ፊት እንደሚቀርቡ እምነታችን ነው።
ባጠቃላይ ፋኖን ተውት ከሃገር ውስጥ ቱባ ቱባ የሚያህሉ አባላት አሉለት ከባህር ማዶ እነ ፕሮፌሰር ሓብታሙ፤አቻምየለህ ታምሩ፤አቶ ተክሌ የሻውን የመሳሰሉ በሳል አመራር ሊሰጡት የሚችሉ ዜጎች ስላሉለት አመራር እንስጥ ገንዘብ በስምህ ሰብስበን ቤትና መኪና እንግዛበት አትበሉት። አሁን ግምቦት 7 በተለይም ታማኝ በየነ በኢትዮጵያን ስም የሰበሰበውን ገንዘብ ኦዲተር ቢታዘዝበት ምን ከምን ያደርገዋል እንደው ዝም ነው እንጅ። ለነገሩ “የብዙ ሰው ገንዘብ ብላ የብዙ ሰው ዘመድ አትንካ” ይል የለ? ፋኖ በርቱ በራችሁን ጠርቅሙ ከኛ በላይ ላሳር ነው የምትሉ አመራሮችም ለቃችሁ ተራ አባል ሁኑ እያንዳንዳችሁን እናጠናለን እኛ ካልደገፍን የሚሆን ነገር የለም።ጌታ ከለላውን ይስጣችሁ ብርሃኑ ነጋ፤ ግርማ…ኢዜማን በለጠ ሞላን ሁናችሁ መኖር ትችሉ ነበር የሞራል ጉዳይ ሁኖባችሁ ነው።
This is it!!!
በፋኖ ላይ የደረሰው ትልቁ ጥፋት ገንዘብን አላግባብ መጠቀም ወይም የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ዲያስፖራ ግለሰቦች የመገፋፋት ጉዳይ አይደለም።
በፋኖ ላይ የደረሰው ትልቁ ጥፋት ከፋኖ አመራሮች ጋር በየቀኑ ለሰዓታት በመነጋገር የሚዲያ ሰራተኞች እና ዲያስፖራ ግለሰቦች የሚያባክኑት ጊዜ ነው። የፋኖ አመራሮች በየቀኑ ከአንድ ወይም ከሌላ ዲያስፖራ አካል ጋር ማለቂያ የለሽ የስልክ ውይይት በማድረግ ወደ አንድ አመት ገደማ አባክነዋል (እንዲባክንባቸው ተደርጓል) ። በዚህ መልኩ የሚባክን ጠቃሚ የአመራር ጊዜ ምን ያህል ጊዜ እንደሆነ እናስብ። ይህ ጠቃሚ ጊዜ የፋኖ መሪዎች ታጋዮቻቸውን በማደራጀት፣ ነፃ በወጡት አካባቢዎች ዜጎችን በማስተማር፣ የፋኖ ድጋፍ ሰጪ ክፍሎችን በከተማ እና በገጠር በማደራጀት፣ ስልታቸውንና የትግል ዘዴዎችን በመገምገም፣ ወዘተ.ለትግሉ ስኬት ሊጠቀሙበት ይችሉ ነበር።
ያ ወርቃማ ጊዜ በከንቱ በመጥፋቱ የጅምላ ገዳይ እና ገዥው አካል እንዲያገግም እና እንዲደራጅ ጊዜ ሰጠው
እየተካሰሱ ሲልላቸው ደግሞ እየተጋደሉ
ለእኔ ብቻ ብለው ድርሻን እያባዙ
በብሄር ተሳክረው በቋንቋቸው ጦፈው
ኑ ግጠሙን አሉ ሰላምን ገፍትረው
ረብ የለሽ ነገር ፍሬ እማያፈራ
ወሎ ላይ ተቀምጦ ልቡ አዲስ አበባ። (ጥር 6, 2017 ዓ.ም)
አተላው የሃበሻ ፓለቲካ ዝንተ አለም እንደፎከረና እንዳስፎከረ ከራሱ ጋር ሳይታረቅ ግባተ መሬቱ ሲቀድመው አይተናል እያየንም ነው። ወደፊትም የሚሆነው ይኸው ነው። ከየትም ይሁን ከየት በትጥቅ ትግል የሚመጣ ለውጥ የወረፋ ጨቋኝ እንጂ ከቀደመው የተሻለ አይሆንም። ይህን ካለፈው ታሪካችን መረዳት ይቻላል። ንጉሱን በወሎ ረሃብ አሳቦ ይዘልፋቸው የነበረው የወታደር ስብስብ በ1975-1980 ዓ. ም በሃገሪቱ የነበረውን አሰቃቂ ረሃብ እንደ ሰው ቅነሳና እንደ ፓለቲካ መሳሪያ ተጠቅሞበታል። ያ ጨካኝ የወታደር መንጋ ሲበተን በኤርትራ ሻቢያ ከቁራሽ በተረፈችው ኢትዮጵያ ወያኔ የሃገር አለቆች ሲሆኑ ደርግን ኮንነው ራሳችውን አልቀው በማሳየት ምድሪቱን አምሰዋታል እያመሷትም ይገኛሉ። ከ 27 ዓመት የመከራና የሰቆቃ ጊዜ በህዋላ ህዝባችን እፎይታ አገኘ ተብሎ በውጭና በሃገር ውስጥ ዳንኪራ ሲረገጥለት የነበረው የአብይ መንግስት አሁን ላይ አበስ ገበርኩ የሚያሰኝ እንደሆነ የየቀኑ ወሬዎች ተበርዘውና ተደልዘውም ቢሆን እየነገሩን ይገኛሉ። ታዲያ በዚህ ሁሉ የፓለቲካ ስንክ ሳር ውስጥ እንሆ ዛሬም ፋኖ፤ ኦነግ – ሸኔ ገለመሌ በሚሉ ስሞች የህዝባችን መከራ የሚያባብሱ ጠበንጃ አምላኪዎች ህዝባችን እንደ ገና ዳቦ ከላይና ከታች እሳት እንዲወርድበት ምክንያቶች ሆነዋል።
ፋኖ የአማራ ህዝብ ጠላት ነው። ኦነግ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነው። ወያኔ የትግራይ ህዝብ መከራ አዝናቢ ነው። የእነዚህ የጥፋት ሃይሎች መንግስት ነኝ ከሚለው ጋር ተዳብለው ምድሪቱን እቶን እያደረጓት ለመሆኑ ዋቢ አያስፈልግም። ታዲያ ነገርየው ሁሉ እንዲህ አሰልቺና ለእኔ ብቻ ከሆነ መፍትሄው ምንድን ነው? መፍትሄው መደራደር፤ ወደ ሰላም መመለስ፤ ለአሸናፊው ሃሳብ ተገዢ መሆን ነው። መናቅ መናናቅ ያኔም አሁንም ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል። ለሃገርና ለህዝብ ሲባል ሁሉም ተደራድሮ በበቃ ተማምኖ በሰላም ሰርቶ ለመኖር መጣር አለበት። እልፍ ት/ቤቶች ተዘግተው፤ የሚያመርቱ ገበሬዎች ሥራ ፈትተው፤ መንገዶች ተዘግተው፤ በየቀኑ ሰዎች እየታፈኑና እየተገደሉ ባለበት በዚህ ጊዜ ላይ ገዳይና አፋኝን እንኳን ለመለየት አይቻልም። የመንግስት ሃይሎች ያፍናሉ፤ ፋኖ ያፍናል፤ ወያኔ ያፍናል ኦነጎች ያፍናሉ። አንድ በሌላው ያሳባል። እውነቱ ግን ሁሉም ግፈኞችና ቀማኞች ናቸው። ጠበንጃ አንጋች በጭንቅላቱ ያሰበበት ጊዜ በታሪክ የለም። በአፈሙዙ እንጂ! አሜሪካዊው ጄኔራል በትለር “War is a Racket” መጽሃፍ ላይ እንደሚለን በስቃይ ውስጥ በሰው ደም የሚነግድ አትራፊዎች እንዳሉ ነው። ጦርነት ለማንንም ነገር ጠቅሞ አያውቅም! አንብቡትና ንቁ!
ለእኔ የፋኖ አደረጃጀት የፋኖ መግለጫና ስብሰባ ሁሉ ዝም ብሎ እሪ በከንቱ ነው። ህዝብን እየጨረሱና እያስጨረሱ፤ የሚማሩ ልጆችን እድል እየዘጉ፤ በፋኖና በመንግስት ታጣቂዎች በሚደረገው ፊልሚያ ሰው በዚህም በዚያም እየተጎዳ ነጻነት ብሎ ነገር የለም። ለእኔ የሚታየኛ አንድ ነገር ብቻ ነው። በተሎ ወደ ልባችን ተመልሰን ጦርነት ካላቆምን ሃገሪቱ ከመፍረስ አትድንም። ስነ ልቦናው በክልል ፓለቲካ የጠነበዘ ህዝብ ይዞ ሃገራዊ ፍቅርና አንድነት ሊኖር አይችልም። እናስብ ወያኔ ክልሎችንና ቋንቋን ተገን አድርጎ ሃገሪቱን የሸነሸናት ከጣሊያኖች ተምሮ ነው። ጣሊያኖች ያደረጉት ይህኑ ነበር! መለስ ብላችሁ ያለፈ ታሪክን ማየት አስፈላጊ ይመስለኛል። እኛ ስንገዳደል እነርሱ ሊኖሩ። አይ መጃጃል…. አክ እንትፍ የዘር ፓለቲካ! ፋኖም ተሳክቶለት በዚህም በዚያም ከሌሎች ጋር ተዳብሎ በወረፋ ሚኒሊክ ቤ/መንግስት ቢገባም በምድሪቱ ሰላም አይኖርም። እንዲያውም አሁን ካለው የመከራ ባህር ይልቅ የያኔው የጠለቀና የከፋ ይሆናል። ለዚህ ነው በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሰውን በምርጫና በሃሳብ ማሸነፉ ጦር ከመስበቅ የሚሻለው። ስለዚህ ለፋኖና ለሌሎችም ታጣቂ ሃይሎች ሁሉ ምክሬ አንድ ነው። ተደራደሩና በሰላም ወደ ህብረተሰቡ ተመልሳችሁ በጥምርም ሆነ በተናጠል ፓርቲ አቋቁማችሁ ለምርጫ ራሳችሁን አቅርቡ። የድር የገደሉ ውጊያ ለሻብያም ሆነ ለወያኔ አልጠቀመም። በቃ በሉ። አዲስ ሃሳብ አምጡ። ሁሌ ጠበንጃ አንግቦ እንዘጥ እንዘጥ እያለ ህዝብን የሚያተራምሰውን ሃይል እኮ አየነው። ከእጅ አይሻል ዶማ ሲሆን… ጦርነት ይብቃን!
ተስፋይ
ፓርቲ አቋቁማችሁ በምርጫ ወደ ስልጣን ቅረቡ ነው የምትለን ብዙ ጊዜ ፋኖ ገዳይ እንደሆነ ወደ ስልጣን ቢመጣም የባሰ እንደሚሆን ነው የገለጽክልን። ህወአት፣ ኦነግና ብልጽግና የሚያዱርሱት በደል ብዙም ወደ ልብህ አይደርስም። አመጽ ስለወደዱ ወደ አመጽ ሄዱ እንጅ ዲሞክራቲክ በሆነ መልኩ ወደ ተሻለ አመራር ይደረሳል ነው የምትለን። እንዲህ አይነቱን አስተያየት ለመገንዘብ ጥልቅ እውቀት ሳይጠይቅ አይቀርም ደጋግመን እናነበዋለን።
እኔ ብልጽግና በደል አላደረስም አያደርስም ብዬ አላውቅም። እንኳን በቋንቋውና በዘሩ የጠነበሰው የኦሮሞ ስብስብ ቀርቶ ሃገር ሃገር የሚለው የአማራው ስብስብም የዘር ፓለቲካን ተገን ማድረጉ ግልጽ እየሆነ ነው። በቋንቋ፤ በብሄርና በክልል የተተበተበ ትውልድ ለራሱም ለሌላውም አይበጅም ባይ ነኝ። ብልጽግና በደል አያደርስም፤ አያፍንም፤ አይገድልም፤ ከሥራ አያባርርም የሚሉን ካሉ እንደ ተለመደው ፍርፋሪ ለቃሚዎችና ተለጣፊ ድርጅቶች ብቻ ናቸው። በቅርብ ከአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የተባረሩት እነማን ናቸው? በቋንቋና በዘር ሥራና ስልጣን በሚታደልበት ሃገር ላይ ፍትህ አለ ማለት ራስን ማጃጃል ነው። በወያኔ ጊዜ እስር ቤቱ ሁሉ ኦሮምኛና አማርኛ ይናገር እንደነበረው ዛሬ ላይ ደግሞ አማርኛ ተናጋሪው የሚታጎርበትና የሚጋዝበት እንደሆነ አይንና ጀሮ ያለው ይረዳዋል። የሚያጠቡ እናቶችን፤ በእድሜ የገፉ አዛውንቶችን አስሮ የሚያሰቃይ መንግስት ምንም የቃል ድርደራው ቢበዛ ለእኔ ከደርግና ከወያኔ ቢከፋ እንጂ የተሻለ ነገር የለውም።
የእኔ ጭምቅ ሃሳብ መገዳደሉ ገደብ የለሽ በመሆኑ ጦርነትን አቁሞ፤ የታሰሩ እንዲለቀቁና ሌሎችም የፓለቲካ ጥያቄዎችን መልስ እንዲያገኙ አድርጎ ለህዝባችን ሰላምና ለሃገሪቱ የአሁንና የወደፊት ደህንነት ሲባል ይቅር በመባባል በሰላም መኖሩ ይሻላል ባይ ነኝ። ከዚህ ውጭ የዘርና የቋንቋ የክልል ፓለቲካ አክ እንትፍ እላለሁ። አቋሜ ይሄ ነበር አሁንም ወደፊትም ነው። ሰው የሚመዘነው በሰውነቱ ብቻ! አምናለሁ ሃሳቤ እንደሚረዳህ።
እንዲህ እቅጭ እቅጩ መነጋገርና እባጮችና ቁስሎች እንዲታከሙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ዝምታና ፍራት አሁን ለደረስንበት ውድቀት አብቅቶናል፡፡ዲያስፖራውም እየጠፋ ያለውን ሕዝብ ቅድሚያ ይስጥ፡፡ ሥልጣንና ሌላው ይደረስበታል፤ ሀገር ስትኖር፡፡
Well and yes, forwarding critical and balanced and realistic opinion is absolutely important if we have to move forward and accomplish a great history of a generation !
However, if our opinions are emotion- driven, we will terribly miss and disregard our very long and horrible political discourses and experiences that have made our political struggle very challenging like the one we are witnessing in the case of Fanno .
Yes, we have to be straightforward and clear when we forward our critical opinions . But we at the same time have to be very careful to look at and understand the very hard reality on the ground as far as the very miserable political systems we have come across and what is going on right now.
Yes, Fano desperately needs to do much and much better by making a real and efficient way of doing things!
However, the very approach and content of the above piece of writing is not only simplistic but also so emotional and kind of wishful thinking . It didn’t sincerely acknowledge and appreciate what has been done in the last 1 1/2 year!
The story of the cowboy is inappropriate for the story of Fabian !! This is not the right way of constructive criticism !
Yes, we need to talk or write to the extent of calling a spade a spade and showing the right way how to get out of the age old and unbelievably horrifying political situation !
But it must be in such a way that it reflects the reality on the ground and it encourages those who had paid and keep paying very priceless sacrifices !!!!
Let’s control our uncontrolled emotions and help the very though fight against the ruling elites of the very ugly and dangerous political gambling of ethnic identity!!!!
I believe Mr/Mrs Tg has gone emotional himself/herself. The writer reflected what he thinks is nice towards his country with regard to Fanno. And it is good to do so instead of keeping silence as many of us. But most of we habeshas are fond of discouraging people who want to give constructive ideas such as this guy and we try to make them quiet. Why? I don’t think it is good. We can fill the gap that such writers haven’t covered and we can write pieces of our own that focus on our interests instead of demoralizing and mistreating them. Frankly speaking I couldn’t see any significant error or wrong in this piece of writing. That is why I couldn’t help giving this comment under Tg. And sorry if I made a mistake.