የሕገ መንግሥት ለውጥ – ለኢትዮጵያዊነት የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጉዳይ – ኪዳኔ ዓለማየሁ

ራዕይ፤ ዓላማና እቅድ፤ ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ሕገ መንግሥት ማዘጋጀቱና ተግባራዊ የማድረጉ ራዕይ ውድ ሐገራችን ከጽንፈኛነት፤ ከዘረኛነትና ከጭቆና የተላቀቀ ኢትዮጵያዊነት፤ ሰላም፤ ጸጥታ፤ አንድነት፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ፤ ሕብረት፤ መከባበር፤ ፈጣን ልማት፤ ወዘተ. የሰፈነባት ሐገር እንድትሆን ለማረጋገጥ ነው። ይህ ራዕይ ስኬታማ እንዲሆን፤ በአጭር ጊዜ (1 ዓመት)  ብቁ በሆኑ ባለሞያዎች የተሟላ ረቂቅ ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅና በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በጥልቀት እንዲመለከተው ማድረግ፤ ከዚያም፤ አስፈላጊው ማሻሻል ተከናውኖ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመላው ሕዝብና ለሚመለከታቸው ድርጅቶች ቀርቦ እንዲመረመር በመጨረሻም ተቀባይነት በሚኖረው ብሔራዊ ጉባኤ ሕገ መንግሥቱ እንዲጸድቅ ሆኖ በሚቀጥሉት ዓመታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሚመረጥ ምክር ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ማሻሻል ይቻላል።   የአሁኑ ሕገ መንግሥት ሰቆቃዎች፤ እንደሚታወቀው፤ በአሁኑ ጊዜ … Continue reading የሕገ መንግሥት ለውጥ – ለኢትዮጵያዊነት የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጉዳይ – ኪዳኔ ዓለማየሁ